Get Mystery Box with random crypto!

Zaphnath-paaneah

የቴሌግራም ቻናል አርማ zaphnathpaaneah1 — Zaphnath-paaneah Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zaphnathpaaneah1 — Zaphnath-paaneah
የሰርጥ አድራሻ: @zaphnathpaaneah1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 648

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-05 23:48:54 ቀንበሩም ከውፍረት የተነሣ ይሰበራል!!

“በዚያም ቀን ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፤ ቀንበሩም ከውፍረት የተነሣ ይሰበራል።”
ኢሳይያስ 10፥27

ቀንበር ከአንገት ላይ እንደሚሰበር ለመረዳት ገጠር አካባቢ በባህላዊ መንገድ የሚያርሱትን የሃገራችንን ዕንቁ ገበሬዎች መመልከት ይበቃል.....ገበሬዎቹ ሞፈርና ቀንበር ተጠቅመው ብዙ ሄክታሮችን ያርሳሉ....በማረስ ላይ ሳሉ ግን ቀንበሩን የተሽከሙ አንዳንድ የደለቡና የፋነኑ በሬዎች በላያቸው ላይ ያለውን ቀንበር መስበር የተለመደ ክስተት ነው.....ከላይ የለጠፍኩትን ጥቅስ ሳስብ አሁን ያነሣሁላችሁ ጉዳይ ይመጣብኛል....በተመሳሳይ ሁኔታ የትኛውም በህይወታችን፣ በቤተሰባችን እንዲሁም በሃገራችን ዘመን ያስቆጠረና ያስጨነቀን ሰይጣን የጫነብን ቀንበር በኢየሱስ ስም ከአንገታችን ላይ ይሰበራል.....አዲሱ መደበኛ ትርጉምን ብትመለከቱት ከውፍረትህም የተነሣ ቀንበሩ ይሰበራል ብሎ ይናገራል.....ተወዳጆች ሆይ አብዛኛው በላያችን ላይ የተጫነና የሰነበተ ቀንበር ምክንያቱ በአጭሩ አለመወፈራችን ነው......እያንዳንዱ አማኝ በቅባትና በእግዚአብሔር ቃል ከታጠቀ አንዳች ቀንበር ሊሰለጥንበት አይችልም.....በጋለ ምጣድ ላይ ዝንብ አይቀመጥም እንዲሉ ዘወትር በመንፈስ ቅዱስ እሳት በሚቀጣጠሉ አማኞች ላይ ምንም አይነት በሽታ፣ እርግማን፣ ጨለማ አይቀመጥም፤ ይልቁንም ይሰባበራል እንጂ!.....ሃሌሉያ.....በኢየሱስ ስም በቅዱሱ ቅባት ማደግና መወፈር እንዲሁም በእግዚአብሔርም ቃል ሰይፍ መታጠቅ እና ዘመኑን መዋጀት ይሁንልን!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
970 viewsYonatan Worku, edited  20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 12:02:22 የእግዚአብሔር ቃል ባለስልጣን ነው!!

