Get Mystery Box with random crypto!

ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)

የቴሌግራም ቻናል አርማ paulosfekadu — ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
የቴሌግራም ቻናል አርማ paulosfekadu — ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
የሰርጥ አድራሻ: @paulosfekadu
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.79K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-15 13:23:52 “ኢቮሊውሽን - ፬”

(Jan 14, 2020 የተጻፈ)

Theistic Evolution (Evolutionary Creationism)

አዝጋሚ ለውጥ እውነት ቢሆንስ? እውነትነቱ የክርስትናን እውነትነት ወይም የእግዚአብሔርን እውነት ያስቀራልን? በጭራሽ። ይህን የሚሉት ዕውቁ ሳይንቲስት ፍራንሲስ ኮሊንስ ናቸው፤ “The Language of God” በሚለው መጽሐፋቸው። ምክንያቱም እውነት ከእውነት ጋር አይጣረስምና! እውነት ከእውነት ጋር አይጋጭምና! እውነትና እውነትን አይቀዋወሙምና።

ፍራንሲስ ኮሊንስ ዕውቅ ሳይንቲስት ናቸው፤ ጥሩ ክርስቲያንም ናቸው። ስለ ዘረ መል ለማጥናት የተቋቋመው Human Genome Project መሪ ነበሩ። አስደናቂውን የዲኤንኤ ግኝት ለፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተንና ለጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌየር ሲያስረዱ ከቢል ክሊንተን ያገኙትን “This is the language of God” የሚል አስደናቂ ንግግር ነው የመጽሐፋቸው ርእስ ያደረጉት። ዶ/ር ኮሊንስ ለእምነትና ለሳይንስ ባደረጉት በጎ አስተዋጽዖ የተከበረውን የቴምፕልተን ሽልማት ተቀብለዋል፤ BioLogos የተሰኘ በእምነትና በሳይንስ መካከል በሚኖረው ግንኙነት ላይ የሚሠራ ተቋምም መሥራች ናቸው። ፍራንሲስ ኮሊንስ ዝግመተ ለውጥ እውነት ስለ መሆኑ ባዮሎጂያዊ ማስረጃዎችን እያቀረቡ ያስረዳሉ። መላለሙ (ዩኒቨርሱ) ቢሊዮን ዓመታት ገደማ እንደ ሆነውም ይቀበላሉ። በሰዎች፣ በዓሣማ እና በዝንጀሮ መሰል እንስሳት ዲኤንኤ መካከል ያለውን ተመሳሳይነትም ያስረዳሉ።

በፍራንሲስ ኮሊንስ የቀረበው የኢቮሊውሽን ንድፈ ሐሳብ ማለትም Theistic Evolution ባለፈው ከተመለከትነው (በቁጥር 3) “ኢንተለጀንት ዲዛይን” ጋር የሚስማማበትም የማይስማማበትም ገጽታ አለው። የሁለቱ ስምምነት የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት መቀበላቸው ላይ ነው። የሕይወት አስገኝ እግዚአብሔር ነው። ይህኛው የዝግመተ ለውጥ ክርስቲያናዊ ትንተና ግን፣ እግዚአብሔር ሕይወትን ከመፍጠሩና ለዝግመተ ለውጥ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ አሟልቶ ሂደቱን ከማስጀመሩ ውጭ በየመካከሉ እየገባ ሂደቱን እንዳልመራ ነው የሚናገረው። በዚህ አመለካከቱ ከኢንተለጀንት ዲዛይን አስተሳሰብ ጋር ይለያያል።

