Get Mystery Box with random crypto!

The Christian News

የቴሌግራም ቻናል አርማ tcnew — The Christian News T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tcnew — The Christian News
የሰርጥ አድራሻ: @tcnew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.99K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።
@TCNEW

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 16:24:13
#አዲስ
#ቡርኪናፋሶ_ውስጥ_ታግተው_የነበሩት_አሜሪካዊት_መነኩሴ_ተለቀቁ

The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ባለፈው ሚያዝያ ወር ቡርኪናፋሶ ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አንድ አሜሪካዊት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መነኩሴ መለቀቃቸውን የሰሜን ምስራቅ ካያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አስታወቁ።

ጳጳሱ ቴዎፍሎስ ናሬ በሰጡት መግለጫ “እህት ሱሌን በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ጤንነት ብሎም ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላይ ይገኛሉ’’ ሲሉ ተናግረዋል።

የ83 ዓመቷ ሱሌይን ቴንሰን የሚጠቀሙበትን መነፅር ብሎም ለደም ግፊት የሚወስዱትን መድሀኒት ሳይዙ እኩለ ሌሊት ላይ ነበር በአካባቢው ከሚኝ ደብር ታግተው የተወሰዱት።

አጋቾቹ ታጣቂዎች ከመሆናቸው ባሻገር እስካሁን ድረስ ማንነታቸው አልታወቀም። ነገር ግን በቡርኪናፋሶ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ጥቃትም ይፈጽማሉ።

ጳጳስ ናሬ መነኩሴዋ ሱሌን እንዲለቀቁ ያስቻለው ሁኔታ ምን እንደሆነ ምንም አይነት መረጃ የለኝም ብለዋል። ኤፍቢአይ ከእገታው በኋላ የመነኩሴዋን መጥፋት የሚገልጽ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር።

ከአልቃይዳ እና አይ ኤስ ጋር የሚተባበሩ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን በቡርኪናፋሶ እና በአጎራባች ሀገራት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚጥቃት እና አፈና
ሲፈጽሙ ይስተዋላል።

የአካባቢው መንግስታት በታጣቂ ቡድኖቹ ላይ ተደጋጋሚ የማጥቃት ዘመቻዎችን ማካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

BBC News Amharic
147 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:18:55
#አሁን_ሊጀምር_ነው
#እግሮ_ሁሉ_ወደ_ቤተክርስቲያኒቱ_የጥናሉ።
መለከቱን መንፋት
Blast the trumpet
የማርቆስ ወንጌል 16
15፤ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፡ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
በ መንግስቱ ምስክሮች ቤተ/ክ የተዘጋጀ
ነሃሴ ከ26---29
ሀሙስ . አርብ . ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ
እሁድ ከ 4:00 ጀምሮ
አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት 3:00 የአገልጋዮች ስልጠና
ለበለጠ መረጃ 0911970550/0925116322
146 views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:06:06
#አዲስ

በኬንያ የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኤምባሲው ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አስታወቀ።
============================
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በኬንያ የኢ.ፌ.ዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ባጫ ደበሌ በኬንያ የኢትዮጵያውያን የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ሕብረት ጋር ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ተወያይተዋል። በኬንያ የሚኖሩ በየሃይማኖቱ ተከታዮች ዜጐችን ማዕከል በማድረግ ከኤምባሲው ጋር በትብብር የሚሰሩበትን ሁኔታ በቀጣይም ህብረታቸውን በማጠናከር ተሳትፎዓቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

ክቡር አምባሳደር ባጫ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች የሁሉም ሰብሳቢ በመሆናቸው በመጥቀስ አሁን በአገራችን ስለተከሰተው ጉዳይ ከምዕመኑ ጋር ለአገራችን ሰላም እንዲፀልዩ እና መንግስት የሚያደርገውን የሠላም ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኃይማኖት ተቋማት መሪዎቹ በዚህ ወቅት ስለአገራችን ሠላም፣ ስለሕዝባችን እፎይታ ዘውትር እንፀልያለን፤ ሠላም በሀገራችን ብሎም በቀጠናው እንዲሰፍን ከሚሲዮኑ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ምንጭ @የኤምባሲው ድረ ገጽ ነው።

ዜናዎችን በቪዲዮ ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ።

224 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:38:20
#አዲስ

በናይጄሪያ ፕላቶ ግዛት በተጠረጠሩ የፉላኒ ሀይሎች በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ግድያ ያለማቋረጥ ቀጥሏል።

