Get Mystery Box with random crypto!

Telkhis (هذه عقيدتنا)

የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا) T
የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا)
የሰርጥ አድራሻ: @telkhis
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.09K
የሰርጥ መግለጫ

((( @IbnusirajBot )))

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-07-26 17:56:15 በትናንሽ ጠላቶች ላይ በማተኮር ዋናውን ጠላት መዘንጋት የከፋ ጉዳትን ያደርሳል። ጥቃቅኖቹን ጸቦች ከልካቸው በላይ ለጥጠን እንድንወስዳቸውና ወደበለጠ ጸብ እንድንገባ ያደርጋል።
አባት ከልጁ
ወንድም ከእህቱ
ባል ከሚስቱ
ጓደኛ ከጓደኛው ጋር ሲጋጭ
ዋነኛው ጠላታችን ሸይጧን መሆኑን ከግምት ውስጥ ያስገባ የተፈጠረውን ግጭት በልኩ መያዝ ይችላል። ለማስተካከልም አይከብደውም። ሸይጧን አጋጭቶን እንጂ እኛማ ወዳጆች ነንኮ ማለቱ አያሳፍረውም።
ለዚያም ነው የዕቁብ ልጁን ዩሱፍን عليهما الصلاة والسلام
ከወንድሞቹ ተንኮል ካስጠነቀቀው በኋላ "ሸይጧንኮ ለሰው ልጅ ግልጽ የሆነው ጠላቱ ነው" ብሎ የመከረው።
ወንድሞችህን ተጠንቀቃቸው እንጂ በጠላትነት አትፈርጃቸው፣ የሸይጧን ሴራ ነው በአንተ ላይ እንዲያሴሩ የሚያደርጋቸው ብሎ መምከሩ ነው። ኋላ ላይም ዩሱፍ ነብይና የመጋዘኑ ዋና አስተዳደር በሆነበት ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር ሲታረቅ" በኔና በወንድሞቼ መካከል ሸይጧን ነው ተንኮልን የፈጸመብን" የሚልን ሀሳብ የተናገረው።

T.me/telkhis
278 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 17:07:29 ተንኮል ተመልሶ ራስን ይጠልፋል። ለነገ መልካም ሰው ለመሆን በማሰብ ዛሬህን በግፍ አታበላሽ።
ዩሱፍን عليه الصلاة والسلام የስጋ ወንድሞቹ ተጋግዘው ከጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ በመወርወር ዝናውን ሊያከስሙት፣ ተወዳጅነቱን ሊያሳጡት ሞከሩ። በዚህ ድርጊታቸውም አባታችን ዘንድ የበለጠ ተወዳጅነትን እናተርፋለን ብለው አቀዱ። ምንም እንኳ ዩሱፍ ከየእቁብ عليهما الصلاة والسلام እይታ ቢሰወርም ከአእምሮው ግን የበለጠ እየገዘፈ መጣ፣ ደጋግሞ የሚያወሳው ዩሱፍን ሆነ። አብዝቶ የሚያስበውም ስለዩሱፍ መገኛ ጊዜ ሆነ። አባታችን ዘንድ የበለጠ እንወደዳለን ብለው ግን ይባስ ተጠሉ። ከብዙ አመታት በኋላ ዩሱፍም ከጉድጓዱ ወጥቶ እነሱ ደግሞ የዩሱፍን እጅ ከጃዮች ሆነው ቀረቡ።

T.me/telkhis
327 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 09:55:35 ዑመር ገነቴ ከዑመር ይማም በምንድነው የሚለየው?