በሰማይም ሆነ በምድር የእግዚአብሔር ቃል የመጨረሻ ስልጣን ያለው እውነት ነው......ቃሉን ላከ ፈወሳቸው ተብሎ እንደተፃፈ የማያዳግምና ዘላለማዊ የመንፈስ፣ የነፍስ እንዲሁም የስጋ ፈውስ የአምላክ ቃል ውስጥ ብቻ ይገኛል.....ይህም የሆነበት ምክንያት የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሁሉን የሚችለው አምላክ እስትንፋስ ስላለና ንግግሩ ሁሉ አንዳች ውሸት የሌለበት እውነት ብቻ በመሆኑ ነው.....ስለ ቃሉ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን.....የእግዚአብሔር ቃል የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ፈጥሯል......በመንፈሳዊው አለም ላይ የእግዚአብሔር ቃል በሰይፍ ተመስሏል፤ በመሆኑም የትኛውንም የጨለማ ሥራ የማንኮታኮትና እንዳልነበረ የማድረግ ትልቅ አቅም አለው......ስለዚህ ዳግም የተወለደ ሰው ሁሉ መመስረት ያለበት በማያልፈው የመለኮት ቃል ላይ እንጂ በብልሀት የተፈጠረ የሰው ፍልስፍና ላይ አይደለም........ቃሉን ሰምቶ የሚያደርገው ሰው ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ሲመስል የማያደርገው ግን ቤቱን በአሽዋ ላይ እንደገነባ ሰነፍ ሰው ነው.....ዝናብና ጎርፍ በመጣ ግዜ የእያንዳንዱ መሠረት ይገለጣል....ከመቼውም ግዜ ይልቅ የእግዚረብሔር ቃል ለድርድር እየቀረበ ያለበት ግዜ ይመስለኛል.....አንድ የሚገባኝ እውነት ግን ከቃሉ ውጪ ክብርም ሆነ ፍፃሜ እንዲሁም ርስት የሚባል ነገር ከቶ አይታሰብም......የሰው ፍልስፍና ለግዜው እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭን ቢመስልም ውጤቱ ግን ውርደትን ማከናነብ ብቻ ነው......ምርኩዜ ሽምበቆ አይደለም እንዳለችው ዘማሪዋ ዛሬ ቆም ብለን የምንደገፍበትንና ራሳችንን የምንጥልበትን አስተማማኝ ዋስትና ያለውን ቅዱስ ቃል ከልባችን እንፈልግ....ከምንም አስቀድመን ዋናውን ጉዳይ ዋና ማድረግን አንዘንጋ.....ሃሌሉያ.....በነገራችን ላይ ለእኔ የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ባለውለታዬ ነው፤ መጥፎ ጠረኔን የቀየረ፣ ከአመድ ከትቢያ ላይ ያነሣኝ፣ ጨለማዬን የገፈፈልኝ፣ እራሴን እንድቀበል ያደረገኝ፣ ከሃጢያት ባርነትና ከሞት ፍርሃት ያዳነኝ፣ ከጨለማው ስልጣን የታደገኝ፣ ሰላምን እና እረፍትን ያጎናፀፈኝ እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለ አይገኝም......ከቃሉ ውጪ ያለ መድሃኒት ሁሉ ማስታገሻ ነው፤ ቃሉ ግን እውነተኛ መድሃኒት ነው.....ስለዚህ መፅሃፍ ቅዱሴን እወደዋለሁ፤ እንደሌላ ሰው አድርጎ የሚለውጥና ባዶነትን ሁሉ የሚሞላ እንደ እሱ ያለ ከቶ ማነው????.....ምናልባት አቧራ የጠገበ መፅሃፍ ቅዱስ ያላችሁ አንስታችሁ ማንበብ ጀምሩ፤ ህይወታችሁ ላይ የተጣበቀ አቧራ ይራገፍላችኃልና......በጌታ በኢየሱስ ስም የተዘጋ ምዕራፍ እንደገና በክብር ይጀምራል...እወዳችሃለሁ....ሻሎም

የህይወታችንን አቧራ የሚያራግፈውንና መደርደሪያ ላይ የተቀመጠውንና ነገር ግን አቧራ የጠገበውን መፅሃፍ ቅዱስ አውርደን እናንብበው!!

“ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።”ዕዝራ 7፥10

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.0K viewsYonatan Worku, edited  09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 09:26:57 በፊቴ ተመላለስ...

