Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሳት መጻሕፍት

የቴሌግራም ቻናል አርማ holy_scriptures — ቅዱሳት መጻሕፍት
የቴሌግራም ቻናል አርማ holy_scriptures — ቅዱሳት መጻሕፍት
የሰርጥ አድራሻ: @holy_scriptures
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.76K
የሰርጥ መግለጫ

In this channel:

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
ማንኛውም ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ በ @HolyScriptures1bot ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ::

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 22:07:21 ኤርምያስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?
² ተክለሃቸዋል ሥር ሰድደዋል፤ አድገዋል አፍርተውማል፤ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
³ አንተ ግን፥ አቤቱ፥ አውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፥ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፥ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
⁴ ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቸ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ ፍጻሜያችንን አያይም ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ጠፍተዋል።
⁵ ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ?
⁶ ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትታመናቸው።
⁷ ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።
⁸ ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን አንሥታብኛለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ።
⁹ ርስቴ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው።
¹⁰ ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።
¹¹ ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፤ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።
¹² በወናዎች ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።
¹³ ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፤ ደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፤ ስለ እግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።
¹⁴ እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
¹⁵ ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እምራቸዋለሁ፥ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።
¹⁶ በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩ፥ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
¹⁷ ባይሰሙኝ ግን ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ አጠፋውማለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።



                     Join us
        @Holy_scriptures
        @Holy_scriptures
                   ይ ላ ሉን
129 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:11:16 '    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን እስካሁን እንዳደረጋችሁት ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አጥብቃችሁ ያዙ።”
ኢያሱ 23፥8 (አዲሱ መ.ት)


                     Join us
        @Holy_scriptures
        @Holy_scriptures
                   ይ ላ ሉን
202 views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:07:37 #መጻሕፍትን_እንመርምር ዘሌዋውያን 4 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፡፤ ² ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ³ የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኃጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኃጢአት መሥዋዕት…
116 views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:05:54 '    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ድነት ቸል ብንል እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ ድነት በመጀመሪያ በጌታ ተነገረ፤ ከእርሱ የሰሙትም ለእኛ አረጋገጡልን።”
ዕብራውያን 2፥3 (አዲሱ መ.ት)


                     Join us
        @Holy_scriptures
        @Holy_scriptures
                   ይ ላ ሉን
78 views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:08:19
ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ከሄደ እንደሚታሰር ትንቢት የተናገረው ማን ነው?
Anonymous Quiz
13%
ሀ. ሐዋርያው ጴጥሮስ
7%
ለ. ወንጌል ሰባኪው ፊልጶስ
7%
ሐ. የፊልጶስ ሴቶች ልጆች
72%
መ. አጋቦስ
69 voters206 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:54:37 #መጻሕፍትን_እንመርምር 2ኛ ቆሮ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና። ² በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ³ ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም። ⁴ በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ…
201 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:51:36 ' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።”
ሐዋርያት 20፥28 (አዲሱ መ.ት)


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
ይ ላ ሉን
210 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:44:22 የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች


ኣስተዋፅኦ


1. መግቢያ (1፡1-17) ለሰው ልጅ ጽድቅ በጽኑ ማስፈለጉ (1፡18—3፥20)

(ሀ) ለኣሕዛብ ማስፈለጉ (1፥18-32)
(ለ) ለአይሁድ ማስፈለጉ (2፡1—3፥8}
(ሐ) ለሰው ልጅ ሁሉ ማስፈለጉ (3፥9-20)

2. የእግዚአብሔር ክቡር የጽድቅ ችሮታ (3፥21-5:21)

(ሀ) በእምነት ስለሚገኝ መዳን አጭር ገለጻ (3፥21-31)
(ለ) በእምነት ስለመዳን የአብርሃም አብነት (4፥1-25)
(ሐ) ጽድቅ የሚያስገኘው ባርኮትና አለኝታ (5፥1-11)
(መ) አዳምና ክርስቶስ ሲነጻጸሩ (5፥12-21)
a. አዳም ኀጢአት፡ ኲነኔ ሞት
b.ክርስቶስ ጸጋ ጽድቅ ሕይወት


3.ጽድቅ በእምነት ሲገለጽ (6፡1—8፥39)

(ሀ) ከኀጢአት ባርነት ነጻ መሆን (6፥1-3)
a. ከክርስቶስ ጋር ለኀጢአት ሙት መሆን (6፥1-14)
b. የጽድቅ ባሪያ ሆኖ ከክርስቶስ ጋር መኖር (6፥15-23) (ለ) በሕግ ሥር ካለው ትግል ነጻ መሆን (7፥1-25)
c. በሕይወት መንፈስ ሕግ ነጻ መሆን (8፡1-39)


4. በእምነት የሚገኝ ጽድቅ፣ ከአስራኤል አንጻር (9፥1-11 ፥ 36)

(ሀ) የእስራኤል የእንቢተኝነት ችግር ( 9፥1-10፥21)
(ለ) የእግዚአብሔር ዕቅድ አሸናፊነት (11፥1-36)

5. በእምነት መጽደቅ በተግባር ሲገለጽ (12፡1—15፡13)

(ሀ) አማኙና ቅድስና (12፥1-2)
(ለ) አማኙና ማኅበረሰብ (12፡3-21)
(ሐ) ኣማኙና መንግሥት (13፥1-7)
(መ) አማኙና የፍቅር ሕግ (13፡8-15፥13)

መደምደሚያ (15፥14—16፥ 27)

ጸሓፊው ጳውሎስ

ዋና ሐሳብ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ መገለጥ
የተጻፈበት ጊዜ፤ 57 ዓ.ም.



ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፣ ገጽ 1731



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
ይ ላ ሉን
251 views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:44:12 #መጻሕፍትን_እንመርምር

2ኛ ቆሮ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና።
² በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና
³ ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም።
⁴ በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን።
⁵ ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።
⁶-⁷ እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥
⁸ ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል።
⁹ ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን።
¹⁰ መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።
¹¹ እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን ሰዎችን እናስረዳለን ለእግዚአብሔር ግን የተገለጥን ነን፤ በሕሊናችሁም ደግሞ የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።
¹² በመልክ እንጂ በልብ ለማይመኩ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት እንሰጣችኋለን እንጂ ራሳችንን ደግሞ ለእናንተ የምናመሰግን አይደለንም።
¹³ እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።
¹⁴ ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤
¹⁵ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።
¹⁶ ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።
¹⁷ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
¹⁸ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።
²⁰ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።
²¹ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።


2ኛ ቆሮንቶስ 5 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ መኖሪያችን የሆነው ምድራዊ ድንኳን ቢፈርስም፣ በሰው እጅ ያልተሠራ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሆነ ዘላለማዊ ቤት በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።
² እስከዚያው ግን የሰማዩን መኖሪያችንን ለመልበስ እየናፈቅን እንቃትታለን፤
³ በርግጥ ከለበስነው ራቊታችንን ሆነን አንገኝም።
⁴ በዚህ ድንኳን እስካለን ድረስ ከብዶን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ሟች የሆነው በሕይወት እንዲዋጥ ሰማያዊውን መኖሪያችንን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንፈልግም።
⁵ ለዚህ ዐላማ ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ሊመጣ ላለው ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን መያዣ አድርጎ የሰጠንም እርሱ ነው።
⁶ ስለዚህ ሁል ጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤
⁷ ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።
⁸ ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋር መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ።
⁹ ስለዚህ በሥጋ ብንኖርም ወይም ከሥጋ ብንለይም ዐላማችን እርሱን ደስ ማሰኘት ነው።
¹⁰ ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እንቀርባለንና፤ እያንዳንዱም ሰው በሥጋው ለሠራው በጎ ወይም ክፉ ሥራ ተገቢውን ዋጋ ይቀበላል።
¹¹ እንግዲህ ጌታን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ስለምናውቅ፣ ሰዎች የምንናገረውን እንዲቀበሉ ለማድረግ እንጥራለን። የእኛ ማንነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጠ ነው፤ ደግሞም በኅሊናችሁ ዘንድ ግልጽ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
¹² ይህን የምለው ራሳችንን በእናንተ ፊት እንደ ገና ለማመስገን ሳይሆን፣ በእኛ እንድትመኩ ዕድል ልሰጣችሁ ነው፤ ይኸውም በውጭ በሚታየው ለሚመኩት እንጂ በልብ ውስጥ ባለው ነገር ለማይመኩ መልስ መስጠት እንድትችሉ ነው።
¹³ ከአእምሮ ውጪ ብንሆን ለእግዚአብሔር ብለን ነው፤ ባለ አእምሮም ብንሆን ለእናንተ ነው።
¹⁴ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ ምክንያቱም አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች ሆነናል፣ ከዚህም የተነሣ ሁሉ ሞተዋል።
¹⁵ በሕይወት ያሉትም ለሞተላቸውና ከሙታን ለተነሣላቸው እንጂ ከእንግዲህ ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ።
¹⁶ ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በውጫዊ ነገር አንመዝንም፤ ከዚህ ቀደም ክርስቶስን በዚህ መልክ መዝነነው ነበር፤ ከእንግዲህ ግን እንደዚህ አናደርግም።
¹⁷ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፣ አዲስ ሆኖአል።
¹⁸ ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤
¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።
²⁰ ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
²¹ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት (ወይም የኀጢአት መመሥዋዕት) አደረገው።


ሙሉውን አውድ በሚገባ ተመልከቱ። ደግሞ በብሉይ ኪዳን "የኃጢአት መሥዋዕት" ምን እንደሆነ በቀጣይ እንመለከታለን። ምክንያቱም የኃጢአት መሥዋዕት አሳቡ በዘፈቀደ የመጣ ሳይሆን ከብሉይ ኪዳን የሚመዘዝ ስለሆነ።



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
ይ ላ ሉን
221 views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:26:29
ስለ ሮሜ መልእክት እውነት የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
35%
ሀ. የሮሜን ቤተክርስቲያን የተከለው ሐዋርያው ጳውሎስ ነው
43%
ለ. የሮሜ መልእክት የተጻፈው በቆሮንቶስ ከተማ ነው
20%
ሐ. የሮሜ መልእክት ሕግ ምንም ጥቅም እንደሌለው ይናገራል
2%
መ. የሮሜ መልእክት ለአይሁዶች ብቻ ነው የተጻፈው
51 voters228 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