~~~~~~~
1- ሁለቱም አሕባሾች ናቸው።

አሕባ - ሽ እዚህ እንዲደርስ ያመቻቸው ከዑመር ይማም ይልቅ ዑመር ገነቴ ነው። አሕባ/ሽ ገና በሁለት እግሩ ሳይቆም በ90ዎቹ ከሊባኖስ በመጡ አሕባ/ሾች የማጥመቅ ስልጠና ሲሰጥ መርቆ የከፈተው ዑመር ገነቴ ነው። አሕ/ባሽ እግሩን በተከለበት ከ1992 እስከ 2000 ድረስ የዑለማእ ምክር ቤት ሊቀመንበር ነበር። ከሚያዚያ 2001 ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ ከፌደራል መጅሊስ አመራሮች ውስጥ ነበር። ይሄ ዘመን የአሕባሽ ፈተና የጠነከረበት ጊዜ ነው። ሐምሌ 9 እና 10/2004 ራስ ሆቴል ውስጥ በተካሄደ የአሕ/ባሽ ኮንፈረንስ ከ100 የሚበልጡ ሱፍዮች ከመላው ሃገሪቱ ተሰብስበው "ወሃ-ቢዮች" የሚሏቸውን ሙስሊሞች ሁሉ ከኢስላም በማስወጣት የክህደት ብይን ሰጥተው መግለጫ አውጥተዋል። ከ 2005 ጀምሮ ደግሞ እስከ 2010 ድረስ የፌደራል መጅሊስ የጠቅላላ ጉባኤው አባል፣ የመስጂድና አውቃፍ ዘርፍ ሀላፊ እንዲሁም የዑለማ ምክር ቤት አባል ሆኖ ሰርቷል። በዚህም ዘመን በአሕ-ባሾች ምን እንደ ደረሰ የምናውቀው ነው።

2- ሁለቱም ሙስሊሞችን ያ - ከ * ፍ - ራ - ሉ።

አዎ ሁለቱም አላህ ከዐርሹ በላይ ነው የሚሉ ሙስሊሞችን በሀሰት "ሙጀሲማ" የሚል ቅፅል ለጥፈው በከሃዲነት የሚፈርጁ ናቸው። የዑመር ይማም አያከራክርም። "ወሃ-ቢዮች ያረዱት አይበላም፣ ኒካሕ የላቸውም" እያለ ባደባባይ የሚናገር ነው። "ዶክተር" አቡበክር የሚባለውም አሕ-ባሽ በቅርቡ ሆሳእና ላይ ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል። እነዚህ ሰዎች የ"ሙፍቲው" ጀማዐ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። ዑመር ገነቴ እራሱ "አላህ ከ0ርሽ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም የሚያስወጣ ፅንፈኛ እንደሆነ የድምፅ ማስረጃ አለ።

3- ሁለቱም ሙስሊሞችን በጠላት ለማስመታት የሚጥሩ ጠላቶች ናቸው።

ዑመር ገነቴ አይደለም እንዴ ክርስቲያኖችን ጭምር ለአመፅ የጠራው? ወደ ደም መፋሰስ የቀሰቀሰው? መስጂድ እያቃጠለ፣ ሙስሊሞችን እየገደለ ያለው ቡድን የሱ ጀማዐ አይደለምን? እስኪ መቼ ነው የሙስሊሞች መሪ፣ የዑለማእ ቁንጮ ነኝ የሚለው ይሄ ሰውዬ በተከታዮቹ የተፈፀመውን ይህንን ፀያፍ ድርጊት የኮነነው? እንዲያውም ቅስቀሳ ሲያደርግ ነው የምናውቀው። እንዲያውም ሙስሊሞችን በጠላት ለማስመታት በግላጭ ሲሰራ የኖረ ሰው ነው። እስኪ ይህንን ጥቅምት 30/2012 በሸገር ሬዲዮ ከቀረበው የዑመር ገነቴ ቃለ ምልልስ የተወሰደ ንግግር መላልሳችሁ አስተውሉ!! ይሄው:–

"ለባለስልጣኖቹም፣ ለእነ አባይ ፀሃዬ – የዚያን ግዜ የደህንነት ኃላፊ ነበሩ –
‘ተው እባካችሁ! ይኼ ችግር (#ሰለፍያን ማለቱ ነው) መንግስት ላይ ይወጣል። እኛ ላይ ብቻ ሳይሆን እናንተም ላይ ይደርሳል’ እላቸው ነበር።
በኋላ እንግዲህ በእነመለስ ግዜ እነርሱ ላይ ሲደርስ መጥፋት አለበት ብሎ ያ ሁሉ ችግር ተፈጠረ። መጀመሪያውኑ ከውጥኑ ማጥፋት ይቻል ነበር።"

ተመልከቱ! መንግስት ሳያስብ በፊት አሕባሽ ያልሆኑ ሙስሊሞችን እንዲያጠፋላቸው ሲወተውት ነበር ማለት ነው። እነዚህ አቅሙ ቢኖራቸው እንደ ዮሐንስ ሙስሊሞችን አጋድመው ያርዱ።

ቀጠለ:—

"መንግስት የዚያን ግዜ በጎናችን አልቆመም። መፈለግ አይፈልገውም። ሙስሊሙ ላይ ብቻ ይቀር መስሎታል እንጂ ወደ መንግስት ያልፋል አልመሰለውም። አሁን ሀገሩ በሙሉ ተዳርሷል። ለማጥፋት አልተቻለም። ወደአንድነት መጥተን ሰላም ቢሆን ይሻላል ሀገሩ ብለን ነው። ወደን አይደለም በአንድነት የምንታየው። ማጥፋት ካልተቻለ አብሮ በሚሆንበት ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል በሚል ነው።"

ምንኛ ልብ የሚያደማ ንግግር ነው?!

