Get Mystery Box with random crypto!

ሣንባ ይዘህ ድመት ማባረር አትችልም!! የድመት ማለፊያ ምግብ የሆነውን ሣንባ ይዘህ ድመቷን ለማ | Zaphnath-paaneah

ሣንባ ይዘህ ድመት ማባረር አትችልም!!

የድመት ማለፊያ ምግብ የሆነውን ሣንባ ይዘህ ድመቷን ለማባረር መሞከር ከንቱ ልፋት ነው....በተመሳሳይ ሁኔታ የሰይጣንን ግሳንግስ እየሰበሰብን እሱን ለመቃወም መሞከር በድንጋይ ላይ እንደማፍሰስ ይቆጠራል!!

በተለይ ስለመንፈሳዊ ውግያ ስንነጋገር ሁለንተናዊ ማለትም በህይወታችን ሁሉ የምናደርገው እንጂ ስንፀልይ ብቻ የጌታን ስም ጉሮሮዋችን እስኪነቃ እየጮህን የምንጠራበት ጉዳይ ብቻ አይደለም....ህይወታችንን በንፅህናና በቅድስና መጠበቅ በራሱ አንደኛው የመንፈሳዊ ውግያ መገለጫ ነው!!

አንዳንድ ግዜ ሰይጣን ዙሪያችንን እየዞረ አልፋታ ያለን ከእኛ ጋር ካለው የመለኮት ኃይል በልጦ ሳይሆን የማይገቡ ነገሮች በጓዳችን ተሸሽገው ስላሉ ይመስለኛል፤ ባለንብረቱ ደግሞ ንብረቱን ፈልጎ ከኃላ ከኃላ እኛን መከተሉ አይቀርም!!

ወዳጆቼ ሆይ በስውር ያስቀመጥናቸው(የደበቅናቸው) ለእግዚአብሔር ክብር የማይመቹ ጉዳዮች(ልምምዶች) በቤታችን ይኖሩ ይሆን???? ላባ እኮ ያዕቆብን የሰባት ቀን መንገድ የተከተለው ሳይነግረው ስለሄደ ብቻ ሳይሆን ራሔል ተራፊሙን ሰርቃበት ስለሄደች ጭምር ነው:-

ዘፍጥረት 31
²² በሦስተኛውም ቀን የያዕቆብ መኮብለል ለላባ ተነገረው።
²³ ከወንድሞቹም ጋር ሆኖ የሰባት ቀን መንገድ ያህል ተከተለው፥ በገለዓድ ተራራም ላይ ደረሰበት።

ይህንን ቁጥር 30 ላይ ማግኘት እንችላለን:-

“አሁንም የአባትህን ቤት ከናፈቅህ ሂድ ነገር ግን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ?”ዘፍጥረት 31፥30

ምናልባት የእኛ ያልሆነ(የሰረቅነው) ነገር በጓዳችን ይኖር ይሆን??....ይህንን ነገር ከቤታችን ጠራርገን እስካላወጣን ድረስ ጠላት እያነፈነፈ ዙሪያችንን መዞሩን አይተውም፤ ምክንያቱም የተሰረቀ ነገር ሁሉ ባለቤት አለው!!

የጨለማውን አለምንና እርግማንን ወደ ህይወታችን ከሚስቡ ነገሮች ሁለንተናችንን መጠበቅ አለብን....ያን ግዜ የክብር ዕቃ ሆነን በትውልዱ መካከል በክብር እንገለጣለን....ፀጋ ይብዛልን!!

“ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፤”ዘፍጥረት 35፥2

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0