2022-08-11 17:25:26
ሙጚስ እና በሪራ رضي الله عنهما ሁለቱም ባሪያዎች ነበሩ። በትዳር ተጣምረው በፍቅር ተሳስረውም ይኖሩ ነበር። ኋላ ላይ ግን በሪራ ከባርነት ቀንበር ቀደም ብላ ነጻ ወጣች። እንደሚታወቀው ሁለት በባርነት ላይ ሳሉ የተጋቡ ባለትዳሮች አንዳቸው ቀድመው ከባርነት ነጻ ከወጡ ትዳራቸውን የማፍረስ መብት ተሰጥቷቸዋል። እናም በሪራ ቀድማ ነጻ ስትወጣ ሙጚስን አልፈልግህም አለቺው። ሙጚስ ደግሞ ልቡ ውልቅ እስከሚል ነበር በሪራን የሚያፈቅራት። ያለ የሌለን ሽማግሌ እየላከ አስለመናት። በሪራ ግን አሻፈረኝ አለች። ሽምግልናው ነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘንድ ደረሰ። ነብዩም ለሙጚስ ሽማግሌ ሆነው ከበሪራ ዘንድ ሄዱ። አብራችሁ ኑሩ ብለው መከሯት። ያረሱለሏህ ትእዛዘዎ ነው? ብላ ጠየቀች። አይ ትእዛዝንኳ አይደለም። ሽምግልና ነው ብለው መለሱ። እንግዳውስ ሽምግልና ከሆነ ሙጚስን አልፈልገውም ብላ የነብዩንም ሽምግልና አሻፈረኝ አለች። ነብዩም صلى الله عليه وسلم ሽምግልናቸውን ስለመለሰች አልወቀሷትም። አልተቀየሙባትም።
ስለዚህ
1- ለምን እንደተወችው ሳታውቁ እንደዚያ የሚያፈቅትን ባሏን እርግፍ አድርጋ ተወችው፣ የእሷማ ግፍ የተለዬ ነው አትበሉ። ነብዩ በሪራን እንድህ እንስፍስፍስ ብሎ የሚያፈቅርሽን ባልሽን እንዴት ትተይዋለሽ ብለው መች ወቀሷት። ለምን እንደፈታት በትክክል ሳትረዱ (ብትረዱም ጭምር) እሷ አፈቅረዋለሁ ስላለች ብቻ እሱን አትውቀሱ።
2- ሽምግልና ሞክራችሁ ካልተሳካ ንቀውኝ ነው አይደል አትበሉ። የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሽምግልና መች ተሳካ። አንተ ከነብዩ በላይ የምትከበር ሰው ነህ እንዴ?
3- ለመለያየት መበዳደልን መናገር ግዴታ አድርጋችሁ አትውሰዱ። በሪራ ምን በደል ደርሶብኛል ብላ ተፈታች?
4- ሽምግልና ታላቅ ዒባዳ መሆኑን አትዘንጉ፣ አጅሩም ከሽምግልናው ዉጤት ጋር የተሳሰረ አይምሰላችሁ። ዉጤቱ ምንም ይሁን ምን ሞክሩ። አጅሩ አይቀርባችሁም።
5- ሸሪዐዊ ትእዛዝት በሙሉ የሚገድባቸው መረጃ እስካልተገኘ ድረስ መሰረታዊዉ መነሻ መርሃቸው ግዴታነት እንደሆነም እወቁ። በሪራ رضي الله عنها "ያረሱሉሏህ ትእዛዘዎ ነውን"?? ብላ ስትጠይቅ አዎ ትእዛዝ ነው ቢሏት ኖሮ ያለምንም ማንገራገር ቀጥ ብላ ከሙጚስ ጋር ልትኖር ነበርኮ።
(شرح خلاصة قواعد الأصولية)
እናንተም ጨማምሩበት።
T.me/telkhis
689 views14:25