Get Mystery Box with random crypto!

የበግ ለምድ የለበሰ አውሬ!! (እውነት ውሸት እላችኃለሁ) አውሬነቱ እንዳይታወቅበት የበግ ለምድ | Zaphnath-paaneah

የበግ ለምድ የለበሰ አውሬ!!
(እውነት ውሸት እላችኃለሁ)

አውሬነቱ እንዳይታወቅበት የበግ ለምድ በመልበስ የሚታወቀው ጠላታችን ዲያቢሎስ መሆኑን ጠንቅቀን መረዳት አለብን!!

ነፍሰ በላው ዲያቢሎስ ወደ ሰዎች ህይወት ሲመጣ በአውሬነቱ(በጨካኝነቱ) ሳይሆን አውሬነቱ ላይ የበግ ለምድ ስለሚደርብበት የሚመስለው አውሬ ሳይሆን አዛኝ ቅቤ አንጓች(ሩህሩህ) ነው!!

ወደ ሰው ህይወት ዘልቆ ከገባ በኃላ ግን እውነተኛ የአውሬነትና የገዳይነት ባህሪው መገለጥ ይጀምራል....ለዚህ ም ነው መፅሃፍ ቅዱሳችን ዲያቢሎስ ሀሰተኛ ብቻ ሳይሆን የሀሰት ሁሉ አባት እንደሆነ የሚመሰክርልን:-

“እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።”ዮሐንስ 8፥44

ጠላታችን በአስመሳይነትና አታላይነት የሚመስለው ማንም የለም፤ ተክኖበታል....እርሱ የውሸቶች ሁሉ አድራጊ ፈጣሪ ሲሆን ንግግሩ ብቻም ሳይሆን የቆመበት መሠረት እንኳን ሀሰት ነው!!

ኢየሱስ ሲናገር እውነት እውነት እላችኃለሁ የሚለው በእውነት ጀምሮ በእውነት ስለሚጨርስና በንግግሩ ውስጥ አንዳች ውሸት ስለሌለ ነው....እባቡ ግን እንዳይነቃበት በእውነት ይጀምርና በውሸት ይጨርሳል፤ እውነት ውሸት እላችኃለሁና ማለት ይህም አይደል!!

“ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።”2ኛ ቆሮ 11፥14

የሰይጣን አስመሳይነት ይሄ ነው ተብሎ በቀላሉ የሚቀመጥ አይደለም፤ አጭበርባሪነት የብዙ ሺህ አመታት ማንነቱና ልምዱ ነው......ከአዳምና ሔዋን ጀምሮ ብዙዎችን በማታለልና በማጥመድ የአላማው ማስፈፀሚያ ሲያደርጋቸው ኖሯል....ዛሬ እግዚአብሔር የሚያወራን እኛም ብንሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ተታልለን እንዳንወድቅ ስለሚፈልግ ነው!!

“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።”2ኛ ቆሮ 2፥11

አቤት ስንቶች በዚህ የሰይጣን ሽንገላ ተታልለው ወደቁ.....ዛሬ መንፈስ ቅዱስ በኃይል ዐይኖቻችንን ከፍቶ እንዲያነቃን እፀልያለሁ፤ መናፍስትን የምንለይበት ቅባት ያግኘን......የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና ያደረገ ጌታ በህይወታችን ሁሉ ላይ በድብቅ የተመከረውን ምክር ሁሉ በኢየሱስ ስም ያፈራርስልን......ባለማወቅ በጠላት ወጥመድ ውስጥ ለገቡ ሁሉ እፀልያለሁ በኢየሱስ ደም ጉልበት ማምለጥ ይሁንላቸው....ጌታ ሆይ በዘመናችን የውርደት ሳይሆን የክብር ዕቃ ሆነን እንድናልፍ ፀጋህ በሙላት ይለቀቅልን...ከራሳችን አልፈን ለዚህ ትውልድ በረከት እንድታደርገን እፀልያለሁ....አሜን!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0