Get Mystery Box with random crypto!

አትድገመው በሕይወት ጉዞ ውስጥ ደጋግመን የምናደርጋቸው ብዙ ነገሮች ያሉትን ያክል የማይደገሙ ነ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

አትድገመው


በሕይወት ጉዞ ውስጥ ደጋግመን የምናደርጋቸው ብዙ ነገሮች ያሉትን ያክል የማይደገሙ ነገሮችም አሉ በቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ውስጥ የማይደገሙና የሚደገሙ ነገሮች መኖራቸውን ሁላችሁም ታውቃላችሁ።በያንዳንዳችንም ሕይወት ውስጥ የሚደገሙ እና የማይደገሙ ብዙ የሕይወት ምሥጢራት አሉ
ልደት ይደገማል፣ ሞት ይደገማል፣ መብል መጠጥ ይደገማል፣ ቁርባን ይደገማል በጎ ንግግር ይደገማል ሌላም የሚደገሙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።
በል አንተም ደግመህ ደጋግመህ ተወለድ ከማኅፀነ አንስት በሥጋ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ በመንፈስ፣ ከማኅፀነ ኃጢአት በንስሐ፣ ከከርሰ መቃብር በትንሣኤ መወለድ ትችላለህ። ከዚያም በላይ ራስህን በመልካም ሥራ ውለድ እንጅ ከማንም በመወለድህ የምትኮራ አትሁን።
መወለድ መልካም ሰለሆነ ክርስቶስ እንኳን ሁለት ልደታትን ተወለደ
ይህ ሁሉ የልደት ድግግሞሽ ለምን ይመስልሃል? አንተ በሕይወት እንድትኖር እኮ ነው። ምክንያቱም ሞት የሚደገም ሆኖ ሳለ ሕይወት የማትደገም ስለሆች ነው ሕይወት አንዲት ናት አትደገምም ትዳር አይደገምም ክፉ ቃል አይደገምም
ምስጋና ግን ይደገማል ለዚህ ነው ጌታ በመጀመሪያ ስብከቱ ብቻ ዘጠኝ ጊዜ ብፁዓን ብፁዓን ብሎ ተናግሯል። ወንጌል በምስጋና ተጀምራ በምስጋና የምትፈጸም የምስጋና መጽሐፍ ናት።
አንተ ግን ርግማንን ትደግማለህ ስህተትን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ትቆጥራለህ ባንድ ቀን ስህተት በዘመንህ ሁሉ በኅሊና ወቀሳ ሥር ትኖራለህ እባክህ ኃጢአት አይደገምም ይህን ብታደርግ ደጋግመህ ትሞታለህ ስህተትን ብትደግም ለዘለዓለም በማያቋርጥ ቅጣት ውስጥ ትኖራለህ
በነገራችን ላይ ስህተትን አትድገም ስል አንድ ጊዜ አድርግ ማለቴ አይደለም ያሰብከውን በገቢር ወይም በነቢብ አትድገመው ለማለት ነው።(ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ)



ዲያቆን ፍፁም ከበደ


https://t.me/zdfitsumkebede
https://t.me/zdfitsumkebede