Get Mystery Box with random crypto!

የትኛውም ቦታ (ብቻህን ስትሰግድም ይሁን ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር ስትሰግድ) አዛንና ኢቃማ ማለትን አ | Telkhis (هذه عقيدتنا)

የትኛውም ቦታ (ብቻህን ስትሰግድም ይሁን ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር ስትሰግድ) አዛንና ኢቃማ ማለትን አትዘንጋ። ግዴታ አይደለም ቢባልን እንኳ ተወዳጅ ተግባር መሆኑ ግን አሳማኝ ነው።

መስጂድ ስትገባ ሰጋጆቹ ተበትነው ብታገኛቸውና መስጂድ መስገድ አለብኝ ብለህ ካመንክ አዛን እና ኢቃማ አድርገህ ብቻህን ስገድ። ይህ ነው በላጩ አሰጋገድ። አዛን እና ኢቃማ የማድረግን አጂር ታገኛለህ።

ኢብኑ አቢ ሸይባና ኢብኑ ሙንዚር በትክክለኛ ሰንሰለት እንደዘገቡት
አነስ رضي الله عنه መስጂድ ሲገባ ተሰግዶ ስላገኘ አዛን እንድያደርጉለት አዘዘ ከዚያም ኢቃማ አስደረገና አብረውት የነበሩትን ባልደረቦቹን አሰገዳቸውም።

(ሸይኽ አልባኒ ብቻውን በሚሰግዱ ሙስሊም ላይ ሳይቀር አዛን ግዴታ ነው ይላሉ።)

T.me/telkhis