Telkhis (هذه عقيدتنا) — የቴሌግራም ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا) T
የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا)
የሰርጥ አድራሻ: @telkhis
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.14K
ተመሳሳይ ቻናሎች ሃይማኖት
የሰርጥ መግለጫ

ይህ እኔ ወንድማችሁ "አህመድ ሲራጅ ሙሐመድ" ከተለያዩ ምንጮች ያገኘኋቸውን ቁም ነገር አዘል መልእክቶች የማጋራበት ቻናል ነው። ስለተወዳጁኝ አመሰግናለሁ።
ጌታዬ ሆይ!!
ወንጀሌን ሁሉ ይቅር በለኝ። አባቴንም ከፍ ካለችዋ ጀነት ኗሪ አድርግልኝ። እናቴንም በጤና ጠብቅልኝ። ሁሉንም ሙእሚን እና ሙእሚናትን ማራቸው፣ ይቅር በላቸው።
رب اغفر لي ولوالدي وللمؤمنين والمؤمنات

የቻናል ስታትስቲክስ
16.7% የተሳትፎ መጠን
689 እይታዎች / ልጥፍ
0 ልጥፎች / ቀን

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

11 aug 2022
ሙጚስ እና በሪራ رضي الله عنهما ሁለቱም ባሪያዎች ነበሩ። በትዳር ተጣምረው በፍቅር ተሳስረውም ይኖሩ ነበር። ኋላ ላይ ግን በሪራ ከባርነት ቀንበር ቀደም ብላ ነጻ ወጣች። እንደሚታወቀው ሁለት በባርነት ላይ ሳሉ የተጋቡ ባለትዳሮች አንዳቸው ቀድመው ከባርነት ነጻ ከወጡ ትዳራቸውን የማፍረስ መብት ተሰጥቷቸዋል። እናም በሪራ ቀድማ ነጻ ስትወጣ ሙጚስን አልፈልግህም አለቺው። ሙጚስ ደግሞ ልቡ ውልቅ እስከሚል ነበር በሪራን የሚያፈቅራት። ያለ የሌለን ሽማግሌ እየላከ አስለመናት። በሪራ ግን አሻፈረኝ አለች። ሽምግልናው ነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘንድ ደረሰ። ነብዩም ለሙጚስ ሽማግሌ ሆነው ከበሪራ ዘንድ ሄዱ። አብራችሁ ኑሩ ብለው መከሯት። ያረሱለሏህ ትእዛዘዎ ነው? ብላ ጠየቀች። አይ ትእዛዝንኳ አይደለም። ሽምግልና ነው ብለው መለሱ። እንግዳውስ ሽምግልና ከሆነ ሙጚስን አልፈልገውም ብላ የነብዩንም ሽምግልና አሻፈረኝ አለች። ነብዩም صلى الله عليه وسلم ሽምግልናቸውን ስለመለሰች አልወቀሷትም። አልተቀየሙባትም።

ስለዚህ
1- ለምን እንደተወችው ሳታውቁ እንደዚያ የሚያፈቅትን ባሏን እርግፍ አድርጋ ተወችው፣ የእሷማ ግፍ የተለዬ ነው አትበሉ። ነብዩ በሪራን እንድህ እንስፍስፍስ ብሎ የሚያፈቅርሽን ባልሽን እንዴት ትተይዋለሽ ብለው መች ወቀሷት። ለምን እንደፈታት በትክክል ሳትረዱ (ብትረዱም ጭምር) እሷ አፈቅረዋለሁ ስላለች ብቻ እሱን አትውቀሱ።

2- ሽምግልና ሞክራችሁ ካልተሳካ ንቀውኝ ነው አይደል አትበሉ። የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሽምግልና መች ተሳካ። አንተ ከነብዩ በላይ የምትከበር ሰው ነህ እንዴ?

3- ለመለያየት መበዳደልን መናገር ግዴታ አድርጋችሁ አትውሰዱ። በሪራ ምን በደል ደርሶብኛል ብላ ተፈታች?

4- ሽምግልና ታላቅ ዒባዳ መሆኑን አትዘንጉ፣ አጅሩም ከሽምግልናው ዉጤት ጋር የተሳሰረ አይምሰላችሁ። ዉጤቱ ምንም ይሁን ምን ሞክሩ። አጅሩ አይቀርባችሁም።

5- ሸሪዐዊ ትእዛዝት በሙሉ የሚገድባቸው መረጃ እስካልተገኘ ድረስ መሰረታዊዉ መነሻ መርሃቸው ግዴታነት እንደሆነም እወቁ። በሪራ رضي الله عنها "ያረሱሉሏህ ትእዛዘዎ ነውን"?? ብላ ስትጠይቅ አዎ ትእዛዝ ነው ቢሏት ኖሮ ያለምንም ማንገራገር ቀጥ ብላ ከሙጚስ ጋር ልትኖር ነበርኮ።

(شرح خلاصة قواعد الأصولية)

እናንተም ጨማምሩበት።

T.me/telkhis
689 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ስለ Telkhis (هذه عقيدتنا) በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

Telkhis (هذه عقيدتنا) 4.14K ተመዝጋቢዎች ያሉት የቴሌግራም ቻናል ነው። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ ግምገማዎች፣ ደረጃ እና ዝርዝር ስታቲስቲክስ ይገኛሉ።
በዚህ ገጽ ላይ "ወደ ቻናል ይሂዱ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ ወይም @telkhis ን በቴሌግራም መተግበሪያ ውስጥ ይፈልጉ። እንዲሁም የቻናሉን የተጠቃሚ ስም ገልብጠው በቴሌግራም መፈለጊያ ውስጥ መለጠፍ ይችላሉ።
አዎ፣ Telkhis (هذه عقيدتنا) ነፃ የቴሌግራም ቻናል ነው። ሁሉንም ልጥፎች ያለምንም ክፍያ መከታተል እና ማንበብ ይችላሉ።
የTelkhis (هذه عقيدتنا) ቻናል በአሁኑ ጊዜ 4.14K ተመዝጋቢዎች አሉት። የተመዝጋቢዎች ቁጥር በመደበኛነት ይዘመናል።
Telkhis (هذه عقيدتنا) ይዘቱን በዋናነት በአማርኛ ቋንቋ ያትማል። መልእክቶቹን ለማንበብ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ ቻናሉን በቴሌግራም ይክፈቱ።
አዎ፣ ተመሳሳይ የሃይማኖት ቻናሎችን ከታች "ተመሳሳይ ቻናሎች" በሚለው ክፍል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ተዛማጅ የቴሌግራም ቡድኖችን፣ ቦቶችን እና ተለጣፊዎችንም እናሳያለን።
መልእክቶቹ በቴሌግራም ውስጥ ይነበባሉ፦ በዚህ ገጽ ላይ ባለው ማገናኛ Telkhis (هذه عقيدتنا) ን ይክፈቱ። በዚህ ገጽ ላይ የቻናሉ መግለጫ፣ የተመዝጋቢዎች ብዛት፣ ግምገማዎች እና ስታቲስቲክስ ያገኛሉ።
Telkhis (هذه عقيدتنا... avatar
Telkhis (هذه عقيدتنا... @telkhis
በቴሌግራም ይክፈቱ