Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-18 15:06:15
ዴይስቶቹ ዴይዝም (Deism) በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው ግንኙነት "በመገለጥ" (Revelation) ላይ ሳይሆን "በአመክንዮ" (Reason) ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብሎ የሚያምን  በዘመነ "አብርሆት" (enlightenment) የምዕራቡን ዓለም አስተሳሰብ ቅርፅ ያስያዘ "ሃይማኖት ቅብ" ፍልስፍና ነው። የፍልስፍናው ተከታዮችም በስነ መለኮት ምሁራኑ ዘንድ "ዴይስቶች" ተብለው ይጠራሉ። …
2.5K viewsΒενιαμίν, 12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 15:06:04 ዴይስቶቹ

ዴይዝም (Deism) በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው ግንኙነት "በመገለጥ" (Revelation) ላይ ሳይሆን "በአመክንዮ" (Reason) ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብሎ የሚያምን  በዘመነ "አብርሆት" (enlightenment) የምዕራቡን ዓለም አስተሳሰብ ቅርፅ ያስያዘ "ሃይማኖት ቅብ" ፍልስፍና ነው። የፍልስፍናው ተከታዮችም በስነ መለኮት ምሁራኑ ዘንድ "ዴይስቶች" ተብለው ይጠራሉ።

ታዲያ ዴይስቶቹ ትምህርታቸውን የሚጀምሩት "አፅናፈ ዓለሙን የፈጠረው ፈጣሪ አለ" ብለው ነው። ነገር ግን "ይህ ፈጣሪ መላለሙን ከፈጠረ በኋላ የፈጠረውን ፍጥረት በሙሉ "ለተፈጥሮ ህግጋት" አሳልፎ ሰጥቶታል። ስለዚህ ፈጣሪ በዕለት ተዕለትም ሆነ በአጠቃላዩ የሰው ህይወትና ኑሮ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የሰውን ህይወት አይመራም አይቆጣጠርም። ፍጥረተ ዓለም የሚተዳደረው በራሱ "የተፈጥሮ ህግጋት" ነውና ብለው ያስተምራሉ።

ዴይስቶቹ ይህንኑ አቋማቸውንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ "እግዚአብሔርን እንደ ሰዓት ሰሪ ቁጠሩት" ይላሉ። ሰዓት ሰሪ ሰዓቱን ይሰራና ይሸጥልናል እኛም ሰዓቱን ይዘን ወደ ቤታችን እንሄዳለን። ሰዓቱም በራሱ ጊዜ ይዞራል (ይቆጥራል) እንጂ ሰዓት ሰሪው ቤታችን እየተመላለሰ አያዞርልንም። "ፈጣሪም" እንዲሁ ነው፤ ተፈጥሮን ፈጠረና "ለተፈጥሮ ህግጋት" ሰጠው። "የተፈጥሮን ህግጋት አውቀህ መኖር ታዲያ የአንተ ድርሻ ነው። ህይወትህ በእጅህ ናት! ማለታቸው ነው። ዴይስቶቹ።

በነገራችን ላይ ዴይዝም "የቃል እምነት" ወይም "የብልፅግና ወንጌል" ስሁት አስተምህሮ "ቅድመ አያት" ነው። ለዚያ ነው ከቃል እምነት መምህራን መካከል እንደ ማይልስ ሞንሮይ ያሉት "እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚሰራው እኛ ስንፈቅድለት ነው" በማለት እግዚአብሔር በምድር ባለ ጉዳይ "አያገባውም" የሚል ዓይነት የድፍረት ቃል የሚጠቀሙት። እንዲሁም "በአንደበታችን ቃል" (word of faith) "የተፈጥሮ ህግጋቱን" አንቀሳቅሰን የምንፈልገውን ሁሉ ማግኘት እንችላለን የሚሉት ። (ትይይዙን በቀጣይ ልጥፍ   እመለስበታለሁ)

ችግሩ ምንድነው?

