Get Mystery Box with random crypto!

Zaphnath-paaneah

የቴሌግራም ቻናል አርማ zaphnathpaaneah1 — Zaphnath-paaneah Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zaphnathpaaneah1 — Zaphnath-paaneah
የሰርጥ አድራሻ: @zaphnathpaaneah1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 648

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-04 16:49:07 እውነትም ግን እንደ አምላካችን ያለ ግን ማነው????

መዝሙር 113
⁵ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በላይ የሚኖር፤
በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤
⁷-⁸ ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፤
⁹ መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት
። ሃሌ ሉያ።

እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው ይልና...የሚዘረዝረውን ተመልከቱ:-

1. የተዋረዱትን የሚያይ
2. ችግረኛን ከመሬት የሚያነሳ
3. ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ
4. መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፤ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት

ሃሌሉያ

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
809 viewsYonatan Worku, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 15:07:55 የንጉስ ልጅ ሆይ ስለምን ከሳህ??
(ከመንፈሳዊ ክሳት መዳን)

“እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።”2ኛ ሳሙኤል 13፥4

መቼስ ሰው ጎዳና ላይ እየኖረ ለምን ከሳህ ተብሎ አይጠየቅም፤ እንደዚህ ፀሃዩና ቁሩ እየተፈራረቁበት...በንጉስ ቤት እየኖሩና የላመውንና የነጣውን እየበሉ መክሳት ግን ለሰሚ ሁሉ ግራ ያጋባል!!

አምኖን መዋል የማይገባውና መውደድ የሌለበትን የማይመጥነውን ነገር መውደድና መፈለግ ሲጀምር ይሄ ነው የማይባል ክሳት ውስጥ ገብቶ ይሰቃይ ጀመር፤ የንጉስ ቤተሰብ መሆኑና የተመረጡ ምግቦችን መመገቡ ከክሳት አላዳኑትም...እንደውም ከቀን ወደ ቀን ክሳቱ ይጨምር ነበር!!

ዘንድሮም እንዲሁ ነው....በጣም ብዙ ሰዎች በንጉሱ እግዚአብሔር ቤት እየኖሩ ክሳት ግን ይታይባቸዋል፤ ያውም ከስጋ የሚብስ የነፍስ ክሳት...ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የማይገባንን ነገር ከመውደድና የማይመጥነን ስፍራ ላይ ከመገመት የሚመነጭ ነው!!

እስራኤላውያንም ከግብፅ ወጥተው ምድረበዳውን ወደ ከነዓን በመሄድ ላይ ሳሉ የማይገባ ምኞት ውስጥ ገብተው እግዚአብሔርን በማሳዘናቸው ለክሳት ተዳርገዋል!!

መዝሙር 106
¹⁴ በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
¹⁵ የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።


ከእግዚአብሔር ቤት ውጪ ሆነው ስለከሱት አይደለም የማወራው፤ ይልቁንም እያገለገሉ የከሱ፣ እየዘመሩ የከሱ፣ እየሰበኩ የከሱ፣ እየተነበዩ የከሱ፣ እየፀለዩ የከሱ....ሰማይ ነሃስ ምድር ደግሞ ብረት የሆነችባቸው.....እግዚአብሔር ከውስጥ ክሳት ያስመልጠን....የእግዚአብሔርን ዕቃ እንደሚሸከም የተመረጠ ሰው ከማይመጥነን ስፍራ እንውጣ...ሻሎም

“ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።”2ኛ ቆሮ 6፥17-18

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
1.0K viewsYonatan Worku, edited  12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 15:22:42 በእርግጥ ይህንን ታውቃላችሁ??
(ያለ እግዚአብሔር ፀጋ ምንም ነን!!)

ሩጫ ለፈጣኖች
ሰልፍ ለሃያላን
እንጀራ ለጠቢባን
ባለጠግነት ለአስተዋዮች
ሞገስ ለአዋቂዎች ...አይደለም

“እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።”
መክብብ 9፥11

የአግዚአብሔር ፀጋ ብቻ በዘመናት መካከል ታሪክ የሌላቸውን ሰዎች ባለታሪክ ይደርጋል፤ ዕድልንና ዘመንን ይሰጣል!!

ፀጋ የበዛላቸው ሰዎች የ30 እና 40 አመቱን መንገድ በ6ት ወርና በ1 አመት ይሄዱታል!!

“እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።”
2ኛ ቆሮ 12፥9

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
479 viewsYonatan Worku, edited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 03:28:10
@ZaphnathPaaneah1
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
473 viewsYonatan Worku, edited  00:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 15:16:22 ሣንባ ይዘህ ድመት ማባረር አትችልም!!

