Get Mystery Box with random crypto!

የስደተኞች ምርኩዝ ...የመጀመሪያዎቹ የእስልምና ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ንጉሡ እንዲቀበሏቸ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የስደተኞች ምርኩዝ

...የመጀመሪያዎቹ የእስልምና ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ንጉሡ እንዲቀበሏቸው ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ የስደተኞች ምርኩዝ ድንግል ማርያም ስላግባባቻቸው ነው።

መሐመድ ወገኖቹን ወደ ኢትዮጵያ እንዲሔዱና ከአሳዳጆቻቸው እንዲያመልጡ በመከራቸው መሠረት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች በንጉሡ እልፍኝ ቀረቡ። ከእነርሱም ጃፋር አቡ ታሊብ የተባለው ንጉሡ ስለ እምነታቸው በጠየቁት ጊዜ ቀድሞ ጣዖት አምላኪዎች እንደ ነበሩ፣ ሰብአዊነት በጎደለው መልኩ ይገዳደሉ እንደ ነበርና ምግባራቸውም መልካም እንዳልነበር ገልጾ ነቢያቸው መሐመድ እስልምናን ካስተማራቸው በኋላ ግን በአንድ አምላክ ማምለክ እንደ ጀመሩ አስረዳቸው። ንጉሡም በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ እንደሆንና ስለ እርሱ ምን እንደሚሉ በቅድሚያ ጠየቁት። ጃፋርም 'በእውነት ክርስቶስ ኢየሱስ፣ የማርያም ልጅ፣ የእግዚአብሔር መልእክተኛ፣ ወደ ማርያም የተላከ ቃሉና ከእርሱ የወጣ መንፈስ ነው' ሲል ከቁራን ጠቅሶ ተናገረ። በማስከተልም ንጉሡ ስለ ድንግል ማርያም ቢጠይቁት ከሉቃስ 1:47-55 የተገለበጠውን የቁራን ጥቅስ ጠቅሶ '(ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፣) መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች...' ብሎ መሰከረ። ንጉሡ ይህን ጸሎተ ማርያም በኢአማኒው አንደበት ሲሰሙ የጉንጫቸው ጺም በዕንባቸው እስኪርስ ድረስ በስሜት አለቀሱ... አብረዋቸው የነበሩት ጳጳሳትም እንዲሁ መጽሐፎቻቸው በዕንባቸው እስኪርሱ ድረስ አለቀሱ። ከዚህ በኋላም ንጉሡ ስደተኞቹን በደንብ እንዲጠበቁ አደረጉ።"

(ከ"የመሰጠት ሕይወት" ገጽ 113-114 የተወሰደ)

ዲያቆን ሕሊና በለጠ


https://t.me/ZDfitsumkebede