Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-23 07:09:18
#የማለዳ_ቃል

መዝሙረ ዳዊት 124
2 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3 ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤
4 በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
5 በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
6 ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.7K viewsMeron, edited  04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 20:00:21 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=55
ሳባ ካሳሁን

ዛሬ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ እየተጣደፍን ነው ሊዱ ልክ እንደ ህፃን ልጅ እማዬ ያዝ አድርጋት ፊቷን ታሻሽላታለች እሷ ግን ልቧ በጣም የምትወዳቸው ጋሽዬ ጋር ስለነበር እማን እያስቸገረቻት "ሜሪ! ኸረ ሜሪ! ቶሎ በያ!" ብላ ደጋግማ ትጠራኛለች እኔ ስሜቴና ባህሪዬ ፍፁም ተደበላልቀው ለምንም ነገር ግድ መስጠት እንዳቆምኩ ነው ቦርሳዬን ያዝኩና እንደ ወትሮው ቦታ የማልሰጣቸውን እናትና አባቴን "በቃ ሄደናል ሰላም ዋሉ" ብያቸው የመጀመሪያ ትምህርት የምንጀምርበት ቀን እንደመሆኑ ቃሉን አንብበን ፀልየን ክርስቶስ ከፊታችን እንዲቀድም በመንፈሱ ተሞልተን መውጣት ሲገባን አባዬ "ቆይ. .ሜሪ" እያለኝ ቅዱሱን መፅሀፍ ሊያመጣ ሲኔሳ እኔ ግን ሊዱን እያጣደፍኩ ይዣት ወጥቻለሁ ቡቻዬ አሁንም ልክ እንደ በፊታችን ነች ልቧ ፍፁም ንፁህ ነው ከጥርሶቿ ሳቅ አልተለየም ከባህሪዋም አንዳችም ለውጥ የለም እኔን እየተሰማኝ ያለው መንስኤ ወይ ከየት እንደመጣ ተጨባጭ ማስረጃ የሌለው ተስፋ መቁረጥ፣ መሰላቸትና ብቸኝነት ሁሉ እሷ ጋር የሚገለፀው በፈገግታዋ ነው እንደረፈደብን እያወቀች በጣም የምትሳሳላቸውና የፈለገ ቢመጣ እነሱን ሳታይ የማትቀርበት አባዬ የምትላቸው ጋሽዬ ጋር እየሮጠች ሄዳ በመቆሸሹ ምክንያት ከነጭነት ታሪኩ ወጥቶ ቀለሙን በቀየረው ጋቢያቸው ስር ተሸጎጠች። እሳቸውም ዐይናቸው ማየት አይችልምና በጉያቸው እቅፍ ስትገባ የሚንሰፈሰፍሏትን ልጃቸውን ፀጉሯን እየደባበሱ ". . . መጣሽ? ልጄ. .መድሀኒቴ መጣሽልኝ?" አሏት እሷም እጃቸውን ጥብቅ አድርጋ ይዛ "አዎ አባዬ መጣሁ. . ደሞ አባ የሚጣፍጥ ቁርስ ይዤልሀለሁ ላጉርስህ" ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ የቋጠረችላቸውን ማዕድ አውጥታ ታጎርሳቸው ጀመር።

