Get Mystery Box with random crypto!

Telkhis (هذه عقيدتنا)

የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا) T
የቴሌግራም ቻናል አርማ telkhis — Telkhis (هذه عقيدتنا)
የሰርጥ አድራሻ: @telkhis
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.09K
የሰርጥ መግለጫ

((( @IbnusirajBot )))

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-07-17 20:01:16 አስተውሉ:
ሰጋጆች ሲሰግዱ ምቾት ሊያገኙ ይገባቸዋል። ስለዚህ ሶፍ ላይ ጥብቅብቅ ብሎ መስገድ ስህተት ነው። አንዳንዴ ከፊታችን ካለ ሶፍ ላይ ትንሽ ክፍተትን ስላየን ብቻ ሰዎችን በመገፋፋት ለመግባት መሞከር የነብዩን صلى الله عليه وسلم ምክር ይጻረራል። ትከሻችሁ ከአጠገባችሁ ለሚሰግዱ ሰዎች የሚመቹ ይሁኑ የሚል ይዘት ያለው ሀዲስን ነብዪ صلى الله عليه وسلم አስተላልፈዋል።

T.me/telkhis
235 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 19:19:05 ሜሴጅ ከላካችሁ በኋላ (በተለይም በሜሴንጀር፣ ዋትሳፕ እና ኢሞ) የተላከለት ሰው ሳያነበው አትደልቱ። ይህ አደብ አይደለም። ምናልባት መደለት ያለበት ሀሳብ ከሆነ ደግሞ የደለታችሁበትን ምክንያት ከስር አስፍሩ።
ሸይጧን በሰዎች የደም ስር ዘልቆ ይገባልና እንድህ አይነት ድርጊቶች ሜሴጅ በተላከለት ሰው ዘንድ መጥፎ ጥርጣሬንና አለማመን ይፈጥራሉ።
ስለዚህ:
ይቅርታ በስህተት ስለላኩት ነው የደለትኩት። ይቅርታ ህጻናት ነበሩ የላኩብኝ።
ይቅርታ የደለትኩት ጽሁፌ የአጻጻፍ ስህተት ስለነበረው ነው ብላችሁ አሳውቁ።

የተጻጻፋችሁትን ሜሴጆችም ከመደለታችሁ ወይም unsent ከማድረጋችሁ በፊት
ማጥፋት እንደምትፈልጉ አሳውቁ።
294 views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 11:23:04 ልዩ የስልጠና እና የስራ ዕድል!
***
ለወጣት ሙስሊም ወንዶችና ሴቶች የተዘጋጀ ልዩ የስልጠናና የስራ ዕድል...
***
በካሜራ ማንነት
በኦድዮ ቪዝዋል ኤዲቲን
በመድረክ አስተዋዋቂነት ስልጠና መውሰድ እና ወደ ኢስላማዊ ሚድያዎች በመቀላቀል ታሪካዊ አሻራ ማሳረፍ ለምትፈልጉ ወንድምና እህቶች የቀረበ ልዩ ዕድል::

በሁሉም ዘርፍ ብቁ ባለሙያዎችን ማብቃት ስለምንፈልግ መቀበል የምንችለው ውስን ሰልጣኞችን በመሆኑ በሶስቱም ሙያ መሰልጠን የምትፈልጉ የትምህርት ዝግጅቱ ያላችሁም ይሁን ችሎታው አለኝ ብላችሁ እምታስቡ ወጣቶች አሁኑኑ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ::

https://t.me/Zawyaacademy ላኩልን::
ሙሉ መረጃችሁን በተጠቀሰው የቴሌግራም አድራሻ ብቻ ላኩልን:: በአካል የሚቀርብ ማመልከቻን አንቀበልም::
*መላክ ያለባችሁ መረጃ*
ሙሉ ስም:-
ዕድሜ:-
ከሙያው ጋር ያላችሁ ልምድ:-
በሙያው የወሰዱት ስልጠና ካለ:-
የመኖርያ አድራሻ:-
ስልክ:-
# ማስታወሻ :- በውስጥ የምትልኩት
https://t.me/Zawyaacademy
መረጃውን ብቻና ብቻ መሆን አለበት::

