Get Mystery Box with random crypto!

'ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ' ዛሬ (ሰኔ 27) በዓሉን የምናከብረው ሶርያዊው አባታችን ቅዱስ ያዕቆ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ"

ዛሬ (ሰኔ 27) በዓሉን የምናከብረው ሶርያዊው አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ: በልጅነቱ ከእናቱ ዕቅፍ ወርዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሮጦ: ኋላም ካህኑ አቅፈው ካቆረቡት በኋላ "ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ" ብሎ ነበር።

"አንሰ እፈርህ ሠለስተ ግብራተ ወይእቲ
ጸአተ ነፍስ እምሥጋ፤
ወተራክቦ ምስለ እግዚአብሔር፤
ወጸአተ ፍትሕ ላዕሌየ
-
ሦስት ነገሮችን እፈራለሁ። እኒህም
የነፍሴ ከሥጋዬ መለየት፤
ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘትና
ፍርድ መስማት ናቸው" እያለ ማልቀስ ጀመረ።

የነፍስ ከሥጋ መለየት ቅዱሱን እንዲህ የሚያስፈራ ከሆነ እኛን ኃጥአኑን እንዴት ማስፈራት ይገባው ይሆን?

በእግዚአብሔር ፊት መቆምና እግዚአብሔርን ማግኘት ለምግባረ ሰናዩ ደራሲ እንዲህ የሚያስደነግጥ ከሆነ ለእኛ በየዕለቱ በክፉ ምግባር ለምናድፈው ምን ያክል የሚያንቀጠቅጥ ይሆን?

ሃይማኖቱና ምግባሩ የሰመረለት ይህ ቅዱስ በራሱ ላይ የሚሰማው ፍርድ እንዲህ የሚያርደው ከሆነ: እኛ ከእጅ ጣት ቁጥር የማይበልጥ መልካምነት ያለን የጽድቅ ምንዱባን ምን ያክል ልንፈራ ይገባን ይሆን?

የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በረከት አይለየን። ምግባራችንን ያቅናልን!


ዲያቆን ሕሊና በለጠ


https://t.me/ZDfitsumkebede
https://t.me/ZDfitsumkebede