4- ዑመር ገነቴ ከዑመር ይማም በላይ የተውሒድ ደዕዋን ሲዋጋ የኖረ ነው። እራሱ እንዲህ ሲል ይመስክራል:-
«ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ–ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ትላላችሁ! ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እና ዐብዱ-ር-ረሕማን ናቸው ወሃቢያን የመሰረቱት፡፡ ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እንጂ ዑመር አይደለም ወሃቢያን የመሰረተው፡፡
እኔ ብቻዬን ስታገል ነው የኖርኩት፡፡.....
ዐቂዳ ትላላችሁ ...ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ነው ወሃብያን የመሰረተው። ዐብዱ-ር-ረህማን ነው ወሃብያን የመሰረተው፡፡ ... ወደኛ የመጣችሁ እደሆነ የዘከዘኩት እንደሆነ ሌላ ታመጣላችሁ!……
ወሃብያን የመሰረተው ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እና ዐብዱ-ር-ረህማን ናቸው፡፡ ስንታገል ነው የኖርነው .... ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ናቸው እንዴ ወሃብያን የታገሉት? ማን መሰረተው?"
ዑመር ገነቴ በ 90 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ባህርዳር ላይ በፖሊስ በታጀበ ስብሰባ ታዳሚዎችን ሲያስጨንቅ ነበር።

አንገቱን የደፋበትን ፎቶ እየለጠፋችሁ አጉል አንጀት ለመብላት አትሞክሩ። ሓሪሥ አልሙሓሲቢ ከዑመር ገነቴ በዒልምም፣ በአደብም፣ በአቋምም የተሻለ ነበር። ኧረ ጭራሽ የሚነፃፀሩም አይደሉም። ነገር ግን በያዘው የቢድዐ አቋም የተነሳ ዙህዱም፣ አደቡም፣ ... በነ ኢማሙ አሕመድ ከመወገዝ አላዳነውም። "እርጋታውና ልስላሴው አይሸውድህ። እራሱን በመድፋቱ እንዳትሸወድ" ነበር ያሉት። ይሄኛው ምኑ ነው የሚሸውደን? እብሪትና በባዶ መኮፈስ እንጂ ምን አደብ አለውና! ለማይታዘነው እያዘናችሁ ተሸውዳችሁ ሌሎችን አትሸውዱ። ለእዝነትም ቦታ አለው። ያለ ቦታው እያዋላችሁ አታሪክሱት። ለማይገባው እያለቀሳችሁ ቅጥ አታሳጡት። በጥቅም ተጋሪዎቹ ወይም በመዝሀብ ዘመዶቹ ሙሾ አትሸወዱ። ሁለቱም ዑመሮች በዐቂዳም ሆነ ለሙስሊሞች ባላቸው አደጋ ልዩነት የላቸውም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
60 views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 17:17:41
ዉዱ ቃሪእ ወንድማችን ዐፊፍ ታጁ
260 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 15:41:24 የትኛውም ቆዳ እስከታረበ ድረስ ንጹህ ነው። መጠቀም ይቻላል።
የዉሻም፣ የአሳማም፣ የአህያ፣ የነብርም፣ የጂብም።

"#ማንኛውም ቆዳ ከታረበ በርግጥም ጦሃራ ሆኗል" ብለዋል ነብዩ صلى الله عليه وسام።