ታዋቂው የስነ መለኮት ምሁር ኤን. ቲ. ራይት "ዴይዝም የኤቲዝም (እግዚአብሔር የለሽነት) ምንጭ ነው ብሎ ያምናል። ራይት ሲናገር "ዴይዝም በመጀመሪያ የመፅሐፍ ቅዱሱን እግዚአብሔር እንደ ባላባት (Landlord) እንድትቆጥረው ያደርግሃል። ቀጥሎ ይህ ባላባት (Landlord) የሆነ እግዚአብሔር በሰርክ ኑሮህ ውስጥ የለም ይልሃል። በመጨረሻ እግዚአብሔር ራሱ የለም ይልሃል" ብሏል። እውነቱን ነው። እግዚአብሔር በሰርክ ህይወታችን ላይ መሪ እና ተቆጣጣሪ ካልሆነ በጊዜ ሂደት "እግዚአብሔር የለም!" የማንልበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ስለዚህ አንዱ እና ትልቁ ችግር ዴይዝም "ለእግዚአብሔር የለሽነት" አስተሳሰብ መንገድ ጠራጊ መሆኑ ነው።

ሌላው ችግር፤ ዴይስት (Deist) ስትሆን "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን" ብለህ መፀለይ አለመቻልህ ነው። "እግዚአብሔር በሰማይና በምድር የወደደውን አደረገ" ብለህም አታመሰግንም። "እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ" እያልህ ለእግዚአብሔር ስልጣን እውቅና አትሰጥም። ዴይስት ስትሆን ተንበርክከህ "ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?" ብለህ እግዚአብሔርን አትለምንም። "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" ብለህም አትዘምርም።

ዴይስት ስትሆን "እግዚአብሔር ምን ይፈልጋል" ሳይሆን "እኔ ምን እፈልጋለሁ" ብለህ ነው ህይወትህን የምትቃኛት። በአይምሮህ ብቻ ነው የምትመራው። ዴይዝም በተፈጥሮ ህግጋት ተጠቅመህ የመረጥኸውን ማምጣት የጠላኸውን ማስወገድ የምትችልበትን ሃይል እንደ ተጎናፀፍህ  እንድታስብ ያደርግሃልና።

በአጭሩ "ዴይዝም" በክርስትናችን ውስጥ መሠረታዊ የሆነውን "እግዚአብሔርን የመታዘዝ" እና "ለእግዚአብሔር ክብር" የመኖር ፍላጎታችንን የሚቀማና "ትዕቢተኛ" የሚያደርግ ክፉ ትምህርት ነው።

ከስር በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው ዳዊትም እና ዳጊ "ዴይስቶች" እንደሆኑ "በአወንታዊ የአስተሳሰብ ሃይል የተፈጥሮ ህግጋትን በመጠቀም ሃብትም ሆነ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ" ማግኘት ትችላለህ" በሚለው ዘውትራዊ ትምህርታቸው እና "አነበብናቸው፣ መመሪያዎቻችንም ናቸው" በሚሏቸው መጻሕፍት እንዲሁም "ጀግኖቻችን ናቸው!" እያሉ በሚጠቅሷቸው ሰዎች በቀላሉ መለየት ይቻላል። ዶ/ር ወዳጄነህም በተለያዩ መድረኮች ላይ በሚያቀርባቸው መርኸ አልባ (አይጨበጤ) "አነቃቂ" ንግግሮቹ እንዲሁም ከዳዊትና ከዳጊ ጋር ከፈጠረው ጥምረት ዴይስት እንደሆነ ማወቅ ይቻላል። (ታዲያ ጥንታዊያኑ ዴይስቶች በፎቶው ላይ እንደሚታዩት እና መሰሎቻቸው በገንዘብና በዝና ፍቅር የወደቁ ነበሩ ለማለት አይደለም)