የእኔ የተዘበራረቀ ስሜት ግን አይደለም በትዕግስት እስክትጨርስ ሊያስጠብቀኝ በፈገግታ እንኳን እንዳያቸው የማይከፈልበትንም ሰላምታ እንዳቀርብላቸው አላስቻለኝም ራቅ ባለ አንድ ፓል ጋር ደገፍ ብዬ የመሰላቸትና የድብርትን ትንፋሼን በረጅሙ እየተነፈስኩ ሳለ እነ ናሆሜ ከሩቁ ሲመጡ አየኋቸው እነሱም እንደኔ ልክ ከራስ ጋር ትግል ያለውን አስቀያሚ የመረበሽ ስሜት ያህል እንደዚያ ፈገግታቸውና ሳቃቸው ከላያቸው ርቋል በዚያው ድባብ እንዳሉ ሰላም አሉኝና ናሆሜ ብቻዬን መቆሜ ግራ አጋብቶት "ሜሪዬ ሊዱስ?" አለኝ እኔም በምልክት ወደ ጋሼ እያሳየሁት "ያቹትልህ" አልኩት ቢኒ በሁኔታዬ ሳቅ አለና "እንዴ ታድያ አንቺ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ ኸረ ኑና ጋሼን ሰላም እንበላቸው" ብሎ እኔና ናሆሜን ግራና ቀኝ ይዞን ወደነ ቡቹዬ ሄድን ጋሼ እጅግ በጣም ትልቅ ፍቅርና የሰው ረሀብ ያላቸው ሰው ናቸው ሊዱ ስታጎርሳቸው ከያዘችው ምግብ ይልቅ እጇን ሳም ያደርጓታል ልክ ድምፃችንን ሲሰሙ በቀልድና በሚያስደስት ጨዋታቸው ተሞልተው "እናንት ጮሌዎች መድሀኒቴን ልትወስዱብኝ ነው አይደል?" አሉንና ሁለቱንም እጆቿን አጥብቀው ያዟት አንዳንዴ ናሆሜ የጋሼ ከሊዱ መለየትን መፍራት ሲያስበው "ሜሪ ግን ጋሼ ሊዱ ከዚህ ስትሄድ እንዴት ነው የሚሆኑት?" ብሎ ይጠይቀኛል በዚያ ሰዐት የኔ ምላሽ እምባ ባቀረረ አይኔ ዝምታ ነበር። ቢኒ ቀስ አድርጎ "ጋሽዬ ትምህርት ቤት ረፍዶብናል ለዛ ነው" አላቸው እሳቸውም ሊዱዬ እንድትማርና አንድም ነገር እንዲጎልባት ስለማይፈልጉ "ሂጅ! ሂጅ መድሀኒቴ ይቺን ታህል ጠረንሽን ካሸተትኩ ከእጅሽ ከቀመስኩ ምን ፈልጋለሁ?" ሂጅ ቡቻዬ" ብለው በዳበሳ እጇን ሳምዋት እሷም እየተፍለቀለቀች "በቃ አባዬ ቻው እሺ! ደሞ ትንሽ ብር ነው የጎደለኝ ሰሞኑን ከየትም ሞልቼ አሳክምሀለሁ ቻውውው" ብላቸው አብረን መሮጥ ጀመርን ትንሽ እንደሮጥንም ከወደ ትምህርት ቤታችን ደረስን ግቢው በሙሉ ተለውጧል በትምህርት ቤታችን አዳዲስ የ""እንኳን ደህና መጣችሁ"" ማስታወቂያዎች ተለጥፈዋል ሳር ቅጠሉ ሁሉ ከበፊቱ እድግ ብለው ለግቢው ውበትን አላብሰውታል የመጀመሪያ ቀን ስለሆነ ሁሉም ተማሪዎች ክፍል አልገቡም በግቢው ውስጥ ስንሄድ ያዩን ሁሉ ዕርስ በዕርሳቸው በመገረም አፋቸውን ከፍተው "ፐ! እነዚህ እኮ ናቸው ከall የዘጉት ፐ 'ኸረ ይመቻቸው አንደኞች! 'ደግሞ ሲያምሩ በጭራሽኮ አይለያዩም' ይባባላሉ አንዳንድ እኛን የማይወዱን በፊት ላይ የወንጌል አርበኞች ሆነን በሄድንበት የምንሰብካቸው ሲቃወሙን የምንባርካቸው ደግሞ በቅናትና በምቀኝነት እያዩን "ቲሽ ባካችሁ አስደግመው እኮ ነው እነዚህን እኮ አብረን ተምረን እናውቃቸዋለን ምንም አያውቁም" እያሉ በውሸት ያሙናል እኛ ግን ከማንነታችን ይልቅ በስሜታችን ስለተዋጥን ምንም ሳይመስለን ክፍላችን የት እንደሆነ መፈለግ ቀጠልን በጣም የሚገርመው ነገር የደረሰን ከእነ ሊያ ጋር አንድ ክፍል ነው ሁላችንም በጣም ደስ አለን ከኬብሮኔ ጋር ብዙም ሳይቆዩ መጡ ደስታችንን መቆጣጠር ስላቃተን ሰላምም ሳንላቸው አንድ ክፍል እንደደረሰን ነገርናቸው እንደጠበቅነው በደስታ ተሞሉና እቅፍ አደረጉን ወዲያውም አንድ በዕድሜ ገፋ ያሉ ለእኛ አዲስ የሆኑ መምህራችን ገቡ እኛም ተከትለናቸው ገብተን ተቀመጥን መምህሩም ራሳቸውን በደንብ ካስተዋወቁን በኋላ "እሺ ተማሪዎች አሁን ደግም አንድ በአንድ እየተነሳችሁ ስማችሁን አሳውቁኝ" አሉን ጥቂት ተማሪዎች ከተናገሩ በኋላ ተራችን ደርሶ ቢኒ ብድግ አለና "እሺ ቲቸር ቢኒያም ሳሙኤል እባላለሁ" ብሎ ቁጭ አለ ቀጣይ እኔ ስለነበርኩ "ሜሮን ሰለሞን" ብዬ ልቀመጥ ስል ቲቸር ወደ ሊዱ እያዩ "ካልተሳሳትኩ አንቺ ሊዲያ ሰለሞን? (ወደ ናሆሜ ዞር አሉና) አንተ ደግሞ ናሆም?" አሉት ሁላችንም ተገርመን እንደማፈር እያደረገን "አዎ ቲቸር" አልናቸው ቲቸርም በሙሉ ዕምነት "Ok ከእናንተ ብዙ እጠብቃለን" ብለውን ሄዱ እኛም ምንም ሳይሰማን ዝም አልናቸው ወዲያው ግን ሊያን ሳያት ወደኛ የነበራት አስተያየት ለየት ያለ ነበር ሰዐት ከሰዐት በቆጠሩ ቁጥር የምንማረውን ትምህርት ትተን ሀሳባችንና ትኩረታችን ሁሉ ጥምና እርካታን ወደሚሰጡን እነዚያ ዕፆች ነበር ታድያ ይሄ ነገር እኔን እየባሰብኝ መጣ ቁጭ ብዬ መማሩ ረፍት ነሳኝ ራሴን ከሚባለው በላይ ወጥሮ ያዘኝ ዝም ብዬ መምህሩን ለመከታተል ስሞክር ይባስ አይኖቼ ማየት እያቃታቸው በእምባ ተሞሉ እስኪብርቶዬን ቀና አድርጌ ልፅፍ ስል እጄ ፍፁም መታዘዝ አቃተው ሰውነቴንም በሀይል ያንቀጠቅጠኝ ጀመር. . .
. . . . . . ይቀጥላል
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.5K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 07:26:59
#የማለዳ_ቃል

" በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።"
-መዝሙረ ዳዊት 37: 3

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.7K viewsMeron, edited  04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 22:09:55 የኔ ጥያቄ?

አጥታችሁት ልትኖሩ የማትችሉት ማንን ነው??...................??????
እኔ ብዙ ነገር አጥቻለው ግን ደግሞ ያጣዋቸውም ሁሉ እኔን አላሳጡኝም
እየሱስ ከሌለኝ ግን መኖር ምችል አይመስለኝም....ኸረ አንደውም ከነጭራሹ አልኖርም...........እናንተስ ??????

እንኳን የእየሱስ ሆናችሁ!!

comment መስጫው ላይ ሀሳባችሁን አስፍሩት


ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
1.8K viewsMeron, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 07:57:15 ለካ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ የሚደጋግፈኝ
ለካ ፡ ይቅርታህ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ
ለካ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ የሚያጠነክረኝ
ለካ ፡ ክብርህ ፡ ነው ፡ ውበት ፡ የሚሆነኝ

ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ይልቅ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረት ፡ ያጠግበኛል (፪x)
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ሠላም ፡ ያሰጠኛል
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ፍቅር ፡ ያጠግበኛል
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ጤና ፡ ያሰጠኛል

በምን ፡ ቃል ፡ ልናገር ፡ በምን ፡ ቋንቋ ፡ ላውራከ
አይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x)

ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙም ፡ ሚለው ፡ ቃል ፡ ከገለጸው
የፍቅርን ፡ ብዛት ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እናገራለሁ
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙም ፡ ሚለው ፡ ቃል ፡ ከገለጠው
የስጦታን ፡ ብዛት ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እናገራለሁ

ለካ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ የሚደጋግፈኝ
ለካ ፡ ይቅርታህ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ
ለካ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው ፡ የሚያጠነክረኝ
ለካ ፡ ክብርህ ፡ ነው ፡ ውበት ፡ የሚሆነኝ

ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ይልቅ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረት ፡ ያጠግበኛል (፪x)
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ደስታ ፡ ያሰጠኛል
በምን ፡ ቃል ፡ ልናገር ፡ በምን ፡ ቋንቋ ፡ ላውራከ
አይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x)

ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙም ፡ ሚለው ፡ ቃል ፡ ከገለጸው
የፍቅርን ፡ ብዛት ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እናገራለሁ
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙም ፡ ሚለው ፡ ቃል ፡ ከገለጠው
የይቅርታን ፡ ብዛት ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እናገራለሁ

ለካ ምሕረትህ ነው
ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን(ሊሊ)

ለኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
sʜᴀʀᴇ sʜᴀʀᴇ sʜᴀʀ
◈ @CHRIST_TUBE ◈
◈ @CHRISTFAMILY ◈
2.0K viewsMeron, 04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 07:50:58
#የማለዳ_ቃል

" ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።"
-ትንቢተ ሆሴዕ 2: 16

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.7K viewsMeron, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 20:00:22 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=54
ሳባ ካሳሁን

