Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-13 12:05:52 ውጫዊ ስጦታዎች፣ ስኬቶች፣ ድሎች ወዘተ ጊዜያዊ ደስታን ሊፈጥሩልህ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ዘለቄታዊ አይደሉም፤ ይለመዳሉና፡፡ በእርግጥ መሻትህ ዘለቄታ ያለው መደነቅ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር ቃል ነው በትሑት ልብ መምጣት ያለብን፡፡ ወደ ጌታ ኢየሱስ ነው መቅረብ የሚኖርብን፤ “የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።” (ቈላ.2፥3)!

ለ23 ዓመታት እንዳየሁት፣ የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም አዲስ ነው፡፡ እንደ አልማዝ (diamond) ብዙ ገጽታዎች (multifaceted) ስላሉት፣ ዛሬ የተደነቅንበት ቃል ነገ ደግሞ ባልተረዳንበት መንገድ ያስደንቀናል፡፡ የሚገርመው ነገር፣ ብዙ በቆፈርን ቁጥር ጥፍጥናው እየጨመረ ይሄዳል እንጂ እንደ ሌሎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች በፍጹም አይለመድም፡፡ ለእኔ እንደ እዚያ ነው የሆነልኝ፡፡ አያሌዎችም ይህንኑ መስክረዋል!

ምናልባት እያነበብከው መደነቅ ያቆምነውና ትርጉም አልባ የሆነብን፣ ልባችንን ዘግተነው ይሆን? ቅዱስ ቃሉ“እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።” (መዝ.24፥7) ስለሚል፣ ከማንበባችን በፊት መጸለዩ አስተዋይነት ነው ብዬ አምናለሁ–ያውም ከተቻለ በሚገባ (ጊዜ ካገኘን ከግሩም ጸሎቶች በኋላ ብናነብበው የበለጠ መልካም ይሆንልናል)።

ቦታው ለጸሎት የማይመች ከሆነ፣ እንዲሁ በጸሎት መንፈስ መሆን ይቻላል (because prayer is an attitude)! ያኔ የክብር ንጉሥ ቃሉን ያበራዋል፤ ዓይናችንንም ይከፍታል፡፡ እናም ከላይ እያወራሁ ያለሁት መደነቅ ይመጣል፡፡ ነፍሳችንም ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው ደስ ይላታል (መዝ.119፥162)!

በመጨረሻም፣ አንዴ ለንባባችን መደላደል ከፈጠረን በኋላ፣ ጌታ በቃሉ ውስጥ ድምፁን እንዲያሰማን በትሕትና እየተማጸንነው፣ የልባችንን ዓይኖች እንዲያበራ መሻታችንን እያሳየነው እናንብበው፡፡ እንዲያ ብናደርግ መንፈስ የሆነው ጌታ ሕያው በሆነው ቃሉ ውስጣችንን በመደነቅ ይሞላዋል፡፡

“ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፤ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው። ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ፤ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።” (ምሳ.24፥13-14)

ተባረኩልኝ!
Dr. Beke
@nazrawi_tube
301 viewsΒενιαμίν, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 15:21:45
ክርስቶስን ማወቅ ፕሮቴስታንት የሚባል ኅይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጉዳይና ናፍቆት ነው::

ፍጥረት ሁሉ የጎደለው ክርስቶስን ከማወቅ ነው ስለዚህም ፍጥረት ሁሉ የሚሞላው ክርስቶስን በማወቅ ነው::

ፍጥረትን እንዳለ የሚፈውሰው ክርስቶስን ማወቅ እንጂ የሆነ ፖለቲካዊ ርዕዮተ-አለምን ማወቅ አይደለም: ፍጥረት በሰው ፍልስፍና አይድንም በእግዚአብሔር "ፍልስፍና" እንጂ - እርሱም ክርስቶስ::

Knowing Christ is the apex of the whole creation.

ጳውሎስ:-

"እርሱንና የትንሳኤውን ኃይል እንዳውቅ . . . ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን ተጎዳሁ"

". . . ክርስቶስን ታውቁ ዘንድ እጋደላለሁ"

". . . ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው"

መልካም ዕለተ እሁድ ለሁላችን::
ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube
922 viewsΒενιαμίν, 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:28:58
አዲስ ኪዳንን በአንድ ወር ውስጥ አንብቦ የመጨረስ ፕላን።

@nazrawi_tube
1.2K viewsΒενιαμίν, edited  17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 23:05:06 ዕብድም ብሆን ፍቅሩ በልቤ ትልቅ ቦታ አለው!"