ከቀናት በፊት አንዲት ክርስቲያን ሴት የቤተክርስቲያኗን ህንፃ ስታጸዳ ጭንቅላቷ ላይ በጥይት ተመትቶ ተገድላለች ሲል Morning Star News (MSN) ዘግቧል።

ሊዮፕ ዳሊዮፕ የተባለችው ክርስቲያን ዜና በሪዮም ካውንቲ ባንጋይ መንደር የሚገኘውን የክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከማለዳው 2:05 አከባቢ ስታጽዳ እንደተገደለች ዘገባው አክሎ አስነብቧል።

በናይጄሪያ ያሉ ክርስቲያኖች ቦኮ ሃራምን ጨምሮ በተለያዩ ቡድኖች እየታደኑ ሲገደሉ እና የፉላኒ እረኞች ኢላማ ሆነዋል።

ናይጄሪያ በእምነታቸው ምክንያቱ የሚገደሉባት ሀገር በመሆን ባሳለፍነው በፈረንጆቹ 2021 ከአለም አንደኛ ሀገር ነበረች።

እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2009 እስከ 2021 ብቻ 43,000 ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ብቻ በናይጄሪያ ምድር ህይወታቸውን አጥተዋል።

ዜናዎችን በቪዲዮ ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ።

209 views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:21:30
241 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:21:15 #የመጨረሻው_ስብከት
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

እንኳን በአሜሪካ ምድር በሌሎች አለሞችም እጅግ ታዋቂው ሰባኪ እና ጸሃፊ ፓስተር ሪክ ዋረን ታዲያ ይህ ታዋቂ ሰባኪ ከሰሞኑ የመጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ማቅረቡን ክርስቲያን ፖስትን ጨምሮ በርካታ የክርስቲያን ሚዲያዎች ብፊት ገጻቸው ይዘውት ወጥተዋል።

ፓስተር ሪክ ዋረን ‘አላማ መር ህይወት’ በተሰኘው እና በበርካታ ቋንቋዎች በተተረጎመው መጽሀፉ ነው ብዙዎች የሚያውቁት በፈረንጆቹ 1980 ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመራት አነስተኛ ቤተክርስቲያን ዛሬ 40ሺህ አባላት ያላት እና በአሜሪካ ምድር ግዙፍ የምትባል ቤተክርስቲያን ሆናለች።

የቤተክርስቲያኒቱ ስም "ሳድል ባክ ቤተክርቲያን ስትባል ላለፉት 43 ዓመታት በዋና መጋቢነት አገልግሎባታል ታዲያ ከሰሞኑ የአገልግሎቱ የመጨረሻ የሆነውን ስብከት ሰብኳል።

ከሁሉም በላይ አነጋጋሪ የሆነው ደግሞ ከ ዛሬ 40 ዓመታት በፊት "ሕይወታችሁን ዘላለማዊ ዋጋ ባለው ነገር ላይ አውሉት" በሚል ርዕስ የሰበከውን ስብከት በድጋሜ ለመጨረሻ ጊዜ መስበኩ ነው።

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የምትገኘው "ሳድል ባክ ቤተክርስቲያን" 40,000 አባላት ያሏት ሲሆን ከ 40 አመታት በፊት በፈረንጆቹ 1980 ዓ.ም በሪክ ዋረን እና ባለቤቱ ኬይ ዋረን በላግና ሂልስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረች ቤተክርስቲያን ነች።

መጋቢ ሪክ ዋረን የአገልግሎቱ መጨረሻ የሆነውን ስብከቱን ያቀረበው በአንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባል በተሰራውና በመጀመሪያዎቹ 15 ዓመታት ይጠቀምበት በነበረው የእንጨት ፑል ፒት ላይ ሲሆን "ለ43 ዓመታት እናንተን መውደድ፣ ለእናንተ መጸለይ፣ ማገልገል ፣ መቃብር አጠገብ ቆሜ ማጽናናት ፣ አልጋ አጠገብ ቆሜ ማበረታታት፣ ሰርጋችሁ ላይ መሰበክ ፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት መምከር እና ማስተማር እግዚአብሄር ለእኔ የሰጠኝ ትልቅ ዕድል ነበር በማለት ምዕመናኑን አመስግኗል።

ቤተክርቲያኒቱ በፈረንጆቹ ሴብቴምበር 3 እና 4 የፓስተር ሪክ ዋረንን የአገልግሎት 43ኛ ዓመት የምታከብር ሲሆን በሴብቴምበር 10 እና 11 ደግሞ ሪክ እና ባለቤቱ በአዲስ የአገልግሎት ዘርፍ የሚመደቡበት ቀን ይሆናል።