ያልጠበቅነው ጭራሽም ያላሰብነው ነገር አየን መሀላቸው ያለችው ሰው ሊያ ነበረች ዐይኔ ያየውን መቀበል ሲያቅተኝ በፍርሀት ይዤው የነበረውን የናሆምን ኮት እጆቼ በመወዛገብ ዝለው ለቀቁት ሁላችንም በጥያቄ ተሞላን "ሊያ እዚህ ምን ታደርጋለች?" ብዬ ለማሰብ ሞከርኩ አፋችን ማውራት አቅቶት ተሳስሮ ሳለ በድንገት ሊያ ከት ብላ ደስ በሚል ግን በዚያ ሰዐት ላይ በሚያወዛግብ ሳቅ ሳቀችብን ከበዋት የነበሩ እኛንም መከራ ፍዳችንን ያሳዩን ከሊዱዬ ጋር ስንመጣ ያገኘናቸው ሰዎችም ድክም ብለው መሳቅ ጀመሩ በሰዐቱ "እኔ አብጄ ነው? ወይስ እነሱ?" ብዬ ይባስ ማሰብ እስኪያቅተኝ ግራ ተጋባሁ ሊያ ወደኛ ጠጋ አለችና ሰዎቹ ዞር እንዲሉ አደረገች የዚህን ጊዜ ሊዱም ልክ እንደነሱ እየሳቀች ድፍን ሀገራችን በሚያውቃት ፍልቅልቅነቷ ሮጣ መጥታ ተጠመጠመችብን ሁላችንም ልክ እንዳየናት ነገሩን መቀበል አቅቶን በመሬቱ ላይ ድፍት ብለን ተቀመጥን ሁኔታው እጅጉን ተወሳሰበብኝ ምንም ሳይቆዩ እነ ኬብሮን ሳሮንና በዚያ ቤት ውስጥ የለመድናቸው ፍቅራቸውን ወደን የተገዛንላቸው ልጆች እነሱም እየሳቁብን እያሽካኩ መጥተው ተቀላቀሉን። ህልም ወይ ቅዠት መስሎ የታየው ቢኒ ነገሩን መቀበል አቅቶት ከወደቀበት መሬት ብድግ እያለ "....አልገባኝም. .ምን እየተፈጠረ ነው?" ብሎ ሁሉንም በጥያቄና በመወዛገብ አስተያየት ተሞልቶ ጠየቃቸው ይህን ጊዜ ሊያ ደስ በሚል ፈገግታዋ ተሞልታ ጠጋ አለችውና "አይዟችሁ ጓደኞች ሁሉም ነገር ጨዋታ ነው ሁላችንም አቀናብረነው ነው ሀሳቡን እነ ሳሮን አመጡትና ሜሪን ልንወስዳት ስንል የላክነው ልጅ ስለማያውቃቸው ተምታተውበት ሊዱን አመጣት. . ብቻ ውዶች ሁሉንም ነገር በስልክ ቀድተነዋል ታዩታላችሁ!!" አለችን ሁሉም በእኛ መዝናናታቸውን አላቆሙም ነበር ናሆሜ እጅጉን በንዴት ተሞልቶ "ድንቄም ጨዋታ!!" አላቸውና ሊያያቸው እንደማይፈልግ እንደተበሳጨ ለማሳወቅ የኔንና የቢኒን እጅ ይዞ እንድንሄድ ጠየቀን።
ለመረጋጋት እየሞከርኩ ስለነበር ድርቅ ብዬ መሄድ እንደሌለብን አምኜ አሳመንኩት ሁሉም መደንገጣችንን ስላዩ እንድንረጋጋ ዝም ብለውን ለራሳቸው የቀረፁትን የድምፅ ቅጂ ማዳመጥ ጀመሩ በሰዐቱ እንዲህ ብዬ ተረዳሁት እንጂ ነገሩስ ሌላ ነው በመካከላችን ሰፋ ያለ ርቀት ነበር እነሱ በአንድ ቦታ ተሰባስበዋል እኛ አራታችን የአብርሀም በጎች ደግሞ በሀሳብ ተክዘን ማውራት አቅቶን ተቀምጠናል ሊያ ሀሳቧን በስልኩ ላይ የጣለች መስላ ትኩረቷ ግን በእኛ ላይ ነበር ድመት ዐይጥን ለማጥመድ አድፍጣ የምትጠብቀውን ያህል እሷም አይንና ጆሮዋን ወደኛ ቀስራ ተወጥራለች። ዝም ስንል ሊዱዬ ተቀይመን ያኮረፍናት መስሏት በእጆቿ ያዝ አድርጋን እየተንሰፈሰፈች "ጓደኞቼ በእውነት በእናንተ እምላለሁ እኔ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም ብቻ ግን ሰውዬው ይዞኝ ከወጣ በኋላ ከዚህ የባሰ በቅጡ እንኳን በር የሌለው በረጅም መስኮት ተዘሎ የሚገባበት ቤት አስገብቶኝ እዚያ ውስጥ ብዙ ከተቀመጥኩ በኋላ እነ ሊያ ሲጨቃጨቁ ድምፃቸውን ሰማሁና በተደጋጋሚ ስጣራ ሁሉም ተሰባስበው መጥተው ጨዋታ እንደሆነ ነገሩኝ ከዛ እንደማይሆንና እናንተ እንደምትጨነቁ ስለማውቅ ቶሎ ወደዚህ እንድንመጣ ነገርኳቸው" ብላ እየተቁለጨለጨች አየችን እኛም በእሷ ስለማንጨክንና ልናስጨንቃት ስላልፈለግን ጥያቄ ሳናበዛ ነገሩ ይበልጥ ግልፅ ሆኖልን ጨዋታ የተባለውንም ወጥመድ በተደፈነው አይናችን ጨዋታነቱን ብቻ አምነን ተረጋጋን ወዲያው ሊዱን እቅፍ አደረግናትና ዕርስ በዕርሳችን ያሳለፍነውን ያሰብነውን የቀባጠርነውን ሁሉ እያሰብን ከት ብለን መሳቅ ጀመርን ሊያም እየሮጠች ወደኛ መጣችና ". . .እ እናንተ ጉደኞች አሁን ተረጋጋችሁ?!" ብላ ያወራነውን ደግማ እየነገረችን ቀለደችብን ቀስ በቀስ ሁሉም መጡና እነሱም በእኛ እየሳቁ ተመልሰን ወደዚያ ቤት ደስታ ገባን በዚህ መሀል ሁላችንም በጣም የምንወደው ከመካከላችን በኮልታፋነቱ የሚታወቀው ምስኪኑ ጓደኛችን ሱራፌል ግን በፊቱ ላይ የሆነ መልዕክት ያሳውቀን ይመስል ዐይን ዐይናችንን እያየ በሀሳብ ተውጧል እኛ ግን በዙሪያችን ባለው ሆይታና ጫጫታ ተሞልተን እንደ መፅሀፈ ቅዱሱ ሳምሶን በብዙ ደሊሊዎች ተከበን ቀናት ቀናትን እያስቆጠሩ የዐይናችንን ዕይታ በአለም ነገር ላይ እንደተከልን ከፈጠረን በላይ ፍጡርን እያስቀደምን ፍቅርን ካስተማረን ይልቅ ፍቅር ናቸው ብለን ካመንናቸው እየዋልን፣ ካደግንበት ካሳደገን ክፉ ደግ ከተማርንበት መንፈሳዊ እህት ወንድም ከልብ የሆነ ትህትናን ከተማርንበት ሁሉ ነገራችን ከሆነው ቤተክርስትያን እየሸሸን የእነሱ ደስታ የእኛ መኖር፣ መልበስ፣ መደሰት መሳቅ የሆነው በእኛ ብዙ ነገር ያዩ ቤተሰቦቻችንን እየራቅን ለእኛ በጊዜው ደስታ መስሎ የታየንን ስናሳድድ የአለም ነገርን ክንፍ እስክንል እየወደድነው ክረምቱ አልቆ አዲሱ ዐመት ብቅ አለ ለብዙዎች ሌላ ተስፋ የሆነው መስከረም ጠባ።