ዘፍጥረት 17
¹ አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤
² ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፥ እጅግም አበዛሃለሁ አለው።

አባታችን አብርሃም ከካራን ሲወጣ የሰባ አምስት አመት ሰው ነበር.....በሚወጣበትም ግዜ ዘርህን እንደ ምድር አሸዋና እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ የሚለውን ጨምሮ ሌሎች ወፋፍራም የተስፋ ቃሎችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብሏል.....ይሁን እንጂ ዕድሜው ዘጠና ዘጠኝ እስከሚሆን ድረስ ከመጠበቅ ውጪ በአይን የሚታይ አንዳች ጠብ እንኳን ያለ ምስክርነት አልነበረም.....ይህ ጉዳይ በእርግጥ እኔ ግን በአብርሃም ቦታ ብሆን ኖሮ እንዴት እሆን ነበር ብዬ ራሴን እንድጠይቅ ያደርገኛል.....የአህዛብ አባት እንደሚሆን ትንቢት የተነገረለት ሰው መቶ አመት እስኪሞላው ድረስ ቢያንስ እንዴት አንድ ልጅ አይኖረውም??......ዘፍጥረት ምዕራፍ አሥራ ሰባት ላይ(በ99 አመቱ) እግዚአብሔር ወደ አብርሃም መጥቶ እንዲህ አለው:- እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፣ በፊቴ ተመላለስ፣ ፍፁምም ሁን፣ ቃልኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ እና እጅግ አበዛሃለሁ........ምንም እንኳን አብርሃም ዕድሜው ገስግሶ ከተፈጥሮ ስርዓት የወጣ ቢመስልም እግዚአብሔር ግን ኤልሻዳይነቱን ደግሞ ደጋግሞ ያስታውሰዋል......ወዳጆቼ ሆይ ልክ እንደ አብርሃም ነገሬ ከባይሎጂ፣ ከኬሚስትሪ፣ ከታሪክ እንዲሁም ከተፈጥሮ ህግ ውጪ ወጣ እኮ ብላችሁ የምትጨነቁ ብትኖሩ የምስራች አለኝ:-"ኤልሻዳዩ ጌታ ኤልሻዳይነቱን ይገልጥላችኃል"....ሃሌሉያ......እግዚአብሔር ኤልሻዳይነቱን ለወዳጁ አብርሃም ከነገረው በኃላ በመቀጠል እንዲህ ይለዋል:- "በፊቴ ተመላለስ!"....በፊቴ ተመላለስ ማለት ሁልግዜ እግዚአብሔር እንደሚያይህ አውቀህ ተመላለስ፣ በንፅህናና በታማኝነት ተመላለስ፣ እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለስ፣ በትዕግስት ተመላለስ እና የመሳሰሉትን ሊወክል ይችላል....ይህንን ሳስብ የሰውን ፊት የምንፈራውን ያህል እንኳን እግዚአብሔርን ብንፈራው ወይም ደግሞ በካሜራ ዕይታ ውስጥ ነዎት የሚል ፅሁፍ ያለበት ቦታ ላይ በምንጠነቀቀው ልክ እንኳን በጌታ ፊት እንደዛ ብንጠነቀቅ የትና የት በደረስን ነበር ብዬ እላለሁ...... እግዚአብሔር እኮ አብርሃምን በፊቴ ተመላለስ ብሎ ሲለው አብርሃም በእያንዳንዷ ሽራፊ ሰከንድ በእግዚአብሔር ዕይታ ውስጥ መሆኑን ሊያስታውሰው ፈልጎ እንጂ ከፊቱ ርቆ እንደሚጠፋበት አይነት ዕርዳት እየጠየቀው አይደለም.....ውድ የጌታ ቤተሰቦች የምናመልከው አምላክ ኤልሻዳይ ስለሆነ በታማኝነት በፊቱ መመላለሳችንን እንቀጥል.....ዘመን እንኳን ያለፈ ቢመስል በእርግጥ እግዚአብሔር ከተናገራችሁ መፈፀሙ አይቀርምና በትዕግስት ጠብቁት.....ከተዓምራታችሁ ጋር ትገናኛላችሁ....ሻሎም

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.1K viewsYonatan Worku, edited  06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 09:35:45 የተባለልን እና መሬት ላይ ያለው እውነታ የተገላቢጦች ሲሆን...