ስለዚህ ሰሞነኛው የሶስቱ ሰዎች ጥምረትና ዘመቻ ምንም እንኳ ዓለማዊ (Secular) ቢመስልም፤ "ሃይማኖት ቅብ" የሆነው፣ "ፈጣሪ" ወይም "አምላክ" የሚሉ ቃላትን ለማታለያነት የሚጠቀመው፣ "ለአዲሱ አስተሳሰብ" (New Tought) እንዲሁም "ለቃል እምነት እንቅስቃሴ" መሠረት የሆነው
"የዴይዝም" (Deism) ፍልስፍና በሀገራችን እየተስፋፋ መምጣቱን አመላካች ስለሆነ ቅዱሳን ወገኖች በተለይ ወጣቶች "ከቃል እምነት" ስሁት ትምህርቶች ብቻ ሳይሆን እንዲህ ካለ ዘመናዊ አስተሳሰብ መስሎ ከሚቀርብና ወደ "ትዕቢት"  ብሎም ወደ "ክህደተ እግዚአብሔር" ከሚመራ "የዴይስቶች" ትምህርት ተጠበቁ ለማለት እወዳለሁ።

ከዴይስቶቹ ተጠበቁ!!

ቴዎድሮስ ተጫን
@nazrawi_tube
2.2K viewsΒενιαμίν, 12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 07:58:11 በሮንዳ ባይረን መጽሓፍ እና ዲቨዲ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር እያደረጉ ያሉ ምሁራን እና ክርስቲያን የዕቅበተ - እምነት ሰዎች በመጽሓፉም ሆነ በፊልሙ ላይ ያለው የባይረን አስተሳሰብ “በዘመናት የቆዩትን የቃል - ወጎች ( oral tradition)፣ በሥነ-ጽሁፍ፣ በሩቅ ምሥራቅ ኅይማኖቶች እና በፍልስፍናዎች ውስጥ ያሉትን  አስተሳሰቦች አሰባስቦ  በአንድ ላይ የመጣ አዲስ ፍልስፍና ነው ብለው ይናገራሉ። መጽሓፉ እና ፊልሙ እንደ አዲስ እና አስደሳች ሆኖ ባለንበት በዚህ ዘመን ለአንባቢያን  የሕይወት ልምምድ ቢቀርብም ከምሥጢሩ መጽሓፍት እና ፊልም በፊት ግን ተመሳሳይ መልእክት ያላቸው ሌሎች  መጽሓፍትና ብዙ ሰዎች ነበሩ...

__
የበለጠ ለማንበብ፦
Instant view የሚለውን ይጫኑ
__

https://telegra.ph/የመሳብ-ሕግ-የሚያስተምረው-ሁለንተናዊ-የኅይል-ጉልበት-መጽሓፍ-ቅዱሳዊ-ወይስ-ሜታፊዚካላዊ-06-18
1.9K viewsΒενιαμίν, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-17 15:57:16 ናዝራዊ Tube pinned «የስበት ሕግ ( law of attraction) ወንጌላዊ አማኝ በሆነውም - ባልሆነውም ።  የመጽሓፍ ቅዱስ ሰባኪ በሆነውም -  በአነቃቂ ተናጋሪም ( motivational speakers)።   እንደገናም በእግዚአብሔር ሕልውና በሚያምነውም ፣በዩንቨርስ ልዕለ- ተፈጥሮአዊ ኅይል( “universal energy force,)  በሚደገፈውና እምነቱን  በእርሱ ላይ በጣለውም  ሰው ዘንድ፣ ሌት ከቀን የሚያውጠነጠን፣…»
12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-17 15:55:50 የስበት ሕግ ( law of attraction) ወንጌላዊ አማኝ በሆነውም - ባልሆነውም ።  የመጽሓፍ ቅዱስ ሰባኪ በሆነውም -  በአነቃቂ ተናጋሪም ( motivational speakers)።   እንደገናም በእግዚአብሔር ሕልውና በሚያምነውም ፣በዩንቨርስ ልዕለ- ተፈጥሮአዊ ኅይል( “universal energy force,)  በሚደገፈውና እምነቱን  በእርሱ ላይ በጣለውም  ሰው ዘንድ፣ ሌት ከቀን የሚያውጠነጠን፣ አዲስ ራስ -ተኮር  ግለ ኅይማኖታዊ ልምምድ ውስጥ የተገባበት፣ ከመጽሓፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር እየተጎናጎነ እንግዳ ትምህርት እና አነቃቂ ንግግር የሚሰጥበት ይህ የስበት ሕግ (law of attraction ) በእውነት ምንድነው?