# ማሳሰቢያ :- ይህ የስልጠና ዕድል በተጠቀሱት ሙያዎች መዝለቅ ለሚያስቡ እንጂ
በትርፍ ሰዓታቸው ለሚሰሩ አልያም ለአጭር ጊዜ መስራት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ
አይደለም:: የስራ ምደባው በዛውያ ቲቪና ሌሎች የሚድያ ባለሙያ ዕጥረት ባለባቸው የሙስሊም ሚድያዎች ላይ ይሆናል::
ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!
489 views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 07:34:32 ሁለት ሶስት ጊዜ መክረኸው ሊቀየር ያልፈለገን ሰው ደጋግመህ እመክራለሁ ስትል የኢኽላስህን ጉዳይ እንዳትዘነጋ። በብዛት ተደጋጋሚ ወቀሳዎችና ምክሮች
* ራስን መኮፈስ
* ስህተት ላይ ነው ብለን ያሰብነውን ሰው
ማናናቅ
* እንዴት ምክሬ አልተሰማም የሚል አመለካከት ይፈጠርብህና ወንጀለኛ እንዳትሆን መጠንቀቅ ያሻል።
441 views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:48:24 እዚያ ፈጥነህ ማረፍ ከፈለግክ እዚህ አትዘግይ።

ከውድድር ውጭ አትሁን። በውድድሩም ከመጨረሻው እርከን መሆን እንደሌለብህ አትዘንጋ።

" ስራው ያዘገየው ቤተሰቡ አያፈጥነውም" ተብሏል።
182 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:08:25 ዒድ እንደማንኛውም ቀን አይደለም። ቀኑ ዉብ ነው። ደስታውም ብዙና ረጂም ነው። ከዋዜማው ጀምሮ በደስታና በናፍቆት የተሞላ ቀን ነው። ከተለመደው ቀን የተለዬ በሚመስል መልኩ ጸሀይዋ ብሩህ ናት፣ አየሩ ምቹ ነው፣ ሌሊቱም የተለዬ ሰላም ያለው ይመስላል። በርግጥ ቀኑ እንዳለፈው ቅዳሜ ወይም እሁድ ነው። ቀኑ አልተለየም። የዛሬውን ቅዳሜ በተመለከተ ያለን አመለካከት ግን ተለይቷል። የዛሬው ቅዳሜ/ እሁድ ልዩ የደስታ ቀን እንደሆነ ልባችን በጽኑ ያምናል። ያ እምነታችን ነው ቀኑን ዉብ ያደረገው። በዒድ ቀን ሀሳቦቻችንንና ፈተናዎቻችን ራቅ እናደርጋለን። በዒድ ቀን ሀዘናችንን እና የውስጥ ህመማችንን ዋጥ አድርገን ፈገግታችንን እና ሳቃችንን ብቻ ለሰዎች እናጋራለን። ለዚያም ነው ዒዱ የደስታ ቀን የሆነልን።

ወዳጆቼ ሆይ!!
ሁሌም ደስ ይበላችሁ፣ ሁሌም እንደ ዒድ ይሁን ኑሯችሁ።

عيد مبارك تقبل الله ومنكم صالح الأعمال


እኛም የዛሬውን ጾማችንን አላህ ይቀበለን። የነገ ሰው ይበለን።
483 views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 00:30:57 ዒዳችሁ ነገ ቅዳሜ የሆነ ሁሉ:

ዒዱኩም ሙባረክ
ተቀበለሏሁ ሚንኩም ሷሊሐል አዕማል


በሰላም፣ በጤና እና በኢማን ደጋግማችሁ የምታከብሩት ያድርጋችሁ
457 views21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:59:00 ዐረፋን ቀን መጾምን እንዳንዘነጋ።

የዐረፋ ቀን ጾም የባለፈውንና የቀጣዩን አመት ኃጢያቶች የሚያስሰርዝ ጾም እንደሆነ በነብዩ صلى الله عليه وسلم ተነግሮናል።
590 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:31:14
750 views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 23:27:40
ሸይኽ ኑረይን
1.2K views20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