Get Mystery Box with random crypto!

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የቴሌግራም ቻናል አርማ richyaneyena — ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።
የቴሌግራም ቻናል አርማ richyaneyena — ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።
የሰርጥ አድራሻ: @richyaneyena
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.72K
የሰርጥ መግለጫ

በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ
ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 12:04:08 ያልፋል!

አያልፍም እንዳትሉ ክፉ ቀን እስኪያልፍ ጎንበስ ብሎ መጠበቅ ነው እንጂ ቀኑ ሁሉ ያልፋል።
ደስታ የሆነለት ሰው የተመቻቸለት ሰውም ቢሆን ሁሌ እንደ ተደሰተ አይቀጥልም ለተረኛ ጊዜውን ይለቃል። የወደቀ ያነሰ የመሰለውም ሰው ታች ሆኖ አይቀጥልም ትልቁ ሲወድቅ ትንሹ ይነሳል ስለዚህ ያልፋል ያልፋል።
ደስ በማይሉ ነገሮቻችን ውስጥ ያሉት ጉዳዮች ያልፋሉ በሉ ይሄም ያልፋል በሉ ደግሞም ያልፋል።
ሲያልፍ ደግሞ አስተምሮን፣ገንብቶ፣አጠንክሮ ነው ሚያልፈው።
t.me/richyaneyena
128 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:40:11 لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ

(አል በለድ - 4)
ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
115 views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:51:18 ገንዘብ የማይገዛው ለሽያጭ ያልዋለ
ከሐብታም ተነጥቆ ለእኛ የታደለ
ሺ ፍቅር ሺ ጤና ከድሃ ቤት አለ።
ልብ እየጠበበ ጨጓራ ሲሰፋ
ታዋቂ ሰው በዝቶ አዋቂ ሰው ጠፋ
እባብ እባብ ነድፎ በሽታውን ከፍ
እርስ በእር ሆነና መድሃኒቱ ጠፋ።

https://t.me/richyaneyena
268 views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 11:46:07 እውነተኛ ታሪክ

አንድ የሃብታም ልጅ ቤተሰቦቹ እንዲያገባ ፈልገው ሚስት ለማጨት የሆነች ቆንጅዬ ልጅ ያመጡለታል። እሱ እኔ ለመዳር ፈልጋችሁ ነው እቺ ያመጣችሁልኝ? ሲል ይጠይቃል አዎ ይሉታል።በቃ እኔ አገባለው ማገባት ግን እቺ ሳትሆን እኔ የምወዳት የማፈቅራት አለች ከተስማማችሁ አገባለው ይላል።ቤተሰብ ሁሉ በሃሳቡ ይስማማ እና ሊያገባ ፕሮግራሙ ይጀመራል። ቤተሰብ ልጅትዋ እንተዋወቅ ሲሉት የማስተዋውቃችሁ የሰርጌ ቀን ነው በማለት ይደመድማል። አይደርስ የለም ሰርጉ ደረሰ ተሰረገ ሙሽራው ሙሽራ ይዞ መጣ አንድ ያልታሰበ እንግዳ ነገር ነበር። ሙሽሪት አንድ እግር የሌላት አካለ ስንኩል ናት ቤተሰብ ሁሉ ተደነጋገጠ ሊያናግሩት በመወሰን አናገሩት ምንድነው ያመጣህብን አዋረድከን እኮ ይሉታል። እሱም በምንድነው ያዋረድኳችሁ ምን ሆነች ይላል። ቤተሰብም አንድ እግር የሌላት አካለ ስንኩል ናት ይሉታል።

እሱም እንዲህ በማለት ይመልሳል አልታያችሁም እንጂ እግር አላት እግሯ ያለው ልቧ ውስጥ ነው እግሯ የታየኝ ለእኔ ብቻ ነው በማለት ሚስቱ በሚስትነቷ ፀናች።
አንዳንድ ልባቸው በእግራቸው ረግጠው ይገድሉታል። አንዳንዶች ደግሞ እግራቸው በልባቸው ውስጥ አድርገው ብዙ መንገዶች ያለ እንከን ይጓዙበታል።
https://t.me/richyaneyena
608 views08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 13:51:14 እቤትህ ተቀምጠህ ከአለም ምሑር ጋር መነጋገር ከፈለክ አንብብ።

ያሲን ኑሩ ልክ ከስርቤት አንደወጣ እንዲህ ብሎ ነበር
ፌስቡክ መረጃን እንጂ እውቀት አይሰጥም
እንዲሁም በሌላ መልእክቱ የኢቅራን (የአንብብ) ትውልድ አያነብም ልክ ብሎዋል

የስንቶቻቹ ቤት መፅሀፍ ነው ትራስ አድርጋቹ የምትተሯሳቸው እህ!