በፍራንሲስ ኮሊንስ አቀራረብ፣ ስለ ፍጥረትም ሆነ ስለ ሕይወት አመጣጥ የሚቀርበው ሳይንሳዊ ትንተና የተሟላ የሚሆነው እግዚአብሔር ሲታከልበት ነው። ለምሳሌ መላለሙ የተገኘው በBig Bang (ታላቁ ቡልቅታ) ንድፈ ሐሳብ መሠረት ከሆነ፣ የፍንዳታው አስጀማሪ እግዚአብሔር መሆን አለበት። ሳይንስም ቢሆን፣ ታላቅ ቡልቅታ/ፍንዳታ በመካሄዱ መላለሙ ስለ መገኘቱ እንጂ የሚፈነዳው ነገር ከየት እንደ መጣ፣ ማን እንዳፈነዳው፣ ሲፈነዳም ሕይወትን ለማኖር አስፈላጊ የሆነው ልከኛ ከባቢያዊ ሁናቴ እንዴት ሊፈጠር እንደ ቻለ መልስ አይሰጥም። የሰዎች፣ የእንስሳትና የተክሎች ሕይወት ከአንድ ሕይወት ጀምሮ እያዘገመ እዚህ ስለ መድረሱ እንጂ “ሕይወት” የተባለው ነገር በመጀመሪያ ከየት እንደ መጣ አይናገርም። ይህ ሁሉ ግን “የእግዚአብሔር ያለህ!” የሚል ጩኸት የያዘ ነው።

መላለሙ ጅማሬ እንዳለው ሳይንሱም ይቀበላል። ጅማሬ ያለው ነገር ሁሉ የተጀመረ መሆኑ ደግሞ አመክንዮታዊ ነው። ይህም የእግዚአብሔርን ተሳትፎ ይጋብዛል። ስለዚህ ክርስቲያኖች የአዝጋሚ ለውጥን ንድፈ ሐሳብ ተቀብለው ከእምነታቸው ጋር ሊያዛምዱት ይችላሉ። የዝግመተ ለውጥ አቀንቃኞችም እግዚአብሔር የፍጥረቱ አስጀማሪ መሆኑን ቢቀበሉ ነው የሚበጃቸው። በዚህም ላይ የአዝጋሚ ለውጥ ትንታኔ ራሱን በየጊዜው እያረመ የሚሄድ በመሆኑ፣ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት እየጠበበ ሊሄድ እንደሚችል ይታሰባል፤ ትንታኔው ወደ እውነት እየተጠጋ የሚሄድ ከሆነ! በዚህ ትንተና መሠረት ሲታይ፣ ኢቮሊውሽን አምላክ የለሻዊ (atheistic) ብቻ ሳይሆን፣ አምላክ አለሻዊ (theistic) ሆኖ ሊቀርብ እንደሚችል መረዳት ይቻላል።

አዝጋሚ ለውጥ ከክርስትና ጋር ሊስማማ የሚችልበት መንገድ መኖሩ ለበርካታ ክርስቲያኖች ግርታ ይፈጥርባቸው ይሆናል። ነገር ግን የዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሐሳብን ጀማሪው ቻርልስ ዳርዊንም ፍጥረት ከእግዚአብሔር መገኘቱን ያምን ነበር። የእርሱ ሙግት ከሕይወት ጅማሬ በኋላ ያለውን ሂደት የሚመለከት ብቻ ነበር። በወቅቱ ከነበሩ ዕውቅ የነገረ መለኮት ሰዎችም የዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሐሳቡን የተቀበሉ ነበሩ። በተለይም አንዳንድ ጥብቅ ካልቪኒያውያን የሰውን ልጅ አጠቃላይ ውድቀትና የመሳሰሉትን አስተምህሮቻቸውን ስለሚደግፍላቸው የአዝጋሚ ለውጥ ትንታኔው ተመችቷቸው ነበር። እናም የክርስትና እና የአዝጋሚ ለውጥ ዝምድና ከመጀመሪያም የነበረ ነው።

Theistic Evolution በእግዚአብሔር ሚና ላይ ያለው ትንታኔ ግን ከጥያቄ አያመልጥም። እግዚአብሔር ሕይወትን ከመፍጠርና አዝጋሚውን የለውጥ ሂደት ከማስጀመር በቀር በሂደቱ ላይ መቼም ያልተሳተፈ ከሆነ፣ ፍጥረቱን በሕያውነትና በንቃት የሚያስተዳድር ሳይሆን፣ የፈጠረውን ዓለም በተለያዩ ሕግጋትና አሠራሮች አጥሮ ከፍጥረቱ ገለል ያለ አምላክ ያስመስለዋል፤ ዓለምን እንደ ሰዓት ሞልቶ የተወ አምላክ። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የእግዚአብሔር አሠራር አይደለም።

* * *

እንደ ክርስቲያን አንድ ልንክደው የማንችለው እውነት ቢኖር፣ እግዚአብሔር መኖሩንና የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ የፈጠረው እርሱ መሆኑን ነው። ከእርሱ በቀር አምላክ፣ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም!