__
ለማ
ንበብ፦
Instant view የሚለውን ይጫኑ
__
https://telegra.ph/የስበት-ህግ-ምንድነው-06-17
1.9K viewsΒενιαμίν, 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-17 14:42:44
በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሠረት በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በ"የልጆቻችን ኢትዮጵያ " ፕሮግራም፣ የገደብ አልባ አዎንታዊ ዕሳቤን (Extreme Positive thinking) ጎጂነት በተመለከተ፣ ከጋዜጠኛ ቢንያም ፍርድ አወቀ ጋር ያደረግነውን ውይይት ቀንጨብ አድርጌ እንደሚከተለው ለጥፌላችኋለሁ። ለርዕሰ ጉዳዩ በሚሆን መልኩ ተቀንጭቦ የተወሰደው የውይይቱ ክፍል 44 ደቂቃ ቢፈጅ ነው። በሚመቻችሁ መንገድ ተከታተሉት።(በምስሉ ላይ 108.7 የሚለው 107.8 በሚለው ይስተካከል)

Getahun Heramo
@nazrawi_tube
1.4K viewsΒενιαμίν, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-16 14:11:02 ቤተክርስቲያንን እያደከሟትና በክርስቶስ በተገለጠው ህይወትና ተልእኮ ልክ እንዳትሆን ያዘገዩአት በውስጥና በውጪ የሚነሱ ኑፋቄዎች ብቻ ሳይሆኑ በክርስቶስ በተገለጠው ብርሃን የታየውን የቤተክርስቲያን ማንነትና ተልእኮ በሚገባ ያላዩ ነገር ግን መድረኮቻችንን በስፋት የያዙ ሰባኪዎች ስብከቶች ናቸው። ከአሳቤ ጋር ላትስማሙ ትችላላችሁ። ነገር ግን እንደ ስህተትና ኑፋቄ የማይቆጠሩ ነገር ግን በሰው አሳብ የተቃኙና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የተደገፉ "ጥሩ ስብከቶች" ቤተክርስቲያንን ከልኳ አውርደዋታል። መልኳ እንዳይታይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ለምን ግን ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ ስብከቶች ጠፉ? ለምን ግን መሲሃዊ ማህበረሰብ መፍጠር አቃተን? ለምን ግን በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተሳነን? ለምን ግን ሙሴ በሰማይ ያየውን በጥንቃቄ ወርዶ እንደሰራ የራሱን መልካም አሳብ እንዳልጨመረበት በተገለጠው በክርስቶስ ልክ ለመስራት አቃተን? ወደ አዲስ ኪዳን ተመልሰን ክርስቶስን ካላገኘነውና በእርሱ አእምሮ ካላሰብን በስተቀር ክርስቲያናዊ ማንነትና ተልእኮ ሊኖረን ከቶ አይቻልም። ስመጥር ስለሆንን በየቦታው ስለተጋበዝን ይህንን የልክነት (የመሲሃዊ አገልጋይነት) ሚዛን ካደረግን ተሳስተናል። በአንድ ስብከት ከመድረክ መድረክ መዞር (ለቀማ ይሉታል!!!) ቤተክርስቲያንን ማገልገል ከመሰለን ተሳስተናል። ልኩ ክርስቶስና በእርሱ የተገለጠው የእግዚአብሔር የፈቃዱ ዕውቀት ብቻ ነው። እግዚአብሔር አሳቡን የነገረን በልጁ ነውና ልጁ በሌለበት ስብከት የልጅነት ህይወት አይታሰብም። አንድም ቀን ብትሆን ክርስቶስን እናውራ እንስበክ። የራሳችንን የንግግር ችሎታ የጥበብ ብልጫ ትተን በክርስቶስ ላይ እናተኩር።