ከዚህ ቀደም አዲስ ዐመት በመጣ ቁጥር ነጋ አልነጋ እያልን እንቅልፍ አጥተን መንጋቱን ለማየት የመኝታ ቤታችንን መስኮት አብዝተን እየተመለከትን ልክ ወፍ ሲንጫጫልን የለበስነውን ልብስ እንኳን ሳንቀይር በጉጉት እየፈነጠዝን ሁሌ ወደማንጠፋበት ቸርች እንሄድና የበዐሉ ፕሮግራም ገና ሳይጀመር ብርክክ ብለን ጌታን እንዲህ እንለው ነበር "አባታችን ሆይ በዐመታት ላይ ዐመታትን ጨምረህ እኛን ደግሞ ለዚህ ጊዜ አብቅተህ ይህን ቀን በሰላም እንድናይ ስለረዳኸን እናመሰግንሀለን ጌታ ሆይ ደግሞ በዚህ ዐመት በትምህርታችን ስኬታማ ሆነን አንተን ሀገራችንን ቤተሰቦቻችንን በኩራት የምናስጠራ ልጆችህ አድርገን አሜን!!" እንልና የልጅ ነገር ሆኖብን ተመልሰን ወደ ቤት ሄደን ድጋሚ ደሞ ለፕሮግራሙ እንመጣ ነበር። ዛሬ ያ ሁሉ ቀርቶ ዐላማችን ስኬታችን ሁሉ ተረስቶ መቃም ማጨስ መጠጣት ለእኛ normal ነገር ከሆነ ሰነባብቷል ሶሲ የተፈተነችው የማጠቃለያ ፈተና ውጤት መጥቶ በከፍተኛ ነጥብ ከትምህርት ቤታችን አንደኛ ሆና አለፈች እኛ ደግም ከነመፈጠር የዘነጋነውን ትምህርት የ12 ክፍል ተማሪዎች ሆነን ዛሬ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ እየተጣደፍን ነው. .
. . . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
2.0K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 07:24:20
#የማለዳ_ቃል

