Get Mystery Box with random crypto!

Telkhis (هذه عقيدتنا)

የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا) T
የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا)
የሰርጥ አድራሻ: @telkhis
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.09K
የሰርጥ መግለጫ

((( @IbnusirajBot )))

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-07-03 21:49:30
"ስጋው ይበላል"
ከእለታት በአንዱ ቀን ለነብዩ صلى الله عليه وسلم ከቀረበው የምግብ ማድ ላይ የዚህ ተሳቢ እንስሳ (الضب) ስጋ ቀረበ። ነብዩ صلى الله عليه وسلم ስጋውን ከመብላት ተቆጠቡ። ኻሊድ ቢን ወሊድ رضي الله عنه ግን ስጋውን ወደሱ አቅራቢያ ጎተት አድርጎ ተመገበው። ሀዲሱ ቡኻሪና ሙስሊም ላይ ሰፍሯል።
ስጋው ሀራም ቢሆን ኖሮ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ኻሊድን እንዳይመገበው ይከለክሉት ነበር።
979 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:46:46 ሙስሊም ወንድምህን ይቅር በል። በአንተ ሰበብ ሙስሊም ወንድምህ ለቅጣት ቢዳረግ አንተ ምን ትጠቀማለህ!!!

አህመድ ቢን ሀንበል رحمه الله
ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ 2/262

T.me/telkhis
957 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:36:30 ሁሉም ዑለማዎች ከጭፍን ተከታይነት ያስጠነቅቃሉ። በጣም ብዙ ቦታ ጭፍን ወገንተኝነት ይቃወማሉ። እነዚሁ የሚቃወሙት ዐሊሞች እንወዳለን የሚሉ ሰዎች ምክራቸውን ወደጎን በመተው «በነሱ ላይ ወገንተኛ» ይሆናል።
...................

"አቡ ሙስሊም ናሙስ"
899 views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 09:51:12 ሸይኽ አልባኒ رحمه الله
የሆነ ሰው መጥቶ ልጆቼ ሰላም ብለውሃል፣ እጆችህንም ስመዋል ሲላቸው አይወዱም ነበር። እንድህ አይነት ወሬዎች ለዉሸትና ለግነት የተጋለጡ ናቸው ብለው ስለሚያምኑ ነው የማያስደስታቸው።
889 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 06:39:41
910 views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:42:53 አቡ ዳውድ በሱነናቸው ላይ ባሰፈሩት ሀዲስ መሰረት:

ነብዩ ﷺ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት፣ ዐሹራእን፣ ከየወሩ ሶስት ቀናቶችን እንድሁም የወሩን የመጀመሪያውን ሰኞ ይጾሙ ነበር።
879 viewsedited  05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 18:18:27 90 ኸይር ስራዎች
1.0K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 10:43:38 ኡድሂያ ለማረድ ካቀዱ ከወዲሁ ጥፍርና ጸጉርዎን ከመቁረጥ ይቆጠቡ!
-------------------
አንድ ሙስሊም ሀጅ የማያደርግ ከሆነና በዒድ አል አድሀ እለት ኡድሂያን ለማረድ ካሰበ የዙልሂጃ ወር ከገባበት የምጀመሪያዉ ቀን ጀምሮ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም፤ ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህም ተከታዩን የኡሙሰለማ ሀዲስ መሰረት ያደረገ ነው።

ከኡሙ ሰለማ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያ ለማረድን ካቀደ፤ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል። በሌላም ዘገባም «ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩና ከጥፍሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል። እንደዚሁ፤ «ከሰውነቱ ቆዳ ወይም ከፀጉሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል።

ይህ ማንኛውም ሙስሊም እራሱን በሀጅ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የሚያመሳስልበት እና የተወሰኑ የኢህራም ክልከላዎችን ከነሱ ጋር የሚጋራበት ዲናዊ ስርአትና ነብያዊ ትዕዛዝ ነው።

☞ጸጉርንና ጥፍርን ከመቁረጥ የሚከለከለው ለራሱ ወይም ለሰው በራሱ ገንዘብ የሚያርድ ሰው ብቻ ነው። ህጉ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው ሲባል፤ በወኪልነት ለሌላ ስው የሚያርድን ሰው አይጨምርም።

እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም ማካካሻ ከፋራም የለበትም። አንዳንዶች እንደሚያስቡት ሳይሆን ወንጀሉን ቢፈፅምም ኡድሂያ ማረዱን መተው የለበትም።

በስህተት ወይም በመርሳት ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን የቆረጠ ሰው ምንም ወንጀል የለበትም። በተመሳሳይ መልኩ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ቢቆርጥ ችግር የለውም። ለምሳሌ የተጎዳን የሰውነት ቆዳ ለማከም ወይም የተሰበረ ጥፍሩን ለማስተካከል መቁረጥ ይፈቀድለታል።

፠ ስለ ኡድሂያ ጥቂት ተጨማሪ ነጥቦች

1 - በዙልሂጃ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደ አላህ መቃረብ አንዱ ነው።

2- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች መካከል ነው። ኡድሂያ የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

3- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ ተቅዋና ታዛዥነት ግልጽ ማድረጋችንን ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፤

‎{ﻟَﻦ ﻳَﻨَﺎﻝَ اﻟﻠَّﻪَ ﻟُﺤُﻮﻣُﻬَﺎ ﻭَﻻَ ﺩِﻣَﺎﺅُﻫَﺎ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻳَﻨَﺎﻟُﻪُ اﻟﺘَّﻘْﻮَﻯٰ ﻣِﻨﻜُﻢْ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﺳَﺨَّﺮَﻫَﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻟِﺘُﻜَﺒِّﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻫَﺪَاﻛُﻢْ ۗ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ اﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ} الحج 37

አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» አል ሐጅ 37

4- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

5- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

6- ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

7- የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ ወይም የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

8- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋራትም ይቻላል።

9- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

10- የኡድሂያውን ስጋ፣ ለቤት፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ ሶስት ቦታ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
1.1K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:02:32 እውነተኛ ወዳጅነት
መቀበልን በመመኝነት እንድሁም ሲከለከሉ (አልችልም፣ የለኝም ሲባሉ) በመራቅ ላይ የተመሰረተ አይደለም። ጓደኝነት ከዉለታ ጋር ፍጹም መያያዝ የለበትም።

T.me/telkhis
868 views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 09:48:44 ኢማሙ ሸርቃዊ እንደሚሉት
"ለፍተው ያገኙት በነጻ ከተገኘው በላይ ዉድ ዋጋና ልዩ ቦታ አለው።"

ድክክም እስከሚልህ ታግለህ አግኝ ብለው የሚያሰለቹን ለካ ለዚህ ነው!!

T.me/telkhis
900 viewsedited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