መቼስ ይሄ ብዙዎቻችንን የሚመለከት ይመስለኛል......አንዳንዴ እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል እንዲሁም ቀጥታ ለራሳችን(በህልም ወይም በራዕይ) ከአዕምሮ በላይ የሆኑና ለማመን እንኳን የሚከብዱ የተስፋ ቃሎችን ይናገረንና የምናልፍበት መንገድ ግን ፈፅሞ የማይገናኝ(አራባና ቆቦ) ይሆንብናል.....በዚህም ምክንያት የሰማነውን ትንቢት ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን ወደ መጠራጠር እንገባለን.....ሌላ ግዜ ደግሞ እግዚአብሔርን ልጠብቀው ብለን ጉዞ እንጀምርና ነገርዬው እልህ አስጨራሽ ሲሆንብን አቋራጭ የመሰሉንን የህይወት መንገዶችን ለመሄድ እናማትራለን......እውነት ለመናገር 'መጠበቅ' የሚባለው እንደ ቃሉ ቀላል እኔም እስማማለሁ......መፅሃፍ ቅዱሳችንን ስንመረምር ግን እግዚአብሔር ትንቢትን ሲናገር አንድም ቀን ሁኔታችንን አይቶና ገምቶ አውርቶ አያውቅም፤ ይልቁንም ከሰው የዕውቀት ልክና የልምድ መጠን በላይ በዘመናት መካከል ሲናገርም ሆነ ሲያደርግ ይታያል.....በደንብ ላስተዋለው የእግዚአብሔር አሠራር በእርግጥም ይደንቃል፤ ከሰውም ይለያል......ሰው ሲናገር ደመናንና ዝናብን አይቶ፤ እግዚአብሔር ግን ራሱን ተማምኖ!....ሃሌሉያ......ቆይ ስንት ኃያላን የሆኑና ከፍተኛ የጦር ልምድ ያላቸው የእሰይ ልጆች እያሉ ብላቴናው ዳዊትን የእስራኤል ንጉሥ እንደሚሆን እግዚአብሔር በሳሙኤል በኩል መልዕክትን ሲያመጣለት አይገርምም፤ እርሱ ሰው እንዲያይ አያይም.......ዳዊት ያለፈበት መንገድ ግን አይደለም ለንጉሥ የሚገባ፤ ተራ ሰው እንኳን አይመኘውም....ዛሬ እነግራችኃለሁ ልክ እንደዳዊት ከእግዚአብሔር የሰማችሁትና እያለፋችሁበት ያለው መንገድ የማይገናኝ የመሰላችሁ ብትኖሩ የተናገረው የታመነ ስለሆነ በስፍራችሁ ላይ ሆናችሁ በትዕግስት ጠብቁት፤ በድንገት ይመጣላችህኃል....በመሠረቱ የትንቢት ቃሉና ኑሮአችሁ እንደዚህ መለያየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑን ያመላክታል፤ እርሱ እንደ አየሩ ፀባይ አይናገርምና.....ስለዚህ እንደ እንባቆም በመጠበቂያችን(ማማ) ሆነን እግዚአብሔርን እንጠብቀው፤ እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭንን ነገር ያደርግልናል.....አንድ ነገር አምናለሁ:-የተናገረው እግዚአብሔር ከሆነ ምንም አይነት ኃይል ከመፈፀም ሊያስቆመው አይቻለውም......በነገራችን ላይ ሰው በተፈጥሮ ውስጥ ሲሰራ እግዚአብሔር ግን ከተፈጥሮ በላይ ይሠራል፣ ሰው በግዜና በቦታ ክልል ውስጥ ሲሰራ እግዚአብሔር ግን ከግዜና ከቦታ ውጪ ይሰራል፣ ሰው በስጋዊ ጉልበትና ጥበብ ሲሰራ እግዚአብሔር ግን በመንፈሱ ይሰራል፤ የሌለውንም ወደ መኖር ያመጣል....እናታችን ሣራ በእርጅናዋ ወንድ ልጅን ለመታቀፍ የታደለችው እኮ የተስፋን ቃል የሰጠው አምላክ ከተፈጥሮ በላይ እንደሆነ በልብዋ ስላመነች ነው.....እናስ ካላችሁኝ.....የሰማችሁትና እያለፋችሁበት ያለው ተቃራኒ ከሆነ በእርግጥም የተናገራችሁ እግዚአብሔር መሆን አለበት፤ እርሱ በማንም የሚገመትን ትንቢት አይናገርምና.....ስለዚህ ታገሱት መጥቶ ያስደንቃችኃል....የምንጠብቅበት ፀጋ ይብዛልን!!