ዝርዝር ታሪኩ ውስጥ አልገባም። ከጥቂት ዓመታት በፊት ካወቅሁትና አልፎ አልፎ እየተገናኘን ስለ ሕይወት ከምናወጋ፣ ጌታ ኢየሱስን አብዝቶ ከሚወድ፣ መናገር የፈለገውን የእግዚአብሔርን ቃል ያለ አንዳች መደነቃቀፍ በቃሉ ከሚወጣ፣ ቸርች በማዘውተር፣ ቃሉን በማንበብ፣ በመጸለይና በመዘመር ነፍሱን ከምትረካ አንድ የተወደደ ወንድም ጋር ከረጅም ጊዜ መጠፋፋት በኋላ ድንገት ተገናኘን። በቆይታችን ካወጋናቸው ቁም ነገሮች መካከል ልቤ የተነካበትን፣ ለእምነታችን ጽናት የሚቀሰም አንዳች ትምህርት ይገኝበታል ብዬ ያሰብኩትንና ከንግግራችንን ክፍል የቆነጠርኩትን ወዲህ አምጥቼዋለሁ።

እሱ፦ ...የማልክደው ነገር የአእምሮ በሽተኛ ነኝ። በየቀኑ ኪኒን እወስዳለሁ። አንዳንዴ ነርቨስ የምሆንበት አጋጣሚ ሲከሰት እንኳ ምን ማድረግ እንዳለብኝና እንደሌለብኝ አውቃለሁ። ከፍ ባለ ድምጽ ብቻዬን ስለፈልፍ አይተኸኝም ታውቃለህ። ብዙ ጊዜ እንደዛ ዓይነት ስሜት ውስጥ ሆኜ ሳገኝህ የምታሳየኝን ፊት ፈጽሞ አልረሳውም። ዕብድም ብሆን ያለሁበትን ሁኔታ ማን እንደሚረዳኝና እንደማይረዳኝ አውቃለሁ።

...በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኜ እግዚአብሔርን አስበዋለሁ፣ በቃሉ እደገፋለሁ። ዕብድም ብሆን መንገዴን አልስትም፣ ዕብደቴ ኢየሱስን ከመውደድና ከመከተል አላገደኝም። ፍቅሩ በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው። ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል፤ እወድሃለሁ።

እኔ፦ (ስሙን በቁልምጫ ጠርቼ) እኔም እወድሃለሁ። አንተ እያለፍክበት ባለው መንገድና ያንን ፈተናህን እያስተናገድክ ባለበት የእግዚአብሔር ፀጋ፣ ጠንካራ መንፈሳዊ ሕይወትህና ብስለትህ ሁሌም እደነቃለሁ። በጠቀስካቸው ስሜቶች ውስጥ ስትሆን የምትሰጠኝ "የብቻዬን ተወኝ" ምልክት ይገባኝ ነበር። አንተ በምንም ሁኔታ ውስጥ የጌታ ነህ። ራስህን "ዕብድ ነኝ" በሚል ቃል ባትገልጽ ደስ ይለኛል። ማንኛውም ሰው የተለያየ የሰውነቱን ክፍል አሞት መድኅኒት እንደሚወስድ ያንተም ችግር እንዲሁ ነው።

እሱ፦ ሽሜ፣ "ዕብድ ነኝ" ያልኩት ህመሜ ከአእምሮ ጋር የተያያዘ ስለሆነ እንጂ በእርግጥም ሙሉ በሙሉ ያበድኩ ዓይደለሁም። ማን ያውቃል ይኼ ነገር እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያጠለቀው ሕይወቴን የሚገራበት ልጓም ሊሆን ይችላል። እኔ እንደዛ አድርጌ ነው የማስበው። የሆነብኝን ነገር በክርስቶስ ኢየሱስ ካገኘሁት ዘላለማዊ ድኅነት ጋር ሳስተያየው ምንም እንዳልሆነ አስባለሁ። ያለ ጌታ በሰው ሀገር ያሳለፍኩትን ከባድ ሕይወት አጫውቼሃለሁ ....

