Get Mystery Box with random crypto!

ውጫዊ ስጦታዎች፣ ስኬቶች፣ ድሎች ወዘተ ጊዜያዊ ደስታን ሊፈጥሩልህ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ዘለቄታዊ | ናዝራዊ Tube

ውጫዊ ስጦታዎች፣ ስኬቶች፣ ድሎች ወዘተ ጊዜያዊ ደስታን ሊፈጥሩልህ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ዘለቄታዊ አይደሉም፤ ይለመዳሉና፡፡ በእርግጥ መሻትህ ዘለቄታ ያለው መደነቅ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር ቃል ነው በትሑት ልብ መምጣት ያለብን፡፡ ወደ ጌታ ኢየሱስ ነው መቅረብ የሚኖርብን፤ “የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።” (ቈላ.2፥3)!

ለ23 ዓመታት እንዳየሁት፣ የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም አዲስ ነው፡፡ እንደ አልማዝ (diamond) ብዙ ገጽታዎች (multifaceted) ስላሉት፣ ዛሬ የተደነቅንበት ቃል ነገ ደግሞ ባልተረዳንበት መንገድ ያስደንቀናል፡፡ የሚገርመው ነገር፣ ብዙ በቆፈርን ቁጥር ጥፍጥናው እየጨመረ ይሄዳል እንጂ እንደ ሌሎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች በፍጹም አይለመድም፡፡ ለእኔ እንደ እዚያ ነው የሆነልኝ፡፡ አያሌዎችም ይህንኑ መስክረዋል!

ምናልባት እያነበብከው መደነቅ ያቆምነውና ትርጉም አልባ የሆነብን፣ ልባችንን ዘግተነው ይሆን? ቅዱስ ቃሉ“እናንት መኳንንቶች፥ በሮችን ክፈቱ፥ የዘላለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።” (መዝ.24፥7) ስለሚል፣ ከማንበባችን በፊት መጸለዩ አስተዋይነት ነው ብዬ አምናለሁ–ያውም ከተቻለ በሚገባ (ጊዜ ካገኘን ከግሩም ጸሎቶች በኋላ ብናነብበው የበለጠ መልካም ይሆንልናል)።

ቦታው ለጸሎት የማይመች ከሆነ፣ እንዲሁ በጸሎት መንፈስ መሆን ይቻላል (because prayer is an attitude)! ያኔ የክብር ንጉሥ ቃሉን ያበራዋል፤ ዓይናችንንም ይከፍታል፡፡ እናም ከላይ እያወራሁ ያለሁት መደነቅ ይመጣል፡፡ ነፍሳችንም ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው ደስ ይላታል (መዝ.119፥162)!

በመጨረሻም፣ አንዴ ለንባባችን መደላደል ከፈጠረን በኋላ፣ ጌታ በቃሉ ውስጥ ድምፁን እንዲያሰማን በትሕትና እየተማጸንነው፣ የልባችንን ዓይኖች እንዲያበራ መሻታችንን እያሳየነው እናንብበው፡፡ እንዲያ ብናደርግ መንፈስ የሆነው ጌታ ሕያው በሆነው ቃሉ ውስጣችንን በመደነቅ ይሞላዋል፡፡

“ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፤ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው። ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ፤ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።” (ምሳ.24፥13-14)

ተባረኩልኝ!
Dr. Beke
@nazrawi_tube