“....፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፥ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥12

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.1K viewsYonatan Worku, edited  06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 09:54:58 ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ ተፈትኗልና ይራራልናል!!

ዕብራውያን 4
¹⁵ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።
¹⁶ እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።

ቅዱሱ እግዚአብሔር እርሱ የርህራሄ አባት የመፅናናትም ሁሉ አምላክ እንደሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ይነግረናል.....በርህራሄና በምህረት ጌታን የሚመስለው የለም......ሁልግዜ ለቁጣ የዘገየ ለማዳን ግን የፈጠነ ነው......በዮሐ ወንጌል ምዕራፍ አሥራ አንድ ላይ ያለውን የአልዓዛርንና የቤተሰቦቹን ታሪክ እስቲ እናንሣ...ይህንን ክፍል ሳነብ እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን የልብ አዛኝነትና ርህራሄ በግልፅ ያሳየኛል.....የእነ ማርያምና ማርታ ወንድም የሆነው አልዓዛር ሞቶ ከተቀበረ በኃላ ኢየሱስ ግን በአራተኛው ቀን እነሱ ወደነበሩበት ብሎም አልዓዛር ወደ ተቀበረበት ቦታ ሲመጣ እንመለከታለን.....በጣም የሚያስገርመው ግን ኢየሱስ አልዓዛርን ከደቂቃዎች በኃላ ከሞት እንደሚያስነሣው ቢያውቅም ፍፁም በመንፈሱ አዝኖ ታወከ እንባውንም አፈሰሰ በማለት የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል.....የኔ ጥያቄ ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት እንደሚያስነሳው ካወቀ ለምን ማልቀስ አስፈለገው የሚል ነው.....ባጭሩ ይሄ እውነት እግዚአብሔር ምትሃታዊ አምላክ ሳይሆን የምናልፍበትን ሁሉ የሚረዳ የፍቅር አምላክ እንደሆነ ያስረዳናል.....ኢየሱስ ፍፁም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፍፁም ሰውም በመሆኑ ስሜቶቻችንን በቀላሉ ይረዳልናል.....በዚህም ምክንያት በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል መሆን የተገባው መካከለኛ(ሊቀካህናት) ሆኗል.....ከሃጢያት በቀር በነገር ሁሉ እንደኛ ስለተፈተነ ደግሞ ይራራልናል(ያስብልናል)......ምናልባት ስላሳለፋችሁት ህይወት ኩነኔ(condemnation)/ፀፀት የሚሰማችሁ ሰዎች ብትኖሩ የምስራች አለኝ:- 'ኢየሱስ ይወዳችኃል፤ ደግሞም ይራራላችኃል....ለእናንተም እጅግ ትልቅና የከበረ አላማ አለው......በቀንና በሌሊት እየመጣ የሚከሳችሁን ክፉው ዲያቢሎስን አትስሙት.....እግዚአብሔር የማንንም ጥፋት(የኃጢያተኞችን ጨምሮ) አይወድም ይልቁንም የተጣለ ሰው ከወደቀበት ተነሥቶ በህይወት ይኖር ዘንድ በምክሩ ዘወትር ያስባል....እሱ ብቻ አይደለም፤የኢየሱስ ደም ደግሞ ከሃጢያት ሁሉ ያነፃል.....ሃሌሉያ"....እስቲ ከሣሻችን ሰይጣን እየሰማ:-"እግዚአብሔር ይወደኛል፣ ያስብልኛል ደግሞም ይራራልኛል" ብላችሁ ፃፉ....ሻሎም

