Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-23 20:34:20 ተለቀቀ

ሰርጎ ገቡ ትምህርት
ደማቅ መስመር ያሻናል



852 viewsΒενιαμίν, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 11:16:41 የተወደዳችሁ ወገኖች የጌታ ሰላም ይሁንላችሁ፤ ይብዛላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በመሥራት ላለፉት ብዙ ዓመታት ቆይቻለሁ። በተለይ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት ሙሉ ጊዜ ሰጥቼ ስሠራው ቆይቻለሁ። በጌታ ቸርነት ከ23 ዓመታት በኋላ ባለፈው ወር፥ ልክ የዛሬ ወር ተጠናቅቋል። እግዚአብሔር ይመስገን።

ይህ መዝገበ ቃላት ወደ 1350 ገጾችና ከ4ሺህ 800 ቃላት በላይ የያዘ፥ ለእያንዳንዱ ቃል ከምንጭ ቋንቋዎች አቻ ቃላትን፥ ትርጕምና ዝርዝር መፍቻ፥ እንዲሁም በቂ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ያካተተ ነው። ይህ ሥራ በተጠቃሚዎች ሁሉ፥ በተለይም በክርስቲያኖችና በአገልጋዮች እጅ ትልቅ እሴት የሚሆን መጽሐፍ ነው።

በኢትዮጵያ ይህን ሥራ ለማሳተም የእናንተ እርዳታ አስፈልጎኛል፤ ለጋስ እጃችሁንና ቸርነታችሁን እጠይቃለሁ። የgofundme አካውንቱ ሊንክ ይህ ነው፤ https://gofund.me/2c4353f8

እግዚአብሔር ይባርካችሁ፤ ለበረከትም ያድርጋችሁ። ዘላለም ነኝ።

Hello my friends. May the peace of Christ be on you. I have been working on the Amharic Bible Dictionary (ABD). The last few years were entirely dedicated to this prodigious work. It came to completion last month (exactly a month ago) after 23 years. Praise God.

The ABD is a 1350 plus pages work with over 4800 entries complete with source language equivalents, meanings, extensive definitions as well as ample Bible verse references. This work would be an asset in the hands of all users; especially Christians and ministers.

To have it printed in Ethiopia I need support, and here I am asking for your helping hands and generosity. The gofundme account link is: https://gofund.me/2c4353f8

God bless you and make you a blessing.

___
አገር ቤት ያላችሁ ይህንን ሥራ ለመደገፍ የምትወድዱ ወገኖች በብርሃን ባንክ የአካውንት ቁጥር፦
1010670778124
መላክ ትችላላችሁ።

ጌታ ይባርካችሁ።
_

Zelalem Mengistu
___


1.0K viewsΒενιαμίν, 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 11:43:45
ሃሰተኛ መምህራን እውነተኛ የሆነውን ትምህርት በመንፈቅ አፈንግጠው የሚወጡ ናቸው። አፈንግጠው ወጥተው ግን አርፈው የሚቀመጡም የሚያስቀምጡም አይደሉም። ራሳቸውንና አስተምኅሯቸውን አስረገው በማስገባት የመንጋውንና የቤተክርስቲያንን ጤና ለማወክ ይዳክራሉ። ትምህርታቸውና እምነታቸው ከቅዱሳት መጽሐፍት በተቃርኖ የቆመ ቢሆንም ትምህርታቸውን አስርገው ለማስገባት ይጥራሉ።

ይህ ዶክመንተሪ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቶችን እየፈተሸ፣ ትውፊትን እያጣቀሰ ከአጉል ተስፋዎች ይጠብቀናል። ብዙ ትኩረት ለሃሰተኞች በሚሰጥበት በዚህ ዘመን ሃሰተኞቹ ስለሚያወድሙት ምስኪን መንጋ ግድ የሚላቸው አገልጋዮች  እንደ እግዚአብሔር እውነት ሙግት ይቀርባል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሃሰተኛ መምህራን ምን ይላል? የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ሃሰተኛ ሆነው ለተገኙ ትምህርቶች ምን ምላሽ ሰጡ? የቤተክርስቲያን አባቶችስ ምላሻቸው ምን ነበር? ለሃሰተኛና ሰርጎ ገብ ትምህርት ምላሽ መስጠት ለምን አስፈለገ? ግንኙነታችን ምን መሆን አለበት? ሃሰተኞች በንስሃ ሲመለሱ ምን መደረግ አለበትና እቅበተእምነት እንዴት መከወን እንዳለበት የሚናገረ ዘጋቢ ነው!