ሸይኽ አልባኒ رحمه الله

T.me/telkhis
321 views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 15:50:13 አንዴንዴ ይሉኝታ የሌላቸው፣ ሞራልን የማይጠብቁ መልሶች ተገቢ ናቸው። በተለይም ስህተቱ እንዳይደገም ለማድረግ ከተፈለገ አንገት የሚያስደፋ፣ ቅስም የሚሰብር መልስ መስጠት ተገቢ ሊሆን ይችላል።
ነብዩ صلى الله عليه وسلم ኸዲጃን ደጋግመው በበጎ በማነሳሳታቸው ምክንያት ቅናት ያደረባት እናታችን ዓኢሻ رضي الله عنها
"ምንድን ነው ያችን ጥርሷ የረገፈን አሮጌት አሁንም አሁንም ማነሳሳት፣ ከሷ የተሻለች እኔን መሳይ ቆንጆ አላህ ተክቶልዎት የለምዴ" የሚል ይዘት ያለውን ቃል ተጠቅማ ኸዲጃን ልታጣጥል ፈለገች። የነብዩ صلى الله عليه وسلم መልስ ግን ጠጠር ያለ ነበር።
"በአላህ ይሁንብኝ ከኸዲጃ የተሻለችንማ አልተተካልኝም" ብለው እንጥል ቆራጭ መልስ ሰጧት። ኧረ መች ይሄ ብቻ
ኸዲጃ رضي الله عنها በምን በምን እንደምትበልጣትም ዘረዘሩላት እንጂ።

T.me/telkhis
290 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:12:33 ቀጣዩን የትግል አቅጣጫ እስከምናሳውቃችሁ ድረስ
#ያሲንን_እየቀራችሁ፣ ዱዓእ እያደረጋችሁ በትእግስት ጠብቁን አሉ አህባሾች።

"ሱረቱል ዋቂዓን በየሌሊቱ ያነበበ ሰው ድህነት አይነካውም" የሚል ትርክት ነበርና ያንን አስታወሰኝ።

ያሲንን ቀርቶ መጅሊስን መረከብ ከተቻለማ እኛም እንወጥራለን።
87 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:47:35 ምስክር የሌለው ፍቺ እንደፍቺ አይቆጠርም ይላሉ ሸይኽ አልባኒ። ይህም በቁርአንም በሀዲሶቹም ላይ ተጠቅሷል። በተለይ በዚህ ዘመን ያለ ምስክሮች የተፈጸመን ፍቺ ተፈትቻለሁ ብላችሁ ብዙም አትተማመኑበት። በተቻላችሁ መጠን በቤተሰብና በሽማግሌዎች አስረግጡ። ይህ አለመሆኑ ቀጣዩን ትዳራችሁን ያወሳስብባችኋል።

ከዑለማኦች እይታ፣ ከሚያጋጥመን፣ ከትዝብትም ጭምር ነው ይህን ያልኩት ።
312 views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:13:40 #አልሀምዱሊላህ
ሙስሊምነታቸው በሚያጠራጥር ግለሰቦች ሲመራ የነበረው የሙስሊሞች ተቋም ወደ ሙስሊሞች እጅ ተመልሷል። ይህ ያስደስታል። ባይሆን ግን ይሄኛውም ቡድን ቢሆን እነሱን ያልመሰለን ሁሉ የሚገፋ መሆኑ የሚገመት ጉዳይ ነውና ደስታችሁን በልክ አድርጉት።
245 views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 12:37:03 ሙዚቃ ያው ሙዚቃ ነው።
በዐረብኛም ብትዘፍነው በአማርኛ
ነብዬ ነብዬ--- ብትለውም ኢትዮጵያ ሀገሬ--- ብትለውም ያው ሙዚቃ ነው። ነብዬ ነብዬ ብለህ ስለዘፈንክ ሰላም ለሀገሬ ብሎ ከሚዘፍነው የተሻልኩ ነኝ ብለህ አታስብ።
344 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