Get Mystery Box with random crypto!

ዒድ እንደማንኛውም ቀን አይደለም። ቀኑ ዉብ ነው። ደስታውም ብዙና ረጂም ነው። ከዋዜማው ጀምሮ በደ | Telkhis (هذه عقيدتنا)

ዒድ እንደማንኛውም ቀን አይደለም። ቀኑ ዉብ ነው። ደስታውም ብዙና ረጂም ነው። ከዋዜማው ጀምሮ በደስታና በናፍቆት የተሞላ ቀን ነው። ከተለመደው ቀን የተለዬ በሚመስል መልኩ ጸሀይዋ ብሩህ ናት፣ አየሩ ምቹ ነው፣ ሌሊቱም የተለዬ ሰላም ያለው ይመስላል። በርግጥ ቀኑ እንዳለፈው ቅዳሜ ወይም እሁድ ነው። ቀኑ አልተለየም። የዛሬውን ቅዳሜ በተመለከተ ያለን አመለካከት ግን ተለይቷል። የዛሬው ቅዳሜ/ እሁድ ልዩ የደስታ ቀን እንደሆነ ልባችን በጽኑ ያምናል። ያ እምነታችን ነው ቀኑን ዉብ ያደረገው። በዒድ ቀን ሀሳቦቻችንንና ፈተናዎቻችን ራቅ እናደርጋለን። በዒድ ቀን ሀዘናችንን እና የውስጥ ህመማችንን ዋጥ አድርገን ፈገግታችንን እና ሳቃችንን ብቻ ለሰዎች እናጋራለን። ለዚያም ነው ዒዱ የደስታ ቀን የሆነልን።

ወዳጆቼ ሆይ!!
ሁሌም ደስ ይበላችሁ፣ ሁሌም እንደ ዒድ ይሁን ኑሯችሁ።

عيد مبارك تقبل الله ومنكم صالح الأعمال


እኛም የዛሬውን ጾማችንን አላህ ይቀበለን። የነገ ሰው ይበለን።