“..፤ እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድድም፥ ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል።”2ኛ ሳሙኤል 14፥14

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.2K viewsYonatan Worku, edited  06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 07:51:52 “የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።”
መዝሙር 16፥11


@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
129 viewsYonatan Worku, edited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 22:32:25 መልካም መልካሞቹ ከወደኃላ የሚሆኑትስ ነገር!!

መፅሃፍ ቅዱሴን ሳጠና አንድ ያስተዋልኩት ጉዳይ ቢኖር መልካምና የተሻለ የተባሉ ነገሮች ዘግየት ብለው የሚመጡት ነገር ነው.....በስንፍናችን ወይም ባለመፀለያችን ምክንያት የዘገዩትን ግን አለማለቴ ይታወቅልኝ፤ እንደዚህ አይነቱንና በጠላት ውግያ ምክንያት የተፈጠሩትን መስተጓጎሎችማ ገስፆ ከማባረር ውጪ ምንም አማራጭ የለም.....በተረፈ ግን አንዳንድ ምሳሌዎችን ለማየት እንሞክር:- በዮሐ ወንጌል ምዕራፍ 2 ላይ ያለውንና ቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ የተከሰተውን አስገራሚ ታሪክ ብንመለከት ደጋሾቹ ለብዙ አመታት ያዘጋጁት የወይን ጠጅ ሲያልቅባቸው ኢየሱስ ግን በተዓምራት ማለፊያ የሆነ ወይን ጠጅ ሰርቶ አስደነቃቸው፤ አሳዳሪውም እንዴት መልካሙን እስካሁን አቆያችሁ ብሎ ሲሞግታቸው እናያለን.....1ኛ ሳሙኤል ላይ ያለውን የሃናንና የፍናናንም ታሪክ ብንመለከት ይህንኑ ይመሰክርልናል...ለተከታታይ አመታት ልጆችን ስትወልድ የቆየችው ፍናና ብትሆንም የተለየ የእግዚአብሔር ፕሮግራም የነበረበት ሳሙኤል ግን የመጣው ዘግይቶ ነበር.....ንጉስ ዳዊትም የአባቱን የእሰይን በጎች እየጠበቀ ያደገ እረኛና የቤቱ የመጨረሻ ልጅ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን የእስራኤል ንጉስ እንዲሆን መረጠው፤ ቀባውም.....በመጀመሪያው አዳም ምክንያት ሰዎች ሁሉ ኃጢያተኞች ሆኑ በሁለተኛው አዳም ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ ግን ሰዎች ህያው የሚሆኑበት መንገድ ተዘጋጀ.....መድሃኒአለም መልካም መልካሙን ግን ከወደኃላ የሚያደርገው ለምንድነው???.....ይሄ ብቻ አይደለም ከመጀመሪያው ቤት ክብር ይልቅ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣልም እኮ ተበሏል....ዛሬ መልዕክት አለኝ:-ነገሬ ዘግይቶብኛል የምትሉ ሰዎች ካላችሁ የተሻለ ክብር ስላለ እንደሆነ ልነግራሁ እወዳለሁ....ጌታ ጉዳያችሁን እረስቶት ሳይሆን እያሰማመረው እንደሆነ እውቁ፤ ደግሞም በቅርቡ በክብር ይገለጣል....እወዳችኃለሁ..ሻሎም

“ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።”
ዮሐንስ 2፥10

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.4K viewsYonatan Worku, edited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 13:19:55 ብረት በብረት እንደሚሣል ሰው በባልንጀራው ይሣላል!!

“ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።”ምሳሌ 27፥17

የደነዘዘና በአግባቡ መቁረጥ የተሣነው ቢላዋ በሌላ ብረት(ሞረድ) እንደሚሣልና እንደገና ለሌላ አገልግሎት እንደሚዘጋጅ እንዲሁ ሰውም ውስጡ ያለው ታለንት በኃይል እንዲገለጥ በሌላ ሰው መሣል አማራጭ የለውም......መፅሃፍ ቅዱሳችን ብረት የሚሣለው በሌላ ብረት እንጂ በእንጨት ወይም በሌላ ነገር እንዳልሆነ መናገሩ ያስገርማል.....በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጣችን ያለውን የሚመስል መክሊት ያለው ሰው ጋር በመሆን አንዱ አንዱን በኃይል እንዲሥል ማድረግ ይቻላል.....ለምሳሌ ቢዝነስ መሥራት የሚፈልግ ሰው መሄድ ያለበት ከዚህ በፊት በቢዝነሱ አለም ብዙ ልምድና ዕውቀት ያዳበረ ሰው ጋር እንጂ ፓለቲከኛ ጋር አይደለም፣ ፓለቲከኛ የመሆን ጥልቅ ፍላጎት ያለው ሰውም መከተልም ሆነ ማንበብ ያለበት የፓለቲካውን አለም በተሻለ ሁኔታ ሊያስረዳውና ወደ ህልሙ ሊገፋው ከቻለ ብቻ ነው፣ በህክምና ወስጥም በማገልገል ሰዎችን ለመርዳት ፅኑ መሻት ያለው ሰውም ቢሆን አንድ ኢንጂነርን ቢከተል ጥቅም የለውም ምክንያቱም ብረት ብረትን ይስለዋል እንጂ ብረት እንጨትን አይስለውምና.......የጌታ እናት ብፅዕት ማሪያም ኢየሱስን በፀነሰችው ግዜ ቶሎ ብላ የሄደችው ከእርሷ በፊት በመፀነስ የምትቀድማት ዘመድዋ ኤልሳቤጥ ጋር የሆነበት ምክንያትም ከዚሁ እውነት ጋር ይያያዛል.....ጌታን የማገልገል ጥሪ የወደቀበትም ሰው አብዛኛው ግዜውን ማጥፋት ያለበት በእውነትና በታማኝነት እንዲሁም በቅንነት ከሚያገለግሉ ሰዎች ጋር ነው....ዛሬ ሁላችሁንም መጠየቅ የምፈልገው ውስጣችሁ ያለው አይነት ነገር ያለበት ሰው በዙሪያችን ማን አለ???.....ጩኽታችንን የሚጮሁ፣ ህመማችንን የሚታመሙ፣ ፅንሳችንን የፀነሱ፣ ረሃባችን የሚርባቸው፣ ፀሎታችንን የሚፀልዩና ሸክማችንን የሚሽከሙ ሰዎች እውነተኛ ወዳጆቻችን ናቸውና ቸል አንበላቸው.....በሚገባ ተሥለንና ተቀርፀን ማብረቅረቅ የሚሆንልን አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ሆነ ብለን መምረጥ ስንችል ብቻ ነው፤ አሊያ ግን በግብታዊነት(በመሰለኝና በደሳለኝ) ይመረጥልናል.....ከአህያ የዋለች ጊደር ምናምን የሚባለውም ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም....ጉዳዩ ቀላል ቢመስልም እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ግን በደንብ እገነዘባለሁ...ጌታ ማስተዋል ይስጠን!!

who is your friend??

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.4K viewsYonatan Worku, edited  10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 11:02:26 እንዴት እናስታርቃቸው??!!