የድመት ማለፊያ ምግብ የሆነውን ሣንባ ይዘህ ድመቷን ለማባረር መሞከር ከንቱ ልፋት ነው....በተመሳሳይ ሁኔታ የሰይጣንን ግሳንግስ እየሰበሰብን እሱን ለመቃወም መሞከር በድንጋይ ላይ እንደማፍሰስ ይቆጠራል!!

በተለይ ስለመንፈሳዊ ውግያ ስንነጋገር ሁለንተናዊ ማለትም በህይወታችን ሁሉ የምናደርገው እንጂ ስንፀልይ ብቻ የጌታን ስም ጉሮሮዋችን እስኪነቃ እየጮህን የምንጠራበት ጉዳይ ብቻ አይደለም....ህይወታችንን በንፅህናና በቅድስና መጠበቅ በራሱ አንደኛው የመንፈሳዊ ውግያ መገለጫ ነው!!

አንዳንድ ግዜ ሰይጣን ዙሪያችንን እየዞረ አልፋታ ያለን ከእኛ ጋር ካለው የመለኮት ኃይል በልጦ ሳይሆን የማይገቡ ነገሮች በጓዳችን ተሸሽገው ስላሉ ይመስለኛል፤ ባለንብረቱ ደግሞ ንብረቱን ፈልጎ ከኃላ ከኃላ እኛን መከተሉ አይቀርም!!

ወዳጆቼ ሆይ በስውር ያስቀመጥናቸው(የደበቅናቸው) ለእግዚአብሔር ክብር የማይመቹ ጉዳዮች(ልምምዶች) በቤታችን ይኖሩ ይሆን???? ላባ እኮ ያዕቆብን የሰባት ቀን መንገድ የተከተለው ሳይነግረው ስለሄደ ብቻ ሳይሆን ራሔል ተራፊሙን ሰርቃበት ስለሄደች ጭምር ነው:-

ዘፍጥረት 31
²² በሦስተኛውም ቀን የያዕቆብ መኮብለል ለላባ ተነገረው።
²³ ከወንድሞቹም ጋር ሆኖ የሰባት ቀን መንገድ ያህል ተከተለው፥ በገለዓድ ተራራም ላይ ደረሰበት።

ይህንን ቁጥር 30 ላይ ማግኘት እንችላለን:-

“አሁንም የአባትህን ቤት ከናፈቅህ ሂድ ነገር ግን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ?”ዘፍጥረት 31፥30

ምናልባት የእኛ ያልሆነ(የሰረቅነው) ነገር በጓዳችን ይኖር ይሆን??....ይህንን ነገር ከቤታችን ጠራርገን እስካላወጣን ድረስ ጠላት እያነፈነፈ ዙሪያችንን መዞሩን አይተውም፤ ምክንያቱም የተሰረቀ ነገር ሁሉ ባለቤት አለው!!

የጨለማውን አለምንና እርግማንን ወደ ህይወታችን ከሚስቡ ነገሮች ሁለንተናችንን መጠበቅ አለብን....ያን ግዜ የክብር ዕቃ ሆነን በትውልዱ መካከል በክብር እንገለጣለን....ፀጋ ይብዛልን!!

“ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፤”ዘፍጥረት 35፥2

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
786 viewsYonatan Worku, edited  12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:54:07 ጌታዬ ሆይ እንደ ዕዝራ ክብርህንና ማዳንህን ለማውራት የማልዘገይ ፈጣን ፀሃፊ አድርገኝ!!!

የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው በሙሴ ሕግ ፈጣን ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ የሻውን ሁሉ ሰጠው።” ዕዝራ 7፥6

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
834 viewsYonatan Worku, edited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:22:29 የበግ ለምድ የለበሰ አውሬ!!
(እውነት ውሸት እላችኃለሁ)

አውሬነቱ እንዳይታወቅበት የበግ ለምድ በመልበስ የሚታወቀው ጠላታችን ዲያቢሎስ መሆኑን ጠንቅቀን መረዳት አለብን!!

ነፍሰ በላው ዲያቢሎስ ወደ ሰዎች ህይወት ሲመጣ በአውሬነቱ(በጨካኝነቱ) ሳይሆን አውሬነቱ ላይ የበግ ለምድ ስለሚደርብበት የሚመስለው አውሬ ሳይሆን አዛኝ ቅቤ አንጓች(ሩህሩህ) ነው!!