በቅርብ ቀን ይወጣልና እያጋራችሁ ጠብቁን!

https://youtube.com/@ethiopianevangelicalreform7708
___
@nazrawi_tube
1.3K viewsΒενιαμίν, 08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 19:50:05 እንዳንሳሳት!
እግዚአብሔር ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል።

እኛ ባለ ራእይና መስራች ሆነን የምንቆርጥባትና የምንፈልጥባት ቤተስኪያንና "አገልጋዮቿ" እንጂ ቴአትር ቤትና ኮሜዲያን የሆኑት የክርስቶስ አካል አሁንም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ናት፡

እግዚአብሔር አሁንም ጉልበታቸውን ለባኦል ያላንበረከኩና የማሲንቆውን፣ የዋሽንቱን፣ የፀናፅሉን፣ የክራሩንና፣ የእምቢልታውን ድምፅ ሲሰሙ በዱራ ሜዳ ለቆመው ምስል የማይሰግዱ ጥቂቶች አሉት:

እግዚአብሔር ቴአትር ቤትና ኮሜዲያኖች ሳይሆን በመንፈስ ተሞልተው ቃሉን ሳይሸቅጡ የሚናገሩ አገልጋዮች አሉት:

ጥቂቶች ቢሆኑም የራሳቸውን ሳይሆን የክርስቶስን ብቻ የሚፈልጉ ትጉሃን አሉት:

የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የሆነችው የክርስቶስ አካል በጥቂት የራሳቸውን ብቻ በሚፈልጉና ለራሳቸው አጀንዳ በሚሯሯጡ ሰዎች አትለካም:

እግዚአብሔር ክርስቶስ አካል ውስጥ የተጠመቁ ህያዋን ብልቶች እንጂ ቀን ጠባቂ አባሎች የሉትም:

ቤተክርስቲያን ቴአትር ቤት አገልጋዮቿ ደግሞ ኮሜዲያን እስኪሆኑ ድረስ የት ሄደን ነበር? እኛው ነን ተጠያቂዎቹ: እስከዛሬ ድረስ በአገልግሎታችን ኮሜዲያን ስናመርት ነበር ማለት ነው?

ቴአትር ቤቶችና ቅጥረኞች ኮሜዲያን ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን የክርስቶስ አካል ቴአትር ቤትም አይደለችም አገልጋዮቿም ኮሜዲያን አይደሉም:

እኛ በመሰረትናትና ባለራዕይ በሆንባት ቤተስኪያን ብቻ ላይ ነው እንደፈለግነው መናገር የምንችለው እንጂ "በገዛ ደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን" ላይ የመጣልንን የመናገር መብትም ስልጣንም የለንም:

የክርስቶስ አካልና፣ ለጥቅማቸው አድረው ክርስቶስን ባበረሩ ግለሰቦች የሚመሩ ስብሰባዎች ለየቅል መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፡

መዝሙርና ስብከት የሚመስል ነገር ያለበት ቦታ ሁሉ ቤተክርስቲያን አይደለም።

ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube
1.4K viewsΒενιαμίν, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 19:36:41
"ታዋቂ መሆን ከፈለግህ፣ ደስታን ስበክ፤ አለመታወቅን ከፈለግህ፣ ቅድስናን ስበክ።"

Leonard Ravenhill
@nazrawi_tube
2.4K viewsΒενιαμίν, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 16:40:37 በህይወቴ ከወሰንኳቸው ውሳኔዎች ሁሉ ትክክለኛ እና ህይወቴን የቀየረው ውሳኔ ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ የተቀበልኩት ቀን እና እሱን በግሌ ላውቀውና ከእርሱም ጋር ህብረት ለማድረግ እሱን የተከተልኩት እለት ነው።

እናንተም በግላችሁ ይህንን ወስኑ ለዚህኛው ዓለምም ሆነ ለሚመጣው በፍጹም አትጸጸቱም።

@nazrawi_tube
2.2K viewsΒενιαμίν, 13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-16 11:19:40 የነፍስ መከናወን (Soul Making)!

የነገረ መለኮት ሊቁ ጆን ሂክ (John Hick) “Philosophy of Religion” የሚል ግሩም መጽሐፍ አላቸው፡፡ በዚህ መጽሐፋቸው (ገጹን ዘነጋሁ) እንዲህ ይላሉ፡-This world has the potential of pain and evil but it also provides the opportunity for growth and character development!

