2023-01-09 13:50:42
Merry christmas
ድንቅ ስጦታ
ኢየሱስ ሲወለድ ሄሮድስ ደነገጠ፤ ለአለም ግን ታላቅ ደስታ ሆነ!
ኢየሱስ ለምን ተወለደ:-
የትኛውም ሰው ሲወለድ አላማው ለመኖር ሲሆን ኢየሱስ የተወለደው ግን በዋነኝነት ለመሞት(መሰዋዕት ለመሆን) ነው.... ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢየሱስ በስጋ የተገለጠበትን 3ት ዋነኛ ምክንያቶችን እናንሣ !!
1. የሰይጣንን ራስ ለመቀጥቀጥ!
“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”
ዘፍጥረት 3፥15
“ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።”1ኛ ዮሐንስ 3፥9
ራስ(head) ብሎ ሲል:-
- ጥበብና ዕውቀት
- ስልጣን
- ሃሳብ
2. አለምን ሁሉ ከኃጢያትና ከሃጢያት እርግማን ለማዳን!
ማቴዎስ 1
¹⁸ የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
¹⁹ እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።
²⁰ እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
²¹ ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።
በአለም ላይ ያለ የትኛውም መድሃኒት የሚያገለግለው ለአንድ በሽታ ነው፤ የኢየሱስ መድሃኒትነት ግን ለሁሉም በሽታ ፈውስ መሆን ይችላል።
የትኛውም መድሃኒት ኤክስፓየሪ ዴት አለው(shelf life)፤ የኢየሱስ መድሃኒትነት ግን ያለግዜ እና ቦታ ገደብ ያድናል።
3.የምድር አህዛብ ሁሉ በእርሱ እንዲባረኩ!
ዘፍጥረት 22
¹⁵ የእግዚአብሔር መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥
¹⁶ እንዲህም አለው፦ እግዚአብሔር፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና
¹⁷ በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤
¹⁸ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።
“ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ። " ገላትያ 3፥16
@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
982 viewsYonatan Worku, 10:50