አዝጋሚ ለውጥንን በሚመለከት አማኞች ሁልጊዜም ሊጠይቁ የሚገባቸው ሌላኛው ጥያቄ ደግሞ፣ “አዝጋሚ ለውጥ እውነት ነው ወይ?” የሚለው ነው። ይህኛው ዋነኛው ጥያቄም ሁለት የመልስ አማራጮች አሉ።

የመጀመሪያው የመልስ አማራጭ፣ አዝጋሚ ለውጥ እውነት ነው የሚለው ነው። አዝጋሚ ለውጥ እውነት ከሆነ ደግሞ፣ እውነት ሁሉ የእግዚአብሔር ነውና የመቀበል ግዴታ አለብን። ከዚያ ግን የእግዚአብሔርን ፈጣሪነትና አዝጋሚ ለውጥን አስተቃቅፈው ከሚጓዙ ንድፈ ሐሳቦች መካከል አንዱን መቀበል አይቀሬ ይሆናል። (ይህ ሁሉ ግን የዘፍጥረት የመጀመሪያ ምዕራፎች ምን ዐይነት የሥነ ጽሑፍ ዘውግን እንደሚከተሉ በመረዳት ላይ ይወሰናል!) ነገር ግን ንድፈ ሐሳቡ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ተቀብሎ እንዲጓዝ፣ ክርስቲያን የሳይንስ ባለሞያዎች ጥረትና ተሳትፎ ያስፈልጋል።

አዝጋሚ ለውጥ እውነት ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሁለተኛው አማራጭ የሚሆነው ደግሞ፣ በጭራሽ እውነት አይደለም የሚለው ምላሽ ነው። አዝጋሚ ለውጥ እውነት ካልሆነ ግን እስካሁን ስንዳስሳቸው የነበሩት የማስታረቅ ሙከራዎች ሁሉ ፋይዳ አይኖራቸውም። እግዚአብሔርና አዝጋሚ ለውጥን በአንድ ላይ መያዝም አቋም የለሽነት ይሆናል። እውነት ያልሆነን ነገር ከእውነት ጋር ቀይጦ የመጓዝ ጥረት ለእውነት ካለመታመን ተለይቶ አይታይምና።

ታዲያ አዝጋሚ ለውጥ እውነት ነውን? ጥያቄው ሁለት የመልስ አማራጮች ቢኖሩትም፣ ትክክለኛው መልስ ግን አንድ ነው። የትኛው ይሆን?

ጨርሻለሁ።

https://t.me/PaulosFekadu
489 viewsedited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 09:44:21 “እናቱና ወንድሞቹም ወደ እርሱ መጡ፥ ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያገኙት አልተቻላቸውም። እናትህና ወንድሞችህ ሊያዩህ ወድደው በውጭ ቆመዋል ብለው ነገሩት። እርሱም መልሶ፦ እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው አላቸው። ... ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ። የተሸከመችህ ማሕፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው። እርሱ ግን፦ አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ።” (ሉቃ. 8፥1921፤ 11፥27-28)
788 views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 13:01:59 ጳውሎስ ፈቃዱ፣ “በቃለ እግዚሓር” ዝግጅት “የእግዚአብሔር ዐብሮነት ከሁሉ ይበልጣል” በሚል ርእስ ያካፈለውን ዐጭር መልእክት ይመልከቱ።




--
በፌስቡክ ገጻችን ይከተሉን:- http://facebook.com/hintset
ቴሌግራም ላይ ይከተሉን:- https://t.me/hintset
ዩትዩብ ላይ ሰብስክራይብ ያድርጉ:- http://youtube.com/hintsetube
ድረ ገጻችንን ይጎብኙ:- http://www.hintset.org
1.2K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 13:33:40 ኢቮሊውሽን - ፫

