Get Mystery Box with random crypto!

ነፃነታችሁን ጠብቁ!! እስራኤላውያን ከግብፅ መራራ የባርነት አገዛዝ ጉበናቸው ላይ በቀቡት የበግ | Zaphnath-paaneah

ነፃነታችሁን ጠብቁ!!

እስራኤላውያን ከግብፅ መራራ የባርነት አገዛዝ ጉበናቸው ላይ በቀቡት የበግ ደም ነፃ እንደወጡ እንዲሁ በቀራኒዮ መስቀል ላይ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የከፈለልንን መስዋዕት በልባችን አምነን በአፋችን የመሰከርን ሁላችን ከሰይጣን አገዛዝ ተላቅቀናል...ክብር ለታላቅ ስሙ ይሁን!!

“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”ቆላስይስ 1፥13-14

ምንም እንኳን እስራኤላውያን ከፈርዖን አገዛዝ በብርቱ የእግዚአብሔር እጅና የተዘረጋ ክንድ ተላቅቀው ከግብፅ ወጥተው በምድረበዳ ወደ ከነዓን መንገድ ቢጀምሩም የተጎናፀፉትን ነፃነት የሚፈታተንና የሚገዳደር ነገር ጋር መገጣጠማቸው ግን አልቀረም!!

ከባርነት ነፃ መውጣት አንድ ነገር ሆኖ ሳለ በነፃነት መቆየት ደግሞ ሌላ ነገር ነው.....እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከ430 አመታት በኃላ ከግብፅ ቢያወጣቸውም ግብፅ ግን ከውስጣቸው አልወጣም፤ በዚህም ምክንያት በየፌርማታው ወደ ግብፅ ካልተመለስን እያሉ በማጉረምረም በመቀጠላቸው ብዙዎቹ ምድረበዳ ቀርተዋል!!

“እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።”1ኛ ቆሮንቶስ 10፥5

ተወዳጆች ሆይ ከጨለማ አገዛዝ በኢየሱስ ደም ነፃ መውጣታችን ድንቅ ነገር ቢሆንም ነፃነታችንን መጠበቅና መንከባከብ ግን የሁልግዜ ሥራችን ሊሆን ይገባል!!

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”ገላትያ 5፥1

ዛሬ ነፃነታችንን የምናስጠብቅበትን አንዱን ቁልፍ ልናገር:-ያልተቋረጠ ፀሎት....ሳይቋረጡ የሚፀልዩ ሰዎች ነፃነታቸውን በፍፁም አያሠርቁም.....ያልኩት ግን ፀሎት አይደለም፤ ያልተቋረጠ ፀሎት.....በግዜውም አለግዜውም፣ በተወሰነ ስፍራ ብቻ ሳይሆን ባገኘነው ቦታና አጋጣሚ የምንፀልይ ከሆነ በክርስቶስ ያገኛነውን ነፃነት ማስጠበቅ እንችላለን!!

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/ZaphnathPaaneah1
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0