2022-07-05 16:00:26
ፃድቅ እንደ ዘንባባ..
ክፍል-3
ስለ ዘንባባ ዛፍ በአራተኛ ደረጃ ልናውቀው የሚገባን እውነት ሁልግዜ አረንጓዴና የለመለመ(evergreen) መሆኑን ይመለከታል...ሁልግዜ የለመለመ ሆኖ ስለመኖር ሳስብ ደግሞ ቶሎ ወደ አዕምሮዬ የሚመጣልኝ በአለማችን ላይ በትልቅነቱ ወደር የማይገኝለት አማዞን ሬይን ፎረስት(amazon rainforest) ሲሆን መገኛውም በዋነኝነት በደቡብ አሜሪካ አህጉር ላይ ነው....የዚህ ጥቅጥቅ ጫካ ከአመት አመት እንደዚህ አረንጓዴ(evergreen) የመሆን ምስጢር ምን እንደሆነ ለማወቅ ሳጠና ያገኘሁት ነገር ቢኖር አማዞን የሚባል ወንዝ(amazon river) በጫካው ውስጥ ለውስጥ ሳይቋረጥ የሚፈስ ወንዝ መኖሩን ነው.....የፃድቅ ህይወትም ልክ እንደዚሁ በወቅቶች መፈራረቅ ሳይረባበሽ በውስጡ ካለው ድንቅ የእግዚአብሔር መንፈስ የተነሣ በልምላሜና በፍሬአማነት ይታወቃል....መቼም ቢሆን መርሳት የሌለብን እውነት ፃድቅ ከውጪ ወደ ውስጥ ሳይሆን ከውስጥ ወደ ውጪ አምላኩን በመስማት የሚኖር ብሩክ ሰው መሆኑን ነው....የፃድቃን በረከታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሆነ በበጋም ሆነ በክረምት በበልግም ሆነ በፀደይ ጠጋ ብንላቸው የሚበላ ነገር አይታጣባቸውም....ሃሌሉያ....ለአማዞን ጫካ ውበት እና ግርማ ምክንያት አማዞን ወንዝ እንደሆነው ሁሉ ፃድቅም ዕለት ዕለት የሚመገበው የአምላኩ ቃል ሁልግዜ ህይወት ያለውና ደስተኛ ሆኖ እንዲኖር ያደርገዋል....በውሃ ፈሳሽ ዳር እንደተተከለች ፍሬዋንም በየጊዜዋ እንደምትሰጥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል ተብሎ እንደተፃፈ እንዲሁ ፃድቅም በህይወቱ ላይ በረከትና ስኬት እንጂ ሞትና ጭንገፋ ወይም እርግማንና ጥፋት ፈፅሞ በህይወቱ ላይ አይሆንም....ስለዚህ ፃድቅ ሰው ልክ እንደ ዘንባባ ዛፍ በየትኛውም ግዜ፣ ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ላይ ብናገኘው ጠውልጎና ደርቆ ሳይሆን አምሮበትና ደምቆ እንዲሁም ለምልሞና በዝቶ ብቻ ነው...ሃሌሉያ...አሜን።።።።
ኤርምያስ 17
⁷ በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።
⁸ በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።
ይቀጥላል...
@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
1.2K viewsYonatan Worku, edited 13:00