አምላኬን እወደዋለሁ፤ ሁሌም እጸልያለሁ። አሁን እናቴን ትንሽ አሟት ልጠይቃት መጥቼ ነው እንጂ እህቴጋ ነው ያለሁት። ሳንተያይ የቀረነው ለዚያ ነው። እዚህ ከነበርኩበት ጊዜ ይልቅ እህቴጋ በነጻነት ድምጼን አውጥቼ የመጸለይ ዕድል አግኝቻለሁ። እናቴም ብትሆን እንዳልጸልይ አትከለክለኝም ነበር። አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነኝ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እንዲህ ዓይነቱ የእምነት ጽናትና የመንፈሳዊ ሕይወት ብርታት በዚህ ዘመን የአየር ክልሉን ከተቆጣጠሩት "ሁሉ በእጄዎች" እና "መልስ በኪሱዎች" የተሰወረ የመንፈሳዊ ከፍታ ሚስጥር ነው። በጤንነት እና በብልፅግና መኖር የእግዚአብሔር ህላዌ ማረጋገጫ እንደሆነ ተደርጎ በሚሰበክበት በዚህ ዘመን እምነትን በሌላ ገፁ የሚያሳዩን፣ እንደዚህ ወንድሜ እንደ ደመና የከበቡን ብዙ ምስክሮች ስላሉን በዚህ ደስ ይለኛል።

ሽመልስ ይፍሩ
@nazrawi_tube
875 viewsΒενιαμίν, 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 16:31:47 “በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች፣ የሰርክ ልማድ እስኪመስል ድረስ እየታዩ ያሉት አንዳንድ ምልልሶቻችን፣ ለትልቅ ቅራኔ በር የሚከፍቱና አሉታዊ ስሜቶች ያየሉባቸው ናቸው። ከዐሳብ ይልቅ ሰብእናን ማጥቃትንና የተቃወመንን ኹሉ በተመጣጣኝ የመልስ ምቶች ማደባየትን ተክነናል። ከፉውን በመልካም የመመለስና በጸድቅ በልጦ የመገኘት ክርስቲያናዊ ዕሴት ያለን እስከማይመስል ድረስ፣ ለኹሉ በሰፈሩት ቍና የመስፈር ዓለማዊ ጥበብ ተጠናውቶናል። ዐሳቡን ያልገዛንለት ሰው ሲኖር፣ ሌሎች ሰዎች ለዚያ ሰው ያላቸው ክብርና ፍቅር እስኪሸረሸር ድረስ በሚዘልቅ ጥቃት እንከፋበታለን፤ የለየለት ማጠልሸት ውስጥ እንገባለን።” አሳየኸኝ ለገሰ

ተጨማሪ ያንብቡ
https://hintset.org/articles/social-media/

--
@nazrawi_tube
1.1K viewsΒενιαμίν, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 08:28:08 አድምጡልኝ ይሄን ዝማሬ


1.9K viewsΒενιαμίν, edited  05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 07:30:07 እንደምን አደርን።

እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ከአንዳንድ ጉድ ውስጥ ቶሎ መንጥቆ ያወጣናል፡ አንዳንዴ ግን ብዙ ስንፍጨረጨርና ስንጨነቅ እያየ ዝም ይልና በራሱ ጊዜ ያወጣናል፡ ሌላ ጊዜ ጭራሹኑ ላያወጣን ሁሉ ይችላል፡ ለዚህ ደግሞ ትልቁና መጽሃፍ ቅዱሳዊው ምክንያት የሚመስለኝ እግዚአብሔር የገባንበትን ጭንቅ ወይም መከራ ወይም "የተወላገደ" የሕይወት መንገድ ክብደት እያየ ሳይሆን የሚሰራው የገባንበት ነገር እርሱ የሚፈልገውን ነገር በሕይወታችን ሰርቶአል ወይ በሚለው መስፈርት መሆኑ ነው፡ መፈተናችንን ወይም መጨነቃችንን አይወድም ነገር ግን እጅግ ለተሻለው ጉዳይ በእኛ ሕይወት ዝም ይላል።

የዕብራውያን ጸሃፊ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦

"እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው"

