Get Mystery Box with random crypto!

የንጉስ ልጅ ሆይ ስለምን ከሳህ?? (ከመንፈሳዊ ክሳት መዳን) “እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ | Zaphnath-paaneah

የንጉስ ልጅ ሆይ ስለምን ከሳህ??
(ከመንፈሳዊ ክሳት መዳን)

“እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።”2ኛ ሳሙኤል 13፥4

መቼስ ሰው ጎዳና ላይ እየኖረ ለምን ከሳህ ተብሎ አይጠየቅም፤ እንደዚህ ፀሃዩና ቁሩ እየተፈራረቁበት...በንጉስ ቤት እየኖሩና የላመውንና የነጣውን እየበሉ መክሳት ግን ለሰሚ ሁሉ ግራ ያጋባል!!

አምኖን መዋል የማይገባውና መውደድ የሌለበትን የማይመጥነውን ነገር መውደድና መፈለግ ሲጀምር ይሄ ነው የማይባል ክሳት ውስጥ ገብቶ ይሰቃይ ጀመር፤ የንጉስ ቤተሰብ መሆኑና የተመረጡ ምግቦችን መመገቡ ከክሳት አላዳኑትም...እንደውም ከቀን ወደ ቀን ክሳቱ ይጨምር ነበር!!

ዘንድሮም እንዲሁ ነው....በጣም ብዙ ሰዎች በንጉሱ እግዚአብሔር ቤት እየኖሩ ክሳት ግን ይታይባቸዋል፤ ያውም ከስጋ የሚብስ የነፍስ ክሳት...ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የማይገባንን ነገር ከመውደድና የማይመጥነን ስፍራ ላይ ከመገመት የሚመነጭ ነው!!

እስራኤላውያንም ከግብፅ ወጥተው ምድረበዳውን ወደ ከነዓን በመሄድ ላይ ሳሉ የማይገባ ምኞት ውስጥ ገብተው እግዚአብሔርን በማሳዘናቸው ለክሳት ተዳርገዋል!!

መዝሙር 106
¹⁴ በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
¹⁵ የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።


ከእግዚአብሔር ቤት ውጪ ሆነው ስለከሱት አይደለም የማወራው፤ ይልቁንም እያገለገሉ የከሱ፣ እየዘመሩ የከሱ፣ እየሰበኩ የከሱ፣ እየተነበዩ የከሱ፣ እየፀለዩ የከሱ....ሰማይ ነሃስ ምድር ደግሞ ብረት የሆነችባቸው.....እግዚአብሔር ከውስጥ ክሳት ያስመልጠን....የእግዚአብሔርን ዕቃ እንደሚሸከም የተመረጠ ሰው ከማይመጥነን ስፍራ እንውጣ...ሻሎም

“ስለዚህም ጌታ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።”2ኛ ቆሮ 6፥17-18

@ZaphnathPaaneah1
@Yoni4Christ
https://t.me/+I4DSx0eJ2iI2MDg0