የሰው ስብከት የሰው ጥበብ የሰው ንግግር የሰው ችሎታ የሰው ምኞት በበዛበት ማህበር መካከል ከክርስቶስ በቀር ላለማየት ላለማወቅ መቁረጥ በክርስቶስ አእምሮ መገኘት ነው። ጥበብ ይህ ነው። የመንፈሳዊ አገልግሎት ከፍታው ይኼ ነው። የአገልግሎት መዘወሪያውና ጽኑ መሰረቱ ይኸው ነው።

ባለቴሌቪዥን ሰባኪዎችማ ከዚህ እሩቅ ናቸው። እነሱን ማሳመንና ርቀው ከሄዱበት መንገድ መመለስ አይቻልም። ስብከታቸውና ትምህርታቸው ከክርስቶስ (our new center of consciousness) በብዙ የራቀ ነው።

No Christological mind, No Christological Community.
No Christ like mind, No Christ like living.

@nazrawi_tube
1.7K viewsΒενιαμίν, 11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-15 13:53:01 “በስውር…”

የተረሳ ወይስ የተጣሰ?

“በስውር…” መረሳትም መጣስም የሌለበት ቃል ነው። በክርስቶስ ትምህርት መሠረት በስውር መፈጸም አለባቸው የተባሉት ሦስቱ ነገሮች አሉ:-

1. ስንሰጥ በስውር መሆን አለበት። “… በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።”(ማቴ.6:3-4)

2. ስንጸልይ በስውር መሆን አለበት። “… በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።” (ማቴ.6:6)

3. ስንጦም በስውር መሆን አለበት። “… በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።” (ማቴ.6:17-18)

እነዚህ በስውር ተፈጽመው ግልጽ ክፍያን የሚያገኙ ክርስቲያናዊ ተግባራት ናቸው።

ስንመጸውት፣ ስንጸልይና ስንጾም ሰዎች “ፐ” እንዲሉን መሆን የለበትም። ለሰዎች ከመታየት ፍላጎት ጋር የሚደረግ የትኛውም መንፈሳዊ ተግባር ውድቅ ነው። በፊታችን መለከት ለማስነፋት የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የከበሩ አይደሉም። በዚህ ዘመን መንፈሳዊ ተግባሮቻችንን እያዝረከረከ ከንቱም እያደረገ የሚገኝ ነገር ቢኖር “ግብዝነት” የሚባለው ነገር ነው። በምኩራብም ሆነ በመንገድ አንድን ነገር ልናደርግ ስንነሳ የሚቀሰቅሰን ኃይል ወይም የተነሳሽነት አቅም የምናገኘው ከልታይ ባይነት ከሆነ ግብዝነት ማለት እሱ ነው። ግብዝነት ደግሞ በሰማያት ባለው አባታችን ዘንድ ያለንን ዋጋ ያሳጣል። እንደ ግብዞች አት ሁን የሚለው መመሪያ ነው።

