Get Mystery Box with random crypto!

#እንድህም_አለ የሌሊትም ይሁን የቀን የሱና ሶላቶችን በእያንዳንዱ ሁለት ረከዓ ላይ እያሰላመቱ መ | Telkhis (هذه عقيدتنا)

#እንድህም_አለ

የሌሊትም ይሁን የቀን የሱና ሶላቶችን በእያንዳንዱ ሁለት ረከዓ ላይ እያሰላመቱ መስገድ በጣም በላጩ እና አዘውትረን ልንተገብረው የሚገባ ነብያዊ ሱንና ነው።

ሆኖም ግን አራት ረከዓዎችን አያይዞ መስገድም ይቻላል። ወንጀለኛ አያስደርግም። ሶላቱም ውድቅ አይሆንም። ምክንያቱም ቲርሚዚይ በዘገቡትና ሸይኽ አልባኒ ሐሰን የሚል ደረጃን በሰጡት ሀዲስ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ከዐስር ሶላት በፊት አራት ረከዓን በአንድ ላይ አያይዘው ሰግደዋል። በመካከል ላይ አተሂያቱን በመቅራት ነው የሰገዱት። ይህም ማለት የሱንናውን ሶላት ልክ እንደ ዐስር ሶላት አስመስለው ሰግደዋል ማለት ነው።

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ እናታችን ዐኢሻም رضي الله عمها ስለነብዩ የሌሊት ሶላት አሰጋገድ ስትገልጽ 4 ረከዓዎች ይሰግዳሉ። ስለማማራቸውና ስለ አረዛዘማቸው አትጠይቀኝ (በጣም ዉብ ሶላቶች ናቸው።) ከዚያም ሌላ ተጨማሪ ያማሩና ረጂም ጊዜ የወሰዱን 4 ረከዓዎችን ከሰገዱ በኋላ ዊትራቸውን 3 ረከዓ ጨምረው ያጠናቅቃሉ ብላ ተናግራለች። ይህን ሀዲስ ምንም እንኳ ብዙሀኑ ምሁራኖች ዐኢሻ رضي الله عنها አራቱን በአንድ ላይ የጠቀሰችው በየአራት ረከዐዎቹ ላይ ረፍት ስለሚያደርጉ ነው በሚል ቢተረጉሙትም ሀዲሱን በቀጥታ ትርጉሙና በግልጽ መልእክቱ ስንረዳው ግን ነብያችን صلى الله عليه وسلم አራቱንም ረከዓ አያይዘው ይሰግዱ እንደነበር ጠቋሚ ነው። ይህ የሀነፊያዎችን የከፊል ሰለፎች ምርጫ ነው።

T.me/telkhis