2023-01-22 01:42:57
ከአንድ ሰው የመጣ ጥያቄ..
ጥያቄ..."ከፅድቅ አኳያ ያዕቆብ 2:21ን እንዴት ትመለከተዋከህ???..ሰው የሚፀድቀው በእምነት ነው ወይስ በሥራ???
መልስ...በመጀመሪያ ስለ ጥያቄው አመሰግናለሁ!....ጥያቄውን ለመመለስ እንዲረዳን ያዕ 2:21ን ልለጥፈው:-
“አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?”ያዕቆብ 2፥21
ቀጥታ ጥቅሱ ስናነበው እውነትም ሰው በሥራ ይፀድቃል የሚል አንድምታ ያለው ይመስላል....አዎን በሥራ ይፀድቃል ብለን ካልን ደግሞ ጳውሎስ ኤፌ 2:8-9 ከተናገረው ጋርና ከሌሎች ጥቅሶች ጋር ይላተምብናል ይህም መፅሃፍ ቅዱስን እርስ በእርሱ የሚጋጭ እንደሆነ ያስመስለዋል.....ኤፌሶን ላይ ያለውን አንዴ ልለጥፈው:-
ኤፌሶን 2
⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
ሆኖም ግን ዶክትሪን አንድ ጥቅስ ላይ በፍፁም አይመሰረትምና አውዳዊ ፍቺውን ለመረዳት መሞከር ይገባል.....በተለይ ከቁ14-26 ያለውን ብናነበው ምዕራፉ እያወራ ያለውን ጉዳይ ለማስተዋል አያዳግተንም(ረዘም ስለሚል እኔ እዚህ ሙሉውን አልለጥፈውም እናንተ አንብቡት).....አስቀድመን ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ምዕራፉ እያብራራ ያለው እምነት አለኝ ስለሚል ነገር ግን ሥራ ላይ ወፍ ስለሆነ ሰው ወይም ደግሞ እምነትና ሥራ ስላላቸው ቁርኝት እንጂ የሚፀደቀው በእምነት ነው ወይስ በሥራ ስለሚሉት ሁለት የክርክር ነጥቦች/የሙግት ሃሳቦች አይደለም......በመሠረቱ እምነትንና ሥራን መለያየት መንፈሳዊውን እውነት በቅጡ ካለማወቅ ይመነጫል.....ይሁንና ግን ሥራን የሚያመጣው እምነታችን እንጂ ሥራችን እምነታችንን በፍፁም አይቀድመውም......ዮሐ ወንጌል ምዕ 15ትን ብንመለከት ሃሳባችንን የተሻለ ያብራራልናል.....እስቲ ቆይ የወይን ግንዱ ላይ የተተከለችው ቅርንጫፍ የፍሬአማነቷ ምስጢር ምንድነው?? ...ቅርንጫፏ ፍሬ ማፍራት የምትችለው ከግንዱ ጋር ካላት አግባብነት ያለው ቁርኝት የተነሣ እንጂ ያለግንዱ ፍሬ ማፍራት በፍፁም አይታሰብም በተመሳሳይ መንገድ ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም ብሎ እንዳለ ጌታ እኛም በእርሱ ላይ በእምነት ሳንተከል የምንሠራው ሥራ ሁሉ ከንቱና የከንቱ ከንቱ ንፋስንም እንደመከተል ይሆንብናል......በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል ሥራችን በልባችን የምናመነውን እምነት እውነተኝነት/አስመሳይነት ይገልጣል ወይም ደግሞ የተተከልንበትን አለም ፍንትው አድርጎ የተቀዳንበትን ምንጭ ጮክ ብሎ ያወራል......ስለዚህ ማንም ሰው ክርስቶስ ላይ በእምነት ከተተከለ መልካምን ፍሬ ማፍራቱ/መልካም ሥራን መስራቱ ሳይታለም የተፈታና የማይታገልበት ተፈጥሮው ይሆናል......ሃሌሉያ......ስለዚህ ልክ ቅርንጫፍ ፍሬን ለማፍራት መጨነቅ ሳይሆን በግንዱ ላይ መተከል እንዳለባት እንዲሁ እያንዳንዱን አማኝ ሊያሳስበው የሚገባው በክርስቶስ ላይ በእምነት ስለመተከሉ ጉዳይ ሲሆን ከላይ እንዳነሣሁት መልካም ሥራ የሚባለው ተያይዞና ቀጥሎ መምጣቱ አይቀርም.....በሥራ ግን ተጀምሮ ለዘላለም ወደ እምነት መድረስ አይቻልም....ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የተናገረውን እስቲ እንመልከት:-
“የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።”ገላትያ 2፥21
ስለዚህ የክፍሉን ዐውድ መረዳት ከስህተት ይታደገናል....እምነትና ሥራ በተመለከተ በነዚህ ነጥቦች የምዕራፉን ሃይለ ቃል ለማስቀመጥ ልሞክር:-
አንድ እምነት እውነት ወይም ውሸት መሆኑ በሥራው ይገለጣል
እምነት የሥራ ምንጭ ሲሆን ሥራ ደግሞ የእምነት መገለጫው
እምነት ሥራን ሲቀድም ሥራ ደግሞ እምነትን ይከተላል
ሙሉ የመፅሃፍ ቅዱስን ዐውድ ስንመለከት ማንም ቢሆን የሚፀድቀው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሠርቶ የጨረሰውን ሥራ በእምነት በመቀበል እንጂ ሥራን በመሥራት አይደለም!!
ሌሎቻችሁም ጨምሩበት!!
@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.4K viewsYonatan Worku, edited 22:42