ኢየሱስ በስጋው ወራት በብዙ ጣርና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ቃተተ፡ ነፍሴ እስከሞት ድረስ ተጨነቀች አለ፡ ጸለየ፡ ይህች ጽዋ ብትወድ ከእኔ ትለፍ ብሎ ለመነ፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሞትን አልወሰደለትም ወይም ሐሳቡን አልቀየረም፡ ነገር ግን የዕብራውያን ጸሃፊ "እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት" ይለናል፡ እግዚአብሔር የኢየሱስን ልመና የሰማው በሞት ውስጥ አሳልፎ ከሞት በማስነሳት ነው እንጂ ሞትን በማስወገድ ወይም ጽዋውን በማንሳት አልነበረም፡ ኢየሱስን ሰምቶታል ግን እኛ በምንጠብቀውና በምንፈልገው መልኩ አይደለም የሰማው፡ በጭንቅ ውስጥ እያሳለፈ ነበር የሰማው፡ እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት አስነሳው ደግሞም በዛ ሞት ሊሰራ የሚፈልገውን ስራ ሰራ፡፡

ኢየሱስ "አምላኬ አምላኬ ስለ ምን ተውኸኝ" ብሎ ሲቃትት እግዚአብሔር "ዝም" ያለው ወይም ጣልቃ ያልገባው በዛ መንገድ የሚሰራው ስራ ስለነበረው ነው፡ ልጁን ረስቶት ወይም ጠልቶት ሳይሆን በዛ ህመም ውስጥ የብዙዎችን ፈውስ ስላየ ነው፡ ስለ ልጁማ ምን ጥርጣሬ አለ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ እርሱ ነው" ብሎ መስክሮለታል፡ ታዲያ መስቀል ላይ ጠልቶት ነው? ፈጽሞ!

የተበላሸ ወይም የተጣመመ በሚመስለው መንገድ እግዚአብሔር ጣልቃ አልገባም ማለት ረስቶናል ማለት አይደለም፡ ለእኛ ባይመስለንም እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከመጋረጃው በስተጀርባ ስራውን ይሰራል፡፡

የቲአትር ቤቱ መብራት ሲደበዝዝ ተመልካቹን ጨለማ እንዲውጠው ተፈልጎ ሳይሆን የመድረኩ ተውኔት በደንብ ተግ ብሎ እንዲታይ ስለሚፈለግ ነው።

እግዚአብሔር በህይወትህ ጣልቃ አልገባም ማለት ረስቶሃል ማለት ሳይሆን መስራት የሚፈልገውን አልጨረሰም ማለት ነው፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ የሚኖረን ብቸኛ አማራጭ በእርሱ ላይ መታመን ብቻ ነው፡ ልክ ኢየሱስ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ እንዳለ እንዲሁ እኛም በምናልፍበት የህይወት መንገድ ያለን ወሳኝ ምርጫ በስተመጨረሻ ታማኝነቱን ለሚያረጋግጠው እግዚአብሔር ነፍሳችንን አደራ አሳልፎ መስጠት ነው።

እግዚአብሔር ከአንድ መከራ መንጭቆ ከሚያወጣን ይልቅ መከራው በእኛ ህይወት ለሚሰራውና ለምንማረው እውነት ቅድሚያ ይሰጣል።

ምንም ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ።

በምናልፍበት መንገድ እግዚአብሔርን እያሰብን መጽናት ይሁንልን።

ሰላምና ጸጋ ለሁሉም።

ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube
2.0K viewsΒενιαμίν, 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 09:39:43 ሌላ ኢየሱስ… ልዩ መንፈስ… ልዩ ወንጌል

“የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።” (2ቆሮ. 11:4)

1. “ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ” -
————————-
ከተሰበከው … መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን … የቀደሙን ምስክሮች እነጳውሎስ ከሰበኩት ጋር የማይመሳሰል ሌላ ኢየሱስ የሚሰብኩ አሉ።

Then, ሁል ጊዜ በመድረኮቻችን እየተሰበከ ስላለው ኢየሱስ ትክክለኛነት ወይም እውነተኛነት እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል።

የተሰቀለውን ለሰው ልጆችም ኃጢአት የሞተውን ክርስቶስ ኢየሱስን ሳይሆን የሰውን ሥጋዊ ምኞትና ፍላጎት ለማሟላት የሚታዘዘውን ኢየሱስ እየተነሡ የሚልኩትን  ኢየሱስ የሚሰብኩ ሸቀጣሞች ምትሐተኞችና አስመሳዮች ሰባኪዎች አሉ። እንደዚህ ያሉትን ሰባኪዎች አትታገሡ። እንደ ቆሮንቶሶች አትሁኑ።

2. “ልዩ መንፈስ ብታገኙ” -
—————————
ያላገኘነውን ልዩ መንፈስ ሊሰጡ የሚመጡ የክርስቶስ ያልሆነውን መንገስ የሚያከፋፍሉ የውሸትን መንፈስ የሚያሰራጩ አሉ።

ያኔ ክርስቶስን ስናምን ከተሰጠን ከታተምንበት ቅዱሱ መንፈስ ጋር የማይናበብ፣ ለክርስቶስ ተገዢ እንድንሆንና ትዕዛዙን አክባሪ እንድንሆን የማያበረታታንን መንፈስ ሊያስተላልፉልን የሚመጡ የልዩ መንፈስ አቀባዮች አሉ።

ክርስቶስን ወደመምሰል የማያሳድገን መንፈስ በተቃራኒው ግን ምድራዊና ቁሳዊ ፍላጎቶቻችንን እየተከተልን እንድንከንፍ የሚጠይቀን መንፈስ የሚያናፍሱ ራሳቸውንም እንደ መንፈስ የሚቆጥሩ ሰባኪዎች አሉ። ይህ መንፈስ ስሙ ብቻ ነው እንጂ ዓይነቱ ሌላ ነው። አትታገሡአቸው። እንደቆሮንቶስ አትሁኑ።

3. “ልዩ ወንጌል ብታገኙ” -
—————————-
ከክርስቶስና ከርሱ ታማኝ አገልጋዮች ከተቀበልነው ወንጌል የሚለይ፣ ሰምተን ከዳንንበት ወደ ሕይወት መንገድ ካመጣን ከጌታችንና ከመድኃኒታችን  ወንጌል ጋር የማይጣጣም ልዩ ወንጌል ይዘው በየከተማው የሚዞሩ ሰባኪዎች አሉ።

የዘር የጎሳ የክፍፍል ወንጌል፣ የጥቅም የክብርና የዝና ወንጌል፣ የባሕል የልምድ የወግና የሥርዓት ብቻ ወንጌል፣ ስሜት ቀስቃሽ ብቻ ወንጌል፣ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ማኅበራዊ ጉዳዮች ወንጌል … የሚሰብኩ ዙሪያችን ላይ ቁጥራቸው ከፍ እያለ ነው።

የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚሰውር ወንጌል፣ አሰናካይና ወደ ኋላ ጎታች ወ ጌል፣ የግልሰቦችን ልምምድ  ብቻ የሚያራግብ ወንጌል ይዘው ወደ ቤታችን፣ ወደ ሠፈራችን፣ ወደ ሀገራችን የሚመጡ ሰባኪዎችን አትታገሡአቸው። እንደቆሮንቶስ አትሁኑ።

ወርቅነህ ኮየራ
@nazrawi_tube
2.3K viewsΒενιαμίν, 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 21:37:30 .     "ማንም የለም"
     ምናሴ ፍርድአወቅ
ድንቅ ዝማሬ

Share
@nazrawi_tube
1.9K viewsΒενιαμίν, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:05:17
የቱንም ያህል ብንወራጭ መቼ እንደሆነ ነው የማናውቀው እንጂ የሆነ ቀን የሆነ ቦታ በሥጋ እንደ ተወለድናት ከሥጋ እንለያታለን፡ ቤንጃሚን ፍራንክሊን ተናገሩት እንደሚባለው ከሆነ በዚህ ዓለም ውስጥ ከሞትና ከግብር በስተቀር ምንም ነገር እርግጠኛ አይደለም፡ የግብሩን እርግጠኞች ባንሆንም ከቀን ወደ ቀን ሞት በሰውነታችን እየጨመረ ስለሚሄድ የሥጋን ሞት ልንክደው አንችልም። በዚህ ዓለም ውስጥ በመወለድ…
2.1K viewsΒενιαμίν, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