2022-08-21 13:40:48
#የዐስር_ሶላት_በዕዲያ
እናታችን ዐኢሻ رضي الله عنها እንደተናገረችው
"ነብዩ صلى الله عليه وسلم ከፈጂር በፊት ያሉትን ሁለት ረከዐዎችና ከዐስር በኋላ ያሉትን ሁለት ረከዐዎች አያሳልፉም ነበር።''
በሌላ ሀዲስ ላይም ስለነብዩ صلى الله عليه وسلم የሱንና ሶላት አሰጋገድ ሁኔታ ስትጠየቅ
ዙህርን ከሰገዱ በኋላ ሁለት ረከዐዎችን ይሰግዳሉ። ቀጥለውም ዐስርን ከሰገዱ በኋላ ሁለት ረከዐዎችን ይሰግዳሉ ብላ መልሳለች። በዚህ ሀዲስ መሰረት ከዐስር ሶላት በኋላ የሚሰግዷቸው ሁለት ረከዐዎች ቀዷእ እንዳልሆኑ መረዳት ይቻላል። ኡመርኮ رضي الله عنه ከዐስር ሶላት በኋላ ሱንናዎችን የሚሰግዱን ሰዎች ይመታቸው ነበር የሚል ተቃውሞ ሲቀርብባት ዑመር የከለከለው ሰዎች ከዐስር ጀምረው ጸሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ እየሰገዱ ስላስቸገሩት ነው። በርግጥ ዑመር ይሄን ማድረጉ ትክክል ነው ብላለች ዐኢሻ رضي الله عنها
ይሄንን ሱንና በርካታ ሰለፎችም ይፈጽሙት እንደነበረ ኢብኑ አቢ ሸይባ በሙሰነፋቸው ላይ አስፍረዋል። ከነዚያም ውስጥ
ዐምር ቢን መይሙን
አቡ ቡርዳ
አስወድ ቢን የዚድ
አቡዋኢል
መስሩቅ
ሙሀመድ ቢን አል ሙንተሺር
ጧውስ
ከሰሀቦችም ውስጥ ዐኢሻ፣ ዐሊይ፣ አነስ ፣አቡ አዩብ እንድሁም ኢብኑ ዑመር ከዐስር ሶላት በኋላ ሁለት ረከዐ ሱንና መስገድ ሱንና እንደሆነ ይገልጻሉ። ከፊሎቹም ይሰግዳሉ።
ዐሊይ ባስተላለፈውና ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይም "ከዐስር ሰላት በኋላ ምንም አይነት ሶላትን አትስገዱ፣ ጸሀይዋ ከፍ እስካለች ድረስ ከሆነ እንጅ" ብለዋል።
ይህች ሱንና የነብዩ ብቻ መለያ ሱንና ነች የሚሉ ዘገባዎች ቢኖሩም ግን ለመረጃነት ብቁ አይደሉም። በተጨማሪም ብዙ ሰሀባዎች ይችን ሱንና በቋሚነት ያልፈጸሟትም ነብዩ صلى الله عليه وسلم አዘውትረው የሚሰግዷት ቤት ከመጡ በኋላ በመሆኑ ነው። እንዳውም ለምን የዐስርን በዕዲያ ሱንና መስጂድ እንደማይሰግዷት ሲጠየቁ ኡማዎቼ እንዳይከብዳቸው ከመስጋት ነው የሚል ይዘት ያለውን ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ እይታ የዘመናችን ምሁራኖች ያመጡት አዲስ እይታ ሳይሆን ጥንትም የነበረ ግን ደግሞ እኛ የተላመድናቸው መሻይኾች በግልጽ ያወጡት የፊቅህ እይታ ነው። እንጂማ ሀዲሶቹን አልባኒ ብቻም ሳይሆን ቀደም ያሉት የሀዲስ ሊቃውንቶች እንደ አል ኢራቂይ ኢብኑ ሀጀር ሶሂህ ብለዋቸዋል።
ከመዝሀብ መሪዎችም ውስጥ ኢማሙ አህመድ ይህችን ሱንና አይቃወሙም ነበር።
ስለዚህ ይሄን ሱንና መተግበር የተረሱ ሱንናዎችን ህያው ማድረግ ነው። ባይሆን ግን ይህ ሱንና የሚተገበረው ጸሀይዋ ቀለሟን ወደቢጫነት ከመቀየሯ በፊት ነው።
T.me/telkhis
993 views10:40