ወደ ሰው ህይወት ዘልቆ ከገባ በኃላ ግን እውነተኛ የአውሬነትና የገዳይነት ባህሪው መገለጥ ይጀምራል....ለዚህ ም ነው መፅሃፍ ቅዱሳችን ዲያቢሎስ ሀሰተኛ ብቻ ሳይሆን የሀሰት ሁሉ አባት እንደሆነ የሚመሰክርልን:-

“እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።”ዮሐንስ 8፥44

ጠላታችን በአስመሳይነትና አታላይነት የሚመስለው ማንም የለም፤ ተክኖበታል....እርሱ የውሸቶች ሁሉ አድራጊ ፈጣሪ ሲሆን ንግግሩ ብቻም ሳይሆን የቆመበት መሠረት እንኳን ሀሰት ነው!!

ኢየሱስ ሲናገር እውነት እውነት እላችኃለሁ የሚለው በእውነት ጀምሮ በእውነት ስለሚጨርስና በንግግሩ ውስጥ አንዳች ውሸት ስለሌለ ነው....እባቡ ግን እንዳይነቃበት በእውነት ይጀምርና በውሸት ይጨርሳል፤ እውነት ውሸት እላችኃለሁና ማለት ይህም አይደል!!

“ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።”2ኛ ቆሮ 11፥14

የሰይጣን አስመሳይነት ይሄ ነው ተብሎ በቀላሉ የሚቀመጥ አይደለም፤ አጭበርባሪነት የብዙ ሺህ አመታት ማንነቱና ልምዱ ነው......ከአዳምና ሔዋን ጀምሮ ብዙዎችን በማታለልና በማጥመድ የአላማው ማስፈፀሚያ ሲያደርጋቸው ኖሯል....ዛሬ እግዚአብሔር የሚያወራን እኛም ብንሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ተታልለን እንዳንወድቅ ስለሚፈልግ ነው!!

“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።”2ኛ ቆሮ 2፥11

አቤት ስንቶች በዚህ የሰይጣን ሽንገላ ተታልለው ወደቁ.....ዛሬ መንፈስ ቅዱስ በኃይል ዐይኖቻችንን ከፍቶ እንዲያነቃን እፀልያለሁ፤ መናፍስትን የምንለይበት ቅባት ያግኘን......የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና ያደረገ ጌታ በህይወታችን ሁሉ ላይ በድብቅ የተመከረውን ምክር ሁሉ በኢየሱስ ስም ያፈራርስልን......ባለማወቅ በጠላት ወጥመድ ውስጥ ለገቡ ሁሉ እፀልያለሁ በኢየሱስ ደም ጉልበት ማምለጥ ይሁንላቸው....ጌታ ሆይ በዘመናችን የውርደት ሳይሆን የክብር ዕቃ ሆነን እንድናልፍ ፀጋህ በሙላት ይለቀቅልን...ከራሳችን አልፈን ለዚህ ትውልድ በረከት እንድታደርገን እፀልያለሁ....አሜን!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
863 viewsYonatan Worku, edited  08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 04:17:15
.                  ሥነ መላዕክት


የትምሕርት ጊዜ
አርብ 13/08/2015
ከ12፡30 - 2፡00 ሰዓት
በብስራተ ወንጌል ገነት ቤተክርስቲያን
(ከዘነቦርቅ የ72 ባጃጅ መዞሪያ)

ዕብራውያን 1
¹³ ነገር ግን ከመላእክት፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ብሎአል?
¹⁴ ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
494 viewsYonatan Worku, edited  01:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:47:35 የሚፀልይ ሰው ትዕቢተኛ አይደለም!!

ሁላችንም እንደምንረዳው ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበትና ሸክማችንን በፊቱ አራግፈን አዲስ ሰው ሆነን የምንነሣበት አስደናቂ የመሰዊያ ስፍራችን ነው....ስለዚህ ድንቅ እውነት እግዚአብሔር ይባረክ!!

ሆኖም ግን ፀሎት ልመናችንን በእግዚአብሔር ፊት የምናቀርብበት መንገድ ብቻ አይደለም ይልቁንም እጅግ ብዙ ምስጢሮች አሉት....በነገራችን ላይ የፀሎት ምስጢሮች በግልፅ የሚገቡን በዋነኝነት ስንፀልይ ነው፤ ልክ መኪናን እስካልነዳን ድረስ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለን ብቻ በቃረምነው እውቀት መንዳት እንደማንችለው ማለት ነው!!

ፀሎት ራሣችንን ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ፊት ህያው መስዋዕት አድርገን የምናቀርብበትና ራሳችንን በማዋርድና ለስሙ በመገዛት ትህትናን የምንማርበት መሰዊያ ነው፤ ነገር ግን ያልተቋረጠ የፀሎት ህይወት መሆኑን እዚህ ጋር ልብ ይሏል!!

