Get Mystery Box with random crypto!

ብረት በብረት እንደሚሣል ሰው በባልንጀራው ይሣላል!! “ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራ | Zaphnath-paaneah

ብረት በብረት እንደሚሣል ሰው በባልንጀራው ይሣላል!!

“ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል።”ምሳሌ 27፥17

የደነዘዘና በአግባቡ መቁረጥ የተሣነው ቢላዋ በሌላ ብረት(ሞረድ) እንደሚሣልና እንደገና ለሌላ አገልግሎት እንደሚዘጋጅ እንዲሁ ሰውም ውስጡ ያለው ታለንት በኃይል እንዲገለጥ በሌላ ሰው መሣል አማራጭ የለውም......መፅሃፍ ቅዱሳችን ብረት የሚሣለው በሌላ ብረት እንጂ በእንጨት ወይም በሌላ ነገር እንዳልሆነ መናገሩ ያስገርማል.....በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጣችን ያለውን የሚመስል መክሊት ያለው ሰው ጋር በመሆን አንዱ አንዱን በኃይል እንዲሥል ማድረግ ይቻላል.....ለምሳሌ ቢዝነስ መሥራት የሚፈልግ ሰው መሄድ ያለበት ከዚህ በፊት በቢዝነሱ አለም ብዙ ልምድና ዕውቀት ያዳበረ ሰው ጋር እንጂ ፓለቲከኛ ጋር አይደለም፣ ፓለቲከኛ የመሆን ጥልቅ ፍላጎት ያለው ሰውም መከተልም ሆነ ማንበብ ያለበት የፓለቲካውን አለም በተሻለ ሁኔታ ሊያስረዳውና ወደ ህልሙ ሊገፋው ከቻለ ብቻ ነው፣ በህክምና ወስጥም በማገልገል ሰዎችን ለመርዳት ፅኑ መሻት ያለው ሰውም ቢሆን አንድ ኢንጂነርን ቢከተል ጥቅም የለውም ምክንያቱም ብረት ብረትን ይስለዋል እንጂ ብረት እንጨትን አይስለውምና.......የጌታ እናት ብፅዕት ማሪያም ኢየሱስን በፀነሰችው ግዜ ቶሎ ብላ የሄደችው ከእርሷ በፊት በመፀነስ የምትቀድማት ዘመድዋ ኤልሳቤጥ ጋር የሆነበት ምክንያትም ከዚሁ እውነት ጋር ይያያዛል.....ጌታን የማገልገል ጥሪ የወደቀበትም ሰው አብዛኛው ግዜውን ማጥፋት ያለበት በእውነትና በታማኝነት እንዲሁም በቅንነት ከሚያገለግሉ ሰዎች ጋር ነው....ዛሬ ሁላችሁንም መጠየቅ የምፈልገው ውስጣችሁ ያለው አይነት ነገር ያለበት ሰው በዙሪያችን ማን አለ???.....ጩኽታችንን የሚጮሁ፣ ህመማችንን የሚታመሙ፣ ፅንሳችንን የፀነሱ፣ ረሃባችን የሚርባቸው፣ ፀሎታችንን የሚፀልዩና ሸክማችንን የሚሽከሙ ሰዎች እውነተኛ ወዳጆቻችን ናቸውና ቸል አንበላቸው.....በሚገባ ተሥለንና ተቀርፀን ማብረቅረቅ የሚሆንልን አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ሆነ ብለን መምረጥ ስንችል ብቻ ነው፤ አሊያ ግን በግብታዊነት(በመሰለኝና በደሳለኝ) ይመረጥልናል.....ከአህያ የዋለች ጊደር ምናምን የሚባለውም ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም....ጉዳዩ ቀላል ቢመስልም እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ግን በደንብ እገነዘባለሁ...ጌታ ማስተዋል ይስጠን!!

who is your friend??

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