2023-02-08 13:10:03
የነቃ ያነቃል፥ ያልነቃ ያንቃል፤
ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደደረሰ ዘመኑን እወቁ!!
“ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።”ሮሜ 13፥11
መፅሃፍ ቅዱሳችን ዘመኑን ስለማወቅ በተደጋጋሚ ይናገራል.....ለምሳሌ ዘመኑን የሚያውቁ የተባለላቸውን የይሳኮርን ልጆች መመልከት ይቻላል:-
“እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።”1 ዜና 12፥32
እነዚህ የይሳኮር ልጆች ጥበበኞች ስለነበሩ ዘመኑን በሚገባ ተረድተዋል.....በዚህም ምክንያት እስራኤላውያን በዛ ዘመን ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያስተምሩ ነበር....ዘመንን የሚያውቁ ብቻ በዘመኑ ውስጥ የታጨቀውን የእግዚአብሔር በረከትና ዕድል እንዲሁም ክብር ጋር መገናኘት ይችላሉ...
ዘመናችን በስኬትና በአሸናፊነትና የታጀበ እንዲሆን ካስፈለገ ዘመኑን በሚገባ መመርመርና ማወቅ አማራጭ የለውም......በርዕሱ ላይ እንደለጠፍኩላችሁ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በአፅንዖት የሚፅፍላቸው ከእንቅልፋቸው የሚነሱበት ሰዓት አሁን እንደሆነና መንቃት እንዳለባቸው ነው.....
ወዳጆቼ ሆይ እንቅልፍ ሲባል እኮ የግድ ዐይን ተጨፍኖ የሚተኛበትን አለም ለማመልከት አይደለም ይልቁንም በክፍሉ ላይ እያወራ ያለው በአዚምና በድንዛዜ ውስጥ ተሸብበው ስለሚንከላወሱት ሰዎች እንጂ......
በምድራችን ላይ እየሆኑ ያሉትን አብዛኛውን ጉዳዮች ብንመለከት ዘመኑ በግልጥ የመጨረሻ መጨረሻ መሆኑን ያመላክታል....ጦርነቱ፣ የመሬት መንቀጥቀጡ፣ ጉስቁልናው፣ አመፁ፣ ፍትጊያው፣ በሽታው ሁሉ ጌታችን ሊመጣ በደጅ እንደሆነ ይመሰክሩልናል....
ስለዚህ ከመንቃትና ከማንቃት ውጪ አማራጭ የለንም....ዘይታችን አልቆ ሙሽራው በድንገት እንዳይመጣብን በፅድቅ ልንነቃና ልንቆም ይገባናል......ለመንቃት ሰዓቱ አሁን ሲሆን ነገን የሚያውቅ ደግሞ አንድዬ ብቻ ነው......
በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ የእንቅልፍና የስካር፣ የአዚምና የድንዛዜ መንፈስ ዕብቅ በንፋስ እንደሚጠረግ ከምድሪራችን ላይ የተጠረገ ይሁን...አሜን!!
“ስለዚህ፦ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል።”ኤፌሶን 5፥14
@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
794 viewsYonatan Worku, edited 10:10