ስንመጸውት፣ ስንጸልይና ስንጾም እግዚአብሔር በስውር የተደረገውን የሚያይ በግልጽም የሚከፍል መሆኑን ከማመን ጋር መሆን ይኖርበታል። ከሰዎች ከምናገኘው የአድናቆት ክፍያ ይልቅ የእግዚአብሔር ክፍያ ይሻላል ብሎ የሚያስብ አማኝ ሁሉ እነዚህን መንፈሳዊ ተግባራት በስውር መፈጸም ይጠበቅበታል። በነዚህ ክፍሎች “በስውር የሚያይ አባትህ በግልጽ ይከፍልሃል” የሚለው ሃሳብ ሁለት ነገሮችን ይዟል። አንድም እግዚአብሔር የተሰወረውን የሚያይ መሆኑን ሲሆን ሌላም እግዚአብሔር በግልጽ ከፋይ መሆኑን ነው። አቤት ትጋቱ፣ አቤት ልገሳው፣ አቤት መሰጠቱና መሥዋዕትነቱ የመባል ፍላጎታችንን ገታ አድርገን በስውር አይቶ በግልጽ በሚከፍል አባታችን ፊት ዋጋ በሚኖረው ሁኔታ ማድረግ ይኖርብናል።

በዚህ ቃል ሚዛን ላይ ስንወጣ እንዴት ነን? ትንሽ የምትሉት ይኖራችኋል? እኔ ይህ ቃል የተረሳ ወይም የተጣሰ መስሎኛል።

ወርቅነህ ኮይራ
@nazrawi_tube
1.8K viewsΒενιαμίν, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 13:39:20 'የትም ተወለድ Competent ሁን' ነው መርሁ

'ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ።' ይላል የግብጽ ንጉስ ፈርዖን። ዮሴፍ በባርነት ተሽጦ የሚኖር የግብጽ ዜግነትም መብትም ያልነበረው እስረኛ ነበር። የንጉሱን ሕልም ፈታ ፈታ አድርጎ በዚያ ብቻ ሳያበቃ በግዞት ለሚኖርባት አገር የ14 አመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቁጭ ቁጭ አድርጎ ዞር ሊል ሲል ፈርዖን ይመሰጥበትና 'ወዴት ወዴት. . . ?! አንተው ካመጣኸው አንተው አሩጠው እኔ ፈታ ልበልበት' ብሎ ስልጣኑን በሙሉ ለጆሲ delegate አድርጎ relax ማድረግ ቀጠለ! ግብጽ በግዜው በነበረው geo-political reality DV የሚሞላባት አገር ሆነች። ሰው ሁሉ ለsurvival የሚሸሽባት። Bible ነው ይህንን የሚነግርህ።

ዛሬ ታሪኩን አንብቤው ገርሞኝ ነው። ባቢሎንን፣ ፋርስና ሜዶንን፣ ሮምን. . . ብትጠቅስ መሪዎቻቸው ከዘር ይልቅ competence ላይ አተኩረው ገራሚ skill የነበራቸውን ግለሰቦች ከየትኛውም ጎሳ እየሰበሰቡ በመንግስታቸው ስርዓት አጥምቀው በአሪፉ reward እያደረጉ ተጠቅመው ይጠቅሙ ነበር። They recognized talent. ዳንኤል፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ . . . talented ምርኮኞች ነበሩ። Somebody recognized their merit. (ያው ለግዜው theologyን ትተን historyው ላይ እናተኩር) That somebody was a great leader who know what to value and whom to reward. ዝም ብሎ ዘሬ፣ ብሔሬ. . . ገለመሌ የሚል ዝባዝንኬ ሳያበዛ problem solverን ከየትም የዓለም ጥግ ፈልጎ አግኝቶ reward ያደርጋል።

አማሪካን ተመልከት። የፈለገ ዘረኞች ቢሆኑ አሪፍ ብቃት ካለህ ከየትኛውም የዓለም ጉራንጉር ውስጥ ጭቃህን እያራገፍክ ብትመጣም ግድ ሳይላቸው እየተነጫነጩም ቢሆን ዶላር ይበጥሱልሃል። ለዚያ እኮ ነው ከእኛው ጨለማ ገጠር ወጥተው ወደ ምዕራባውያኑ የፈለሱ አንዳንድ የተሳካለቸው talented አበሾች autobiography ሲጽፉ፣