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15
51-52 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን።
53 ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
54 ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.3K viewsMeron, edited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 07:01:48 ....ሰዶም...
የህመም ሁሉ ህመም~የመንፈስ በሽታ
የድፍረት ሁሉ ድፍረት~የሀጥያት ከፍታ
        ጣርያ የነካ፥
                     በደልን ያለፈ፣
የእግዚአብሔርን ሕግ፥
                    ሰብሮ የተላለፈ
ሰውነት አስክዶ~ለአለም ያስሰለፈ፣
ሞትን የጎመራ_እሳት የወለደ
ሲኦልን የተባ_ሕይወት ያስቀጠፈ

ሀጥያተ ሰዶም ሕሊናን ያስተወ
ተጉዞዉ ተጉዞዉ ከ እንስሳ ያሳነሰ

መውጫ የለውም_የሰዶም በሽታ
ሀኪም አያየውም_በመመራመርያ

#ከሚመጣው_ጥፋት_ከሲኦል_መዳኛ
#እየሱስ_ብቻ_ነው_የነብስ_ማትረፊያ

              ፅኑ ፣ መሰረቱ ፣ አለት ፣ ባለ ዝና
              እየሱስ ይመጣል ፥ በአለም ፍፅምና።

    ታድያ ግን ወዳጄ !
አንተስ/ቺስ በምን ላይ ነህ ? ?

ልብስህንስ አጥበህ
   ለቀኑ ተዘጋጀህ ?
*  *  *  *  *  *  *  * 
          ተዘጋጅተሃል ወይ !

ለመሄድ ወደ ሰማይ...
....ወይስ ልትቀር ነው ?
ከመንግስተ ሰማይ

“እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።”
  — ይሁዳ 1
፥7

ሰዶም የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም።
@CHRIST_TUBE
@CHRIST_FAMILY
#ለእኔ_ሕይወት_ክርስቶስ_ነው።

#ተፃፈ_በአና_ንጉሴ
24/10/2015 ቅዳሜ 2:30am
Join our Tg&Y_T
Share Share Share
1.9K viewsAna, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 20:00:09 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=53
ሳባ ካሳሁን

ከወዲያ ወዲህ እጄን ሳወራጭ ሊዱዬ ቢኒና ናሆሜ የሉም በጣም ደነገጥኩ ሁኔታውን መቀበል እስኪያቅተኝ ሰውነቴ ከዳኝ ፍርሀት ውስጤን ረብሾት ማሰብ እስኪከብደኝ ተርበተበትኩ "ከኋላዬ የያዘኝ ሰው ምን አስቦ ነው? እነ ሊያ የት ናቸው? ምናልባት የቅድሞቹ ሰዎች ይሆኑ? አሁን ምን ልናደርግ ነው?" እያልኩ የጭንቀትና የድንጋጤ ዕምባዬን ማውረድ ጀመርኩ አፌንና እጄን ከያዘኝ በኋላ የትንፋሽ እንኳን ምንም አይነት ድምፅ በቤት ውስጥ አልነበረም። ሰከንዶች እየተዟዟሩ ደቂቃን በሰጡን ቁጥር ልቤም ፍርሀቱ እየጨመረበት አካሌ ከንቱ ሆኖ እየከበደኝ የታፈነ አፌ ለማውራት መታገሉ እየደከመው ሲመጣ ተስፋ ቆርጬ ሳለ ናሆም ከየት መጣ ሳልለው በለቅሶና በሲቃ ድምፁን ስስ አድርጎ "ሜሪ!! ሜሪ!! ቢኒዬ!! የት ናችሁ? ሜሪ!" እያለ መጣራት ጀመረ በዚህ ሰዐት ድምፁን ስሰማው በደስታ ጭላንጭል ተስፋ ብቅ አለልኝ በልቤ "እንዴ!! ናሆሜ!! ናሆሜ አለ ብቻዬን አይደለሁም!" ብዬ ድምፄን እንዲሰማውና መኖሬን እንዲያውቅ ያለ የሌለኝን አቅሜን እያወጣሁ የያዘኝን ጠንካራና ልረታው ያልቻልኩትን ግዙፍ ሰው በእግሮቼ እየተወራጨሁ "እም!! እም! እም!" እያልኩ መኖሬን አሳወኩት ነገር ግን ናሆሜ ፍፁም መልስ ሊሰጠኝ ካለሁበትም ዳስሶ ሊመጣ አልቻለም ይባስ ከፋኝ ማውራቴ ነፃነቴ ሳቄ ናፈቀኝ "ለምን ያዙን?? ለምን ተዘጋብን? ለምን ያሰቃዩናል?" እያልኩ ይበልጥ ማልቀሴን ቀጠልኩ ማውራት ብቻ ሳይሆን የሚያወራ ሰው አጓጓኝ "ምናለ ከኛ ምን እንደሚፈልጉ ቢነግሩን?" እያልኩ ዝምታን ጠላሁት በተደጋጋሚ የተዘጋው በር ሲከፈት ሰማለሁ የሚወጡና የሚገቡ ሰዎች ኮቴያቸው ያስታውቃል ሁኔታው እውነት እስከማይመስል ልጅ እያለን አስፈሪ ፊልም አይተን እንደሚያቃዠን ልክ እንደዛ የሚመስል አይነት ነበር።