(Dec. 23, 2019 የተጻፈ)

በክፍል 1 እና 2 Creationism ተብሎ የሚታወቀውን ክርስቲያናዊ አማራጭ ተመልክተናል። ይህ ምልከታ የትኛውን የፍጥረት አካል ከአንድ ቤተሰብ በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ወደ ሌላ ቤተሰብ አልተለወጠም፤ የሚታየው ነገር ሁሉ በዚሁ መልኩ ነው የተፈጠረው የሚል ነው። ዛሬ የምንመለከተው ክርስቲያናዊ አማራጭ ግን ፍጥረት ረጅም ዓመታትን በፈጀ ሂደት እንደ ተፈጠረና በሂደቱም ውስጥ ከአንዱ የፍጥረት ቤተሰብ ወደ ሌላኛው ቤተሰብ የተደረገ ለውጥ (Macro Evolution) መኖሩን የሚቀበል ነው።

ይህ ዐይነቱ አዝጋሚ ለውጥ እውነትነቱ ቢረጋገጥ የክርስትናን እውነትነት ያፈርሳልን? በጭራሽ! በዚህ የሚስማሙ ትልልቅ ክርስቲያን ፈላስፎች፣ ዐቃብያነ እምነት፣ የሳይንስ ባለሞያዎች አሉ። ለምሳሌ አልቪን ፕላንቲጋ፣ ዊልያም ሌን ክሬይግ፣ ዊልያም ዴምቤስኪ፣ …። (በነገራችን ላይ ፍጥረት በረጅም ጊዜ ሂደት እንደ ተፈጠረ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (Gregory of Nyssa) የተባለው የቤተ ክርስቲያን አባትም አመልክቷል።)

ዳርዊንያዊው የአዝጋሚ ለውጥ ትንተና በሳይንስ የተረጋገጠ አይደለም። መላ ምት ነው። ለምሳሌ በሰውና በዝንጀሮ መካከል 99 በመቶ የDNA መመሳሰል መኖሩ እውነት ቢሆንም፣ ይህ ግን ሰውና ዝንጀሮ የጋራ ቅድመ አያት ያላቸው ስለ መሆኑ አያረጋግጥም። ማለትም በሰውና በዝንጀሮ መካከል ያለው ተመሳሳይነት ማስረጃ (evidence) ቢኖረውም፣ ሰውና ዝንጀሮ ለመዛመዳቸው ማረጋገጫ (proof) አይደለም። ከመጀመሪያውም በዚህ መልኩ የተፈጠሩ ቢሆንስ? (በነገራችን ላይ ስለ ዳርዊንያዊው አዝጋሚ ለውጥ ሲነሣ ብዙዎቻችን “ሰው ከዝንጀሮ መጣ” በማለት የሚያትት አድርገን ነው የምናስበው። ሰው እና ዝንጀሮ የጋራ ቅድመ አያት ስላላቸው ዘመዳሞች ናቸው እንጂ አንዳቸው ከሌላኛቸው አልመጡም፤ በዳርዊንያዊው የአዝጋሚ ለውጥ ሐተታ መሠረት። እንዲያውም ሰው እና ዝንጀሮ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹም እንስሳት ጭምር ከአንድ ምንጭ ነው የተቀዱት። አንዱ ነጠላ ሕዋስ ነው በአዝጋሚ ለውጥ እነዚህን ሁሉ የተለያዩ እንስሳት ወደ መሆን የመጣው። ዳርዊን እንደሚያትተው ይህ አዝጋሚ ለውጥ ግን በዕቅድ የተመራ አይደለም፤ በዕድልና በአጋጣሚ እንጂ። natural selection acting on random variations. ዳርዊኒዝም መዝሙሩ ይሄ ነው።