በብሉይ ኪዳን የነበረው የቃልኪዳኑ ታቦት በአሁኑ ግዜ ስለሚገኝበት ቦታና ስላለበት ሁኔታ በተመለከተ መፅሃፍ ቅዱስ እና ክብረ ነገሥት የተባሉት ሁለት መፅሃፍት የተለያየ መረጃ ያቀርባሉ:-

መፅሃፍ ቅዱስ:-

2 ዜና 35
¹ ኢዮስያስም ለእግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ፋሲካ አደረገ፤ በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አረዱ።
² ካህናቱንም በየሥርዓታቸውም አቆመ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ አጸናቸው።
³ እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ፤

ክብረ ነገስት

ምንጭ፤ ‹‹ክብረ ነገሥት ከገጽ ፳፩-፶፭›› ተርጓሚ ሥርግው ገላው በ፲፱፺፬ ዓ.ም. የታተመ

ንጉስ ኢዮስያስ(648-609ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረ የይሁዳ ንጉስ) ሲሆን በእርሱ ዘመን ታቦቱ በእስራኤል እንደነበር ከላይ በለጠፍኩላችሁ የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ማየት ይቻላል....ክብረ ነገስት ደግሞ ታቦቱ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት(970-931ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረ የእስራኤል ንጉስ) ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ ይናገራል...በመካከላቸው ደግሞ ወደ 300 አመት የሚጠጉ የአመታት ልዮነቶች አሉ!!

እናስ ታድያ ትክክለኛው የቱ ነው
መፅሃፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የቃልኪዳኑ ታቦት በኢዮስያስ ዘመን እስራኤል ውስጥ ከተገኘ ከ300 ምናምን አመት በፊት ማለትም በሰሎሞን ዘመን ኢትዮጵያ መጥቷል የሚባለውን ትርክት አያፈርሰውም ወይስ ተመልሶ ወደ እስራኤል ሄዶ ይሆን እስራኤላውያንስ እንደ ዐይን ብሌን የሚያዩት የቃል ኪዳኑ ታቦት ሲወሰድባቸው እንዴት ዝም አሉ

“በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።”
ኤርምያስ 3፥16

የእግዚአብሔር ቃል ግን ባለስልጣን ነው!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.5K viewsYonatan Worku, edited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 08:32:02 L_Y_R_I_C_S

ሳይነጋ ለሊቱ ሳትቀድመኝ ጀምበር
መጥቻለሁ ፊትህ ለሊት ላልከኝ ጉዳይ
አንተን ባየ አይኔ ይስሃቄን አይቼ ንቄዋለሁ
ሳላንገራግር ሣራን ሳላማክር እሰዋዋለሁ/2×

ይሁና የኔ ሳቅ ለሱ
ይሁና ደስታዬ ለሱ
ይበሉኝ ባዶ የቀረ
ይበሉኝ የተሞኘ/2×

ቀሎብኝ አይደለም ረብ ቢሆነኝ ለኔ
ጠብቄ ያገኘሁት የሚሳሳለት አይኔ
እሱን አየሁና ትምክህቴን በሙሉ ንቄዋለሁ
ድጋሚ ሳላስብ ግራ ቀኝ ሳላይ እሰጠዋለሁ/2×

ሞኝ ነህ ይበሉኝ
ያለህን ይበሉኝ
መካሪ አጣህ ይበሉኝ
ተሳሳትህ ይበሉኝ/2×
እሱን ካከበረ ከተቀበለልኝ ምን እሻለሁ
ካለኝ ብቻ ሳይሆን ራሴን ጨምሬ እሰጠዋለሁ/2×

ይሁና የኔ ሳቅ ለሱ
ይሁና ደስታዬ ለሱ
ይበሉኝ ባዶ የቀረ
ይበሉኝ የተሞኘ/2×

ካረካህ አንተን ደስ ካሰኘህ
ሰዋልኝ ያልከኝ ደስታ የሚሆንህ
አንድ ለሊት አይደር
አንድ ለሊት አይዋል
ሰዋልኝ ያልከው
በእኔ ቤት አያድር/2×

በረከት ለማ[አንተን ባየ አይኔ]
(እጅግ የሚያረሰርስና ለጌታ የሚያስጨክን ድንቅ ዝማሬ)

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.6K viewsYonatan Worku, edited  05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