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።”ሮሜ 12፥1

ሁልግዜ በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት የመንበርከክ ልምድ ያለው ሰው አወቀም አላወቀም፣ ተረዳም አልተረዳም ባህሪው እንኳን ሳይቀር እየተቀረፀ ወደ ክርስቶስ ፍፁም ሙላት እያደገ መሄዱ እሙን ነው!!

ዕብራውያን 5
⁷ እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤
⁸ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤

በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት መቆየት የለመደ ሰው ትህትና፣ ቅንነት፣ ታዛዥነትና መገዛትን ስለሚለማመድ ራሱን ለማዋረድ አይቸገርም፤ Already መንበርከክ ተምሯልና......በፀሎት ያልተገራ ልብና መንበርከክ ያልለመደ ጉልበት ያለው ሰው ግን ሁልግዜ በሰዎች ፊትም በትህትናና በቅንነት መመላለስ ትልቅ መከራ ይሆንበታል!!

ለዚህም ነው እውነትኛ የፀሎት ሰዎች ትሁታን የሆኑት....በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ትሁት የለም የተባለለት ሙሴ እንኳን የፀሎት ህይወቱን ማየት ይቻላል....ስለዚህ በፀሎት በጌታ ፊት በመቆየት ያልተሠሩ ማንነቶቻችን እንዲሰሩ መፍቀድ አለብን....መንፈሳዊነት እንደ ሎሊፓፕ ጭንቅላታችንን ብቻ የምናሳድግበት ዝንባሌ ሳይሆን ከጌታ ጋር በመነካካት ጠረናችን በእርሱ አስደናቂ መዓዛ እስኪቀየር ድረስ ህልውናው ውስጥ ተውጥን የምንጠፋበት የህይወት ሥርዓት ነው!!

አቤት ግን በፀሎት ውስጥ የታጨቁት አስገራሚ ህይወት ለዋጭ ሚስጥሮች ብዛታቸው!!!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
778 viewsYonatan Worku, edited  07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 12:33:16 ነፃነታችሁን ጠብቁ!!

እስራኤላውያን ከግብፅ መራራ የባርነት አገዛዝ ጉበናቸው ላይ በቀቡት የበግ ደም ነፃ እንደወጡ እንዲሁ በቀራኒዮ መስቀል ላይ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የከፈለልንን መስዋዕት በልባችን አምነን በአፋችን የመሰከርን ሁላችን ከሰይጣን አገዛዝ ተላቅቀናል...ክብር ለታላቅ ስሙ ይሁን!!

“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”ቆላስይስ 1፥13-14

ምንም እንኳን እስራኤላውያን ከፈርዖን አገዛዝ በብርቱ የእግዚአብሔር እጅና የተዘረጋ ክንድ ተላቅቀው ከግብፅ ወጥተው በምድረበዳ ወደ ከነዓን መንገድ ቢጀምሩም የተጎናፀፉትን ነፃነት የሚፈታተንና የሚገዳደር ነገር ጋር መገጣጠማቸው ግን አልቀረም!!

ከባርነት ነፃ መውጣት አንድ ነገር ሆኖ ሳለ በነፃነት መቆየት ደግሞ ሌላ ነገር ነው.....እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከ430 አመታት በኃላ ከግብፅ ቢያወጣቸውም ግብፅ ግን ከውስጣቸው አልወጣም፤ በዚህም ምክንያት በየፌርማታው ወደ ግብፅ ካልተመለስን እያሉ በማጉረምረም በመቀጠላቸው ብዙዎቹ ምድረበዳ ቀርተዋል!!

“እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።”1ኛ ቆሮንቶስ 10፥5

ተወዳጆች ሆይ ከጨለማ አገዛዝ በኢየሱስ ደም ነፃ መውጣታችን ድንቅ ነገር ቢሆንም ነፃነታችንን መጠበቅና መንከባከብ ግን የሁልግዜ ሥራችን ሊሆን ይገባል!!

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”ገላትያ 5፥1

ዛሬ ነፃነታችንን የምናስጠብቅበትን አንዱን ቁልፍ ልናገር:-ያልተቋረጠ ፀሎት....ሳይቋረጡ የሚፀልዩ ሰዎች ነፃነታቸውን በፍፁም አያሠርቁም.....ያልኩት ግን ፀሎት አይደለም፤ ያልተቋረጠ ፀሎት.....በግዜውም አለግዜውም፣ በተወሰነ ስፍራ ብቻ ሳይሆን ባገኘነው ቦታና አጋጣሚ የምንፀልይ ከሆነ በክርስቶስ ያገኛነውን ነፃነት ማስጠበቅ እንችላለን!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/ZaphnathPaaneah1
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0
1.1K viewsYonatan Worku, edited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