ፈረንጆች አፍሪካን ሲተርቡ ምን አሉን መሰላቹ፣ ገንዘብ ስትደብቅ መፅሀፋቸው ውስጥ ደብቅ ምክንያቱም አፍሪካዎች በብዛት መፅሀፍ ከፍተው ስለ ማያዩ ስለ ማያነቡ ። መልእክቱ ለገባው ወላሂ ጥልቅ መልክት ነው። ወንድሜ እህቴ እቤትሽ ውስጥ ያለው ስለ ማንኛውም መፅሀፍ አንስተሽ አገላብጪ የኔ ወንድም እቤትህ ወስጥ ያለው መፅሀፍ ስለ ማንኛውም ነገር ይሁን አንስተህ አንብብ ትራስ አድርገህ/ ገሽ ከመተኛት በማንበብ ፈልገህ ያላገኘሀው ማንነተህ ፍንትው ብሎ ይታይሀል ።ሙሉ ሰው እንድትሆን ወኔ ይችረሀል/ርሻል። ሁሌም መፅሀፍ ስታነብ/ነቢ ከራስሽ ጋር የምታወርያቸው/ቸው አዳዲስ ነገሮች ይፈጠራሉ። ንባብ በኤለመንታሪ በሀይስኩል በኮሌጅና በዩንቨርስቲ ቆይታ የተገደበ አደለም። የብዙዎቻችን ችግር ይህ ነው። አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል።

ሪቾ ነኝ
628 views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 10:40:56 የአላህ ፍትህ እና ፍርድ ...

ነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) በአንድ ወቅት አላህን "ጌታዬ እስቲ ያንተን ፍትህ እና ፍርድ አሳየኝ?" ብለው ጠየቁት።

አላህም፦ "አንተ እኮ ትዕግሥት የለህም እንዴት አድርጌ ላሳይህ" አላቸው።

ሙሳም ..."ባንተ እገዛ ትዕግስት አደርጋለሁ" አሉት።

አላህም... "እንዲህ የሚባል ቦታ ላይ ያለው የውሀ ምንጭ አጠገብ ሂድና ተደብቀህ ዝም ብለህ የሚሆነውን ተከታተል" አላቸው።

ሙሳም ምንጯ አጠገብ በመሄድ እንዲት ዛፍ ላይ ወጥተው የሚሆነውን ለመከታተል ተዘጋጁ።

ከዚያም አንድ ፈረሰኛ ምንጯ ጋ መጣና ፈረሱን አቁሞ ውሀ ከጠጣ በኋላ የያዘው ከረጢት አጠገቡ አስቀምጦ ትንሽ ጋደም አለ።

ከትንሽ እረፍት በኋላ ፈረሰኛው ያስቀመጠውን ከረጢት ረስቶ ጉዞውን ጀመረ። ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ልጅ መጥቶ ከምንጩ ውሃ ጠጥቶ ሊሄድ ሲል ያ ፈረሰኛ ረስቶት የሄደውን ከረጢት ያገኝና ከፍቶ ሲያየው 1000 ዲናር አገኘ። ደስ ብሎት ይዞት ሄደ። ይህ ሁሉ ሲሆን ሙሳ (ዐሰ) በደንብ እየተከታተሉ ነው።

ልጁ እንደሄደ አንድ ማየት የተሳነው ሽማግሌ መጣ። ከምንጩ ጠጥቶ ውዱዕ አደርጎ እዚያው ሰግዶ ጋደም አለ። ይህ ሽማግሌ ጋደም እንዳለ ፈረሰኛው ረስቶት የሄደውን ዲናሩን አስታውሶ ሲጋልብ መጣ። ፈረሰኛውም ሽማግሌውን ቀስቅሶ ..."አሁን እዚህ ጋ ውሀ ጠጥቼ 1000 ዲናር የያዘ ከረጢት ረስቼ ሄጃለሁ። ካንተ ሌላ ማንም በዚህ ፍጥነት እዚህ መጥቶ ሊሄድ አይችልምና ንብረቴን ስጠኝ አለው።

ሽማግሌውም ..."ልጄ እኔ እንደምታየኝ ዓይነ ሥውር ነኝ እንዴት አድርጌ ያንተን ገንዘብ እወስዳለሁ?" አለው። ፈረሰኛውም ተናዶ እየዋሸው እንደሆነ በማሰብ ጎራዴውን በማውጣት "ንብረቴን መልስ አይ ካልክ በዚህ ጎራዴ ሆድህን እተረትረዋለሁ" ሲለው... ሽማግሌው ደንግጦ ማልቀስ ጀመረ። ሙሳም (ዐ.ሰ) ይህን ሁሉ በጭንቀት እየተከታተሉ ትዕግስታቸው ተሟጥጦ ጫፍ ደርሶ የአላህን ትዕዛዝ በማስታወስ ባሉበት ፀኑ።

