2023-03-11 15:34:45
ከአደገኛ የአድመኝነት መንፈስ ጋር አንተባበር!!
የመፅሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት አድመኝነትን እንደዚህ ይፈታዋል:-
አድመኝነት=ጠብን፣ ክርክርን፣ መለያየትን መፍጠር ይህም በዓመፅ፣ በትግል፣ ባለመስማማት፣ በመከፋፈል፣ በውድድር ይገለጣል......እንግሊዘኛው ደግሞ 'strife' ይለዋል.
Strife=bitter sometimes violent conflict or dissension,
an act of contention(fight,struggle) for superiority,
division, conflict,,,,,,etc
አድመኝነት አንድ ትልቅ ስብስብን ለማፍረስ ከስብስቡ ውስጥ በእንቢተኝነትና በትዕቢት ብሎ በእኔ አውቃለሁነት በወጡ ሰዎች አማካኝነት ይከናወናል.....ምናልባት በእውነት ሆነ በሐሰት መረጃ ላይ ተመስርቶ የሚደረግ ሊሆን ቢችልም የመነሻ ሃሳቡ(ሞቲቭ) ግን ጠማማ ነው......በነገራችን ላይ ይሄ ጉዳይ በእኛ ሃገር ላይ በእጅጉ ይስተዋላል(በሃገር፣ በቤ/ክን እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች)
መፅሃፍ ቅዱስ አድመኝነት(ማደም) የሥጋዊነት መገለጫ እንደሆነ ያስተምረናል:-
“ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥”ገላትያ 5፥20
“ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።”ያዕቆብ 3፥16
“ስመጣ፥ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፤ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፤”2ኛ ቆሮ 12፥20
የእግዚአብሔር ቃል መሪዎችንና ባለስልጣናትን በምን አይነት አግባብ መቅረብና ማናገር ስህተቶችም ቢኖሩ ማሳወቅ እንዳለብን እየነገረን በስጋዊነት ተነስተን ማበሻቀጥና ማዋረድ ምን ያህል ከመንፈሳዊነት እየራቅን እንደሆነ ያመላክታል.......ለስልጣን ስርዓት መገዛት(submission) መንፈሳዊነት ነው፤ መሪዎችን የሚሾም እግዚአብሔር ነውና.....በነገራችን ላይ ጳውሎስ ለመሪዎች ስለመገዛት ሲሰብክ የነበረው ክፉና ጨካኝ በነበረው ንጉስ ቄሣር ዘመን መሆኑ ያስደንቃል.....ለምንድነው ግን በዘመናችን ብዙ ሰው በአድመኝነት መንፈስ ተሞልቶ ለመሪዎች መገዛት የተሣነው???.....ይልቁንም የራሱን ትንንሽ መንግስት ለመመስረት ደፋ ቀና የሚለው???.....እንዴትስ ሁላችንም የአንድ ሃገር ወይም ቤ/ክን ወይም ተቋም መሪ ልንሆን እንችላለን???....ምናልባት እረፍትና ሰላም ያጣነው መገዛትን እንደ መሽነፍ አድርገን ስለምንቆጥረው ይሆን??? በዘመናችን ፀጥ እና ዝግ ብለን እንድንኖር ከተፈለገ ከአድመኝነት መንፈስ በመላቀቅ እግዚአብሔር ለመሪዎቻችን በአግባቡ መስራት የሚችሉበትን ጥበብ እንዲሰጣቸው መፀለይ ይጠበቅብናል....ፀጋ ይብዛልን!!
“እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1-2
@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
704 viewsYonatan Worku, edited 12:34