2022-08-08 10:37:27
አብዛኛዎቹ ሙስሊሞች
ከወለደች ሚስት (ከአራስ) ጋር ግንኙነት መፈጸም የሚቻለው ከ40 ቀን በኋላ ነው ብለው ነው የሚያስቡት። ነገሩ ግን እንደዚህ አይደለም ወዳጆቼ።
ቢበዛ ቢበዛ የመጨረሻ ቢዘገይ 40 ቀን ሊጠብቁ ይችላሉ ማለት እንጂ ጉዳዩ የሚገናኘው ከወሊድ ደም ፍሰቷ ጋር ብቻና ብቻ ነው።
እንደወለደች ወዲያውኑም ይሁን በ3ኛ ቀኗ ደም የሚባል ነገር ካቆመላት ሶላት መስገድ አለባት።
አቅማቸውን ባማከለና ጉዳት በማያስከትል መልኩ የወሊድ ደሟ በቆመበት ጊዜ ከተጣጠበች በኋላ ግንኙነቱንም መጀመር ይችላሉ። ቀኑ ደግሞ ከተመቻቸው በወለደችበትም እለት ሊሆን ይችላል፣ በ3ኛውም፣ በ10ኛውም፣ በ20ኛውም፣ በ30ኛውም ቀን ሊሆን ይችላሉ። ደሙ ሳያቆምላት ከ40 ቀን ካለፈ ግን በ40ኛው ቀኗ ተጣጥባ ደም እየፈሰሰም ግንኙነት መፈጸም ይችላሉ።
ይሄ ነውር አይደለም። ሀራምም ይሁን የተጠላ ተደርጎ አይወሰድም።
T.me/telkhis
865 views07:37