ታዲያ ይህንን የምናልፍበትን ሂደት “Soul Making” ብለው ነው የሚጠሩት፡፡ ይህንን ስያሜ ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ እንዳሰፈረው የነፍስ መከናወን እንበለው ይሆን? “ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።” (3ዮሐ.1፥2) ብሏልና!

ሐዋርያው “ነፍስህ እንደሚከናወን/ as your soul prospers” ሲል፣ እኛ አማኞች በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ስናልፍ የሚመጣውን መንፈሳዊ ብስለት መናገሩ ነው ብዬ ነው የወሰድኩት፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ በሂደቱ ሐዋርያው ያዕቆብ የሚመጣውን መከናወን “ፍጹማንና ምሉዓን/ mature and complete” መሆናችን እንደ ሆነ መውሰድ እንችላለን ብዬ አስባለሁ።

“ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።….Let perseverance finish its work so that you may be mature and complete, not lacking anything.” (ያዕ.1፥2-4)፡፡

ታዲያ Soul Making (የነፍስ መከናወን) ትርፉ ታላቅ ከሆነ ከእኛ የሚጠበቀው ምንድነው? በጥበቡ ከፍ ያለው ጌታ እንደ ወደደ እንዲሠራን “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” ብሎ መታመን ነዋ!

ጌታ ሆይ፣ የምናልፍባቸው ሂደቶች የሚያሳምሙ ቢሆኑም፣ ነፍሳችን በአንተ ላይ እንድትደገፍ ጸጋህን አብዛልን!

Dr. Beke
@nazrawi_tube
2.2K viewsΒενιαμίν, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-14 10:06:39 “በራሴ በኩል ታላቅ ክህሎት ወይም አንደበተ-ርቱዕነት ባልጎናጸፍም እንኳን፣ እግዚአብሔርን የሚንቁትን፣ የቅዱሳን መጽሐፍትን ስልጣን በብልጠታቸውና በቀልዳቸው ሊያብጠለጥሉ የሚፈልጉትን ሰዎች ክርክር መግጠም ካለብኝ፤ ልቅ አፋቸውን በቀላሉ ጸጥ ለማሰኘት ወኔው አለኝ፡፡”

መራሔ ተሓድሶ ጆን ካልቪን
@nazrawi_tube
2.1K viewsΒενιαμίν, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-12 21:12:25 ፀሐይ የምትኖረው ብርሃንንና ሙቀትን ለመስጠት እንደሆነ ሁሉ ቤተክርስቲያንም በምድር የምትኖረው ዋናው ዓላማ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ (ለሚጠፉት ሁሉ) ለማድረስ ነው።

- ዶናልለድ ሚሌር
@nazrawi_tube
4.1K viewsΒενιαμίν, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-11 12:43:39
ዛሬ የጆን ካልቪን የልደት ቀን ነው። ( July 10, 1509 - May 27, 1564)። ልደቱን ስናስብ ቀጥሎ ያሉትን ሁለት ማሳሰቢያዎች ልተውላችሁ:-

ከሐዋርያው ከጳውሎስ:-

“ከሙታን የተነሣውን፣ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤ የእኔም ወንጌል ይኸው ነው።” (2 ጢሞ. 2:8)

ከካልቪን:-

“እረኞች በቃሉ እውነት ደፋሮች ይሁኑ . . . ማንኛውንም የዓለም ኅይል፣ ክብርና ልቀት ለቃሉ መለኮታዊና ግርማዊነት ያስገዙ። ከትልቁ እስከ ትንሹ ሁሉን በቃሉ ሥልጣን ይምሩ፤ የክርስቶስንም አካል ያንጹ። የሰይጣንን አገዛዝ ያፍርሱ፤ መንጋውን ያሰማሩ፤ ተኩላውን ይግደሉ፤ ዐመፀኛውን ይገስጹ፣ ይምከሩም። ካስፈለገም ነጐድጓድና መብረቁን ይሰሩና ይፍቱ፤ ነግር ግን ሁሉን እንደ እግዚአብሔር ቃል ያድርጉ። ” (Sermons on the Epistle to the Ephesians, xii).

ጌታችን ሆይ፣ “ክብርህን ተጠሚዎች፣ ቅዱስ ቃልህን ብቻ ሰባኪዎች፣ ለራሳቸው ፈቃድ የሞቱ ታማኝ ባሪያዎችና የወንጌል ዐደራ ጠባቂዎች አድርገን።”

አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)
@nazrawi_tube
2.5K viewsΒενιαμίν, edited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