Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሰው አባቱን በመካድና በመራቅ እስካልሆነ ድረስ ወደእናቱ ተጠግቶ መጠራቱ ሀራም አይሆንም። | Telkhis (هذه عقيدتنا)

አንድ ሰው አባቱን በመካድና በመራቅ እስካልሆነ ድረስ ወደእናቱ ተጠግቶ መጠራቱ ሀራም አይሆንም።

በርካታ ሶሃባዎች በእናታቸው በኩል ይጠሩ ነበር። ነብዩም صلى الله عليه وسلم ስማችሁን አስተካክሉ ብለው አላረሟቸውም። እንዳውም እርሳቸውም በእናታቸው ስም ይጠሯቸው ነበር።
ከታች ያሉት በአባት ስም ቦታ የእናታቸውን ስም ተጠቅመው የሚጠሩ ሶሃባዎች ነበሩ።

ዐብዱላህ ቢን #ኡሚ_መክቱም
ኢብኑ #ቡሀይናህ
ሀሪስ ቢን #በርሷእ
የዕላ ቢን #ሙንያህ
رضي الله عنهم

ስለዚህ
ሙሀመድ ሰዒድ
ሙሀመድ ፋጢማ
በሁለቱም መጠራት ወይም መጥራት ሀራም አይደለም። አደቡ ግን ወደአባት መጠጋቱ ነው ይላሉ ብዙዎቹ።

T.me/telkhis