በሴብቴምበር 12 ደግሞ የግዙፏ ሳድል ባክ ቤተክርስቲያን አዲስ ሲኒየር ፓስተርን እንደምትሾም ክርስቲያን ፖስት አክሎ አስነብቧል።
253 viewsedited  11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:31:44
እዚህ ስፍራ ሲመጡ ቃሉን ብቻ ሳይሆን የቃሉን መንፈስ አግኝተው ሕይወትንም ይካፈላሉ።

ላለፉት 26 ዓመታት ልምድ ያለው እና በርካታ ቁጥር ያላቸውን ቅዱሳን አስታጥቆ ወደ አገልግሎት አሰማርቷል።

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በጅማ ፤ በሀዋሳ ፤ በባሕር ዳር ፤ በድሬደዋ ፤ በአዶላ በሌሎችም አከባቢዎች እንገኛለን።

Pentecostal theological Collage (PTC)
ለበለጠ መረጃ ፦ 0115 52 23 32 / 0115 52 43 95 / 09 35 80 45 መደወል ይችላሉ።
281 viewsedited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:49:53 #በ1 ዓመት ብቻ 620 ክርስቲያኖች ተገለዋል #ሀይማኖት በትምህርት ስረዓት ውስጥ መግባት አለበት ተባለ #የሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ አስቸኳይ መግለጫ ተሰጠ።

282 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 23:09:52
#በሰላም_ተጠናቋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን #91ኛው_መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሠላም ተጠናቀቀ።

ከነሐሴ 15 /2014ዓም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ መሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪዮም ግቢ ውስጥ በየደረጃው የሚገኙ የቤተክርስቲያንቷ የአመራር አካላት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና በቤተክርስቲያን የህልውና ተግዳሮት ዙሪያ ምክክርና ጸሎት ሲደረግ ቆይቷል።

ከነሐሴ 19 እስከ 21/2014 ዓም ደግሞ #ስለ_ወንጌል_ሁሉን_አደርጋለሁ " በሚል መሪ ቃል መደበኛ የቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድ ቆይቶ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሣለፍ ዛሬ አመሻሹን በአምልኮና ዝማሬ ተጠናቋል።

በዚሁ መሠረት ከመደበኛ እና የተለመዱ ተግባራት በተጨማሪ፣
፩) ዘጠኝ አዳዲስ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን መርምሮ አጽድቋል።
፪) ለሚቀጥሉ ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ 11 የአመራር ጉባኤ አባላትን መርጦ ሾሟል።
፫) በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪም ግቢ ውስጥ ተገንብቶ በአንድ ጊዜ ከ1000 ሰዎች በላይ የሚይዝና ከ27ሚልዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ዘመናዊ አዳራሽ አስመርቋል።

በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት የቤተ እምነት መሪዎች በተጨማሪ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ እና ከጀርመን የቤተክርስቲያኒቱ አጋር ድርጅት ተወካዮች የጉባኤው ታዳሚ እንደነበሩ ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከተገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል።

በመጨረሻም በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች አብሮነትን ለመግለጽ ያህል የጉባኤው አባላት ገንዘብ በማወጣት ቀለብ አጥተው ለተቸገረ የወንጌል አገልጋዮች እንዲላክላቸው ከመደረጉ በተጨማሪ ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ምልጃና የህብረት ጸሎት በማድረግ ነሐሴ 21/2914 ዓም ጉባኤው በሠላም መጠናቀቁን መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።
424 views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:00:25
#አስደሳች
#እንኳን_ደስ_አለን።

"እዚህ ድረስ በመገኘት ስላበረከታችሁልኝ የክብር ዶክትሬት አመሰግናለሁ።"
Breakthrough International Bible University (Kenya)
#ቄስ_ዶክተር_በሊ_ሳርካ

ቄስ በሊና ሳርካ ከብሬክ ስሩ ኢንተርናሽናል ባይብል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው።

መሰረቱ ኬኒያ የሆነው ብሬክስሩ ኢንተርናሽናል ባይብል ዩኒቨርሲቲ የወንጌል አገልጋዮችን ማሰልጠን፣ ማነሳሳት እና ለመጨረሻ ዘመን የመኸር ወቅት ማዘጋጀት አላማ ያለው የመጽሃፍ ቅዱስ ዩንቨርሲቲ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የወንጌል ኣገልግሎት ውስጥ ለነበራቸው አስተዋጽኦ እና ለረዥም ዘመን አገልግሎታቸው ለቄስ በሊና ሳርካ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
466 views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