ፈረሰኛውም በያዘው ጎራዴ የሽማግሌውን አንገት ቀንጥሶ ከዚያም ልብሱን ሲፈትሽ ምንም ሊያገኝ ባለመቻሉ ትቶት ሄደ።

ከዚያም አለህ ለሙሳ " አንተ ሙሳ ሆይ! ይህ የኔ ፍትህ እና ፍርድ ነው፡፡" አላቸው።

ሙሳም.... "ጌታዬ ትዕግስቴ ተሟጥጦ አልቋል አንተ ጥበበኛ ነህ እስቲ አስረዳኝ" አሉ።

አላህም.... "እኔ ውስጥ አዋቂ ነኝ አንተ የማታውቀውን አውቃለሁ። የፈረሰኛውን ንብረት የወሰደው ልጅ አባት ፈረሰኛው ዘንድ ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። ፈረሰኛውም በጉልበቱ ተመክቶ የላቡን ሳይከፍለው ቀርቶ ነበር። ስለዚህ ልጁ ዛሬ የወሰደው የአባቱን ሀቅ ነው።"

"ዓይነ ሥውሩ ሽማግሌ ደግሞ አይኑ ከመጥፋቱ በፊት የዚያን ፈረሰኛ አባት ገድሎት ስለነበር። ፈረሰኛው የአባቱን ገዳይ እንዲገድል አድርገናል።"

"ሙሳ ሆይ! ለሁሉም ሀቁን አድርሰናል። አንዱ ፍትሐችን ሲሆን አንዱ ደግሞ ፍርዳችን ነው።
★★★★

ቢዘገይም በዚሁ አለም አልያም በመጪው አለም ሁሉም በዳይና ተበዳይ ፍርዱንና ፍትህን ያገኛል።

«አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡»
[ኢብራሂም 14:42]
695 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 15:43:16 ምትወደው ሰው ስታይ ፈገግ በል እንደምትወደው ይረዳሃል።
ጠላትህ ስታገኝ ፈገግ በል፣ጥንካሬህ ይመለከታል።
ጥሎህ የሄደ ሰው ስታይ ፈገግ በል፣ፀፀት ይሰማዋል።
የማታውቀው ሰው ስታገኝ ፈገግ በል፣ሰላም ያስገኝልሃል።
ሲዋሹህ በውሸት ሊያሳምኑህ ሲፈልጉ ፈገግ በል፣ እንደ ምትበልጣቸው ይገባቸዋል።
መልካም ሰው ሆነህ ሆድ ሲሰርቁህ ፈገግ በል፣ስራቸው ያለ እረፍት ይጨነቁበታል የቤት ስራ ትሆንባቸዋለህ።

በመብትህ ሲመጡ ግን በምንም ነገር አትደራደር ፈገግታህ ስበርና መብትህ አስከብር

ሪች ነኝ

https://t.me/richyaneyena
1.2K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 16:00:36 ሲከፋኝ ማኩረፍ እንጂ መቀየም አላውቅም።ሲበድሉኝ ሰውን መራቅ እንጂ ቂም መያዝ አልችልም።

ህይወት አንዳንዴ ፊልም ትሆንብናለች ደራሲዋ አሏህ ሲሆን ተዋናዮቹ እኛ ነን።ሁሉም ሰው በግሉ አሪፍ አክተር ለመባል ይሮጣል።ነገር ግን ሁሉም ከተፃፈለት ውጭ አይተውንም።

https://t.me/richyaneyena
1.2K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 15:56:44 አንዳንድ ሰዎች
ሲገፉን ስንገፋላቸው
ሲገፉን ስንገፋላቸው የሚገፉን አገፋፍ ወደ ገደል ቢመስላቸውም ወደ መልካም መንገድ ገፍተው ሚያሻግሩን ክፉ ሰዎች ባይኖሬ ኖሮ ምናልባት ዛሬ ላይ የቆምንበት ትንሽም ይሁን ትልቅ ስኬት ላይ አንደርስም ነበር።ብዙ ጊዜ በጠማማ መንገድ ውስጥ የእኛ ቀጥ ያለ መንገድ ምናገኝበት አጋጣሚም ጭምር ነው። መገፋት አትፍሩ ወተት ስለረጋ ሳይሆን ስለተገፋ ነው ቂቤ ሚወጣው።

https://t.me/richyaneyena
1.3K viewsedited  12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