ከመዳ ወላቡ እስከ Malibu፣
ከአርማጭሆ እስከ Idaho፣
ከዋልድባ ገዳም እስከ Amesterdam
ከዋድላ-ደላንታ እስከ Atlanta
ከሸገር እስከ Manchester
ከገላን እስከ Milan

የሚል ቅጥያ ርዕስ ጨምረው ተዓምር የመሰላቸውን destiny እያሰቡ የሚነግሩን። ‘እዚህ ግባ ከማይባል ሰፈር ብወለድም እዚህ ግባ ብለውኝ ይኸው እያኖሩኝ ነው’ የሚል መልዕክት ያደርሱናል።

እናማ በአጭሩ ምን ለማለት ነው. . . በገራሚ ክህሎት ሰልጥነን እስካልተዘጋጀን ድረስ ዘሬ፣ ብሔሬ፣ አያቴ. . . ስንል ዛሬም መዘበቻ እና እጅግ ከሚገባው በላይ የተናቅን ህዝቦች ሆነናል። ምንም ነው የእኛ ብሔር። ችግር ፈቺዎች ናቸው ድርሻ ያላቸው በዚህች ዓለም።

ምን ያምረኛል. . . ይህንን ሁሉ ሚሊየን በብሔሩ ብቻ ተመክቶ ውጥርጥር ብሎ አገር ጠበበኝ የሚልን ወጠምሻ ሰብስቤ ትልልቅ የምዕራባውያን ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የጉልበት ስራ እንዲሰራ አራግፌ መምጣት! አለ አይደል incompetencyውን እና ስንፍናውን በብሔሩ ውስጥ ተሰውሮ የሚሸሸውንና የሌሎችን ስኬት ለመቀማት አገር የሚያምሰውን ወስጄ ጥልቅ እና ሰፊ coal mine ውስጥ ከሰል በአካፋ እየዛቀ ሰርቶ በላብ ማደርን እንዲማር መተው።

ይቆጫል ኢትዮጵያ መወለድ።
Yared Donis
@nazrawi_tube
1.9K viewsΒενιαμίν, 10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 18:53:26
የክርስትንና መንገድ እንደ "አስቸጋሪ፣ የማይቻልና ጠባብ" አድርገን እንደናስብ የሚያደርገን፣ ለሥጋችን የሚመቸውን ሰፊውን መንገድ ስለምንመረጥ ነው። ከክርስቶስ ፍቅር ይልቅ በሰፊው በር በኩል የምናገኘው የኀጢአት ደስታ ስለሚበልጥብን ነው። ስለ በደላችንና ስለኀጢአታችን በመስቅል ሞት ሕይወቱን ስለ ለእኛ አሳልፎ የሰጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "አስጨናቂ ገዢ" አይደለም።

በመስቀሉ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር የተረዳ ሰው ጠባቡን መንገድ እንደ ዕዳ አያየውም። ይልቁንም ለዓለምና ለሥጋው ፈቃድ በየጊዜው ይሞቷል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው፣ “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።” ( ገላትያ 2 : 20) ክርስቶስን መሲሕ ብቻ ሳይሆን ጌታ አድርጐ በልቡ ላይ አንግሧል።  ከኀጢአት ከሚገኘው ደስታ ይልቅ በማይወዳድር መልኩ በክርስቶስ ፍቅርና ክብር ደስ ይለዋል። የዓለም ሳይሆን የክርስቶስ ፍቅር እስረኛ በመሆኑ በጠባቡ በር ይገባል። ጠባቡ በር የፍቅርና የክብር በር ነው። በአንድ ጊዜ የጌታም የዓለምና የሥጋ መሆን አይቻልም። የት ይሆን ያለነው?

አቤቱ፤ የመስቀልህ ፍቅር ያድሰን። አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)
@nazrawi_tube
1.9K viewsΒενιαμίν, 15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