በዚያ ክፍል ውስጥ እርግጠኛ የሆንኩበት ነገር እኔ በሰውየው መያዜን ብቻ ነው "ሊዱዬ የት ነች? ቢኒ የት ነው? ናሆሜ የት ገባ?" ላውቅ ብታገልም አልቻልኩም ከብዙ ዝምታ በኋላ አንድ ነገር ተፈጠረ ይኸውም የእልህ እልሁን ድርቅ ብሎ እጄን ወደኋላ ጎትቶ የያዘኝና አፌን በእጆቹ ለጉሞ ትንፋሼን ያመቀው ሰው ድንገት ወደ በሩ ወሰደኝ ልክ ስንደርስም በሩን በቀስታ ከፍቶ በፍጥነት ወጣ ከሁሉ በፊት ድንጋጤዬ ስላለቀቀኝ ለደቂቃዎች አፍኖት በነበረው አፌ ለጉድ እያለከለኩ ብርሀን አሳይቶኝ ድጋሚ የነሳኝን የተዘጋውን በር እየደበደብኩ በእምባ ስቃይ ተሞልቼ "እርዱኝ!! እርዱኝ!! ሰው የለም?!! እባካችሁ ጓደኞቼን አገናኙኝ እባካችሁ!" እያልኩ በበሩ ላይ ድፍት ብዬ ቀረሁ ይህን ጊዜ ከቤቱ ጥግ ጋር አንድ ልክ እንደኔ አፉ የተለጎመ ማውራት እየፈለገ በእምባ የተሞላ የእኔን እርዳታ ወይ ለኔ መከታ ሊሆን የሚፈልግ አንድ ሰው ድምፁን አሰማኝ እኔም በጣም ደንግጬ በመሬቱ ላይ እየተንፏቀቅኩ ሄጄ ከአጠገቡ ደረስኩ በቤቱ ጭራሽም ብርሀን ስላልነበር ፍፁም መለየትና ማወቅ ከበደኝ እሱ ግን የታፈነ ድምፁን ማሰማቱን አላቆመም ወደሱ እየቀረብኩ "ማነህ? ማነህ? እጄን ያዘኝ" እያልኩ እጄን ስዘረጋለት ያዝ አደረገኝና አፉ ላይ እንዳያወራ የታሸገውን ትልቅ ላስቲክ አስነካኝ አሁንም መርበትበቴን ላቆም አልቻልኩም "እሺ! እሺ አስረውህ ነው? ቆይ! ቆይ አንዴ" ብዬ እየተንቀጠቀጥኩ ላስቲኩን በዳበሳ አነሳሁለት ልክ እሱም እንደኔ በሀይል እየተነፈሰ "ሜሪዬ!!" አለኝ ይህን ጊዜ ከልቤ ተደሰትኩ ከአራታችን አንዱ መከታችንን ቢኒን አገኘሁት በደስታ ተሞልቼ "ቢኒዬ አለህ? አንተ ነህ?" እያልኩ አቀፍኩት እሱም ደስ ብሎት እምባውን እየጠራረገ "አለሁ አለሁ" አለኝ በመሀል ግን አንድ ሌላ የእርዱኝ ወይ አለሁኝ የማያ ሳይሆን የድካምና የህመም የሚመስል ድምፅ የቱ ጋር እንደው በማናውቅበት ቦታ ሰማን አሁንም በድንጋጤ ሁለታችንም በመሬቱ ላይ ተንበርክከን እየተንፏቀቅን ድምፁን ላሰማን ሰው ልንደርስለት በተለያየ አቅጣጫ መፈለግ ጀመርን ብዙም ሳይቆይ ቢኒ በጣም ጮክ ብሎ "ሜሪ ሜሪ ይኸው እዚህ ጋር አገኘሁት ናሆሜ ነው! ሜሪ ናሆሜ ነው!! ናሆሜ ናሆም ናሁዬ" እያለ ጠራው ድምፁ ወደሚሰማኝ እየሮጥኩ ሄጄ ስጠጋቸው ናሆሜም ልክ እንደኛ አፉ ተሸፍኖ የትግል ድምፅ ማውጣቱ ልቡን አድክሞት ተስፋ ቆርጦ ወድቋል እግራችን ላይ ጭንቅላቱን ዘመም አድርገን ደጋግመን ስንጠራው የእኛን መምጣትና የአፉን መፈታት ያላመነው ጓደኛችን ቀና ብሎ "መጣችሁልኝ? ጓደኞቼ!!" ብሎ በግራና በቀኝ እቅፍ አደረገን ወዲያው ግን ፀጉሬን መደባበስ ጀመረ ከጠዋት ጀምሮ በገጠሙን ነገሮች ግን ልስት የነበረው ራሴን መቆጣጠር ስላቃተኝ ሁኔታውን አላስተዋልኩም ናሆሜ በቅፅበት ተስፈንጥሮ ተነስቶ "እንዴ! እንዴ ሊዱስ! የታለች?" አለን ይህን ቃሉን ስሰማ ሰማይ ከምድር ተደባልቆ ነውጥ የተነሳ ያህል ልክ እንደዛ ጭንቅላቴም ሊፈነዳ ያህል ተሰማኝ በጭለማ ውስጥ ለኛ ብርሀንን የምትሰጠን ቡቻዬን የት ረሳናት? ማሰብና ማስተዋል ተሳነኝ. ራሷን ስታ ይሆን? ድንገት ተነስቶ ምጥ የሚሆንባት የልቧ ህመም አገኛት ይሆን? ብዬ እግሮቼ መሄድ እስኪያቅታቸው ተሳስረውብኝ በእንብርክክ አልቆም ባለው እምባዬ እየተንሰቀሰኩ እንደእብድ ወለሉን ስዳብስ ናሆምና ቢኒ እየተዘዋወሩ ስሟን ደጋግመው እየጠሩ በጭለማው ዕርስ በዕርሳቸው እየተጋጩ ሲፈልጓት ግን ሊዱ ዬን ፍፁም ልናገኛት አልቻልም በቤቱ ውስጥ እንደሌለች ካወቅንም በኋላ ቢኒ "ሊዱ ዬ ቀልድ ነው በይኝ አለሁላችሁ በይን!" እያለ በለቅሶ ቢለምናትም "አቤት ወዬ መጣሁላችሁ" አላለችንም አሁን ይበልጥ ነገሩ ተወሳሰበብኝ የጠዋቱን ነገር አሁን ካለንበት ነገር ጋር ሳገጣጥመው በፍርሀት ተወረርኩ ልክ እንደ አንድ "በቃ ለየለት" እንደሚባል ሰው በቤቱ ጠርዝ ጋር ሽጉጥ ብዬ ዐይኔን ግድግዳ ላይ እንደተከልኩ ደርቄ ቀረሁ ናሆምና ቢኒ ግን በሀይልና በጩኸት "ሊዱን ልቀቋት!! ወንድነት ካላችሁ ኑ እኛን ውሰዱን!! አንድ ነገር ብትሆን ከፀጉሯ አንዲት ዘለላ ብትነካ አንለቃችሁም!!" እያሉ በተደጋጋሚ ሳይሰለቹ በሩን እየደበደቡ ተናገሯቸው።
ነገሩን እንዲህ ጀመሩልን የነቢኒን ማቆሚያ የሌለው ጩኸት የታከታቸውና እልህ ውስጥ ያስገባቸው ይመስሉ ነበር የእኔ ዝምታ ሲያስጨንቃቸው እነ ናሆሜ ቀረብ ብለውኝ ሊያበረቱኝ እየሞከሩ ሳለ ለሰዐት የተዘጋብን በር ተበረገደ ሆን ተብሎ ይመስል ብርሀኑ እጅጉን ሀያል ነበር ሁላችንም ዘለን ተነስተን ወደ ውጪ ለማየት ስንሞክር ስንመጣ አግኝተናቸው የነበሩት እነዚያ ትላልቅ ልጆች መሀላቸው ሌላ አንድ ሰው አድርገው ወደኛ መጡ ልቤ በጣም እየፈራ ምቱ እየጨመረ የናሆሜን ኮት አጥብቄ ያዝኩትና በጉጉት እጠብቅ ጀመር ልጆቹ ወደኛ እየተቃረቡ አጠገባችን ሊደርሱ ትንሽ ሲቀራቸው ፍፁም ያልጠበቅነው ጭራሽም ያላሰብነው ነገር አየን መሀላቸው ያለችው ሰው ሊያ ነበረች. . .
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
2.0K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