ዳርዊንያዊው የአዝጋሚ ለውጥ ንድፈ ሐሳብ፣ እግዚአብሔር ጠል የሆነው ዓለም በጡንቻው ተመክቶ በሳይንስ የተረጋገጠ አስመስሎ ቢያቀርበውም፣ በሳይንስ የተረጋገጠ እውነታ አይደለም። ከመላምትነት አልፎ እውነትነቱ ገና ያልተረጋገጠ አንድ የሳይንስ ንድፈ ሐሳብ ነው። በዚህም ላይ የፍጥረትን የለውጥ ሂደት እንጂ የመጀመሪያ ሕዋስ ከየት እንደ መጣና የፍጥረት ዓላማም ምን እንደሆነ ንድፈ ሐሳቡ የሚያውቀው ነገር የለም። ነገር ግን “ሳይንስ ነው” ተብሎ በየትምህርት ተቋሙ ይቀርባል። ታዲያ ይህ ንድፈ አሳብ እውነት ሆኖ ቢገኝ፣ ክርስትናን ፉርሽ ያደርጋልን?

“ኢንተለጀንት ዲዛይን” የሚባለው አማራጭ ብቅ የሚለው በዚህ ዐውድ ውስጥ ነው። ኢንተለጀንት ዲዛይን በአዝጋሚ ለውጥ ያምናል፤ በማይክሮም ሆነ በማክሮ ኢቮሊውሽን። ነገር ግን ፍጥረት በአዝጋሚ የለውጥ ሂደት ከአንድ ነገር ወደ ሌላው እየተለወጠ የመጣው በዕድልና በአጋጣሚ አይደለም። ይህ አማራጭ በክርስቲያናዊ ዕይታ ሲወሰድ፣ የፍጥረት ፈጣሪና የፍጥረት ባለቤት በሆነው በእግዚአብሔር የተመራ ሂደት ነው። እግዚአብሔር ፍጥረቱን አሁን ወዳለበት ስፍራ ለማምጣት አዝጋሚ ለውጥን ተጠቅሟል። የመጀመሪያውን ፍጥረት እግዚአብሔር ፈጠረ፤ ከዚያም በዘመናት ሂደት ይህ ፍጥረት በአዝጋሚ ለውጥ እየተለወጠ ሌሎቹን ፍጥረታት እንዲያስገኝ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ወደ ፍጥረቱ እየመጣ ለውጡን ይመራዋል፤ ያበጃጀዋል። ኢንተለጀንት ዲዛይነሩ እግዚአብሔር የፍጥረትን ለውጥ አሁንም እየመራ ነው። ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 በዚህ ውስጥ የራሱ ቦታ አለው። የሆነው ሁሉ የሆነው በዚህ መልኩ በእግዚአብሔር እየተመራ እዚህ ደርሷል። ስለዚህ አዝጋሚ ለውጥ እውነት ቢሆንም፣ የተካሄደው በዕቅድና በዓላማ ነው፤ ዐቃጁም ሆነ ፈጻሚውም ራሱ እግዚአብሔር ነው። በዳርዊንያዊው የአዝጋሚ ለውጥ ትንተና ግን ፍጥረት ዕቅድ ያለው ይመስላል እንጂ በጭራሽ በዕቅድ የተመራ አይደለም። አቃጅም የለውም።

የኢንተለጀንት ዲዛይን አቀንቃኞች ይህ ምልከታ ሳይንሳዊ ንድፈ ሐሳብ ነው ባዮች ናቸው። ምክንያቱም አስቀድሞ ፍጥረትን ይቃኛል (observation)፤ ከዚያም በቅኝቱ ላይ ተመሥርቶ መላምት ያቀርባል (hypothesize)፤ ለዚያም ማረጋገጫ የሚሆን ሙከራና ጥናት ያካሂዳል (experiment)፤ ከዚያም ድምዳሜውን ያቀርባል (conclusion)፤ ልክ እንደ የትኛውም ሳይንሳዊ ንድፈ ሐሳብ። ክርስቲያን የባዮሎጂ ባለሞያዎቹ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሙግታቸውን ያቀርባሉ (ከbacterina propulsion systems እስከ human DNA ድረስ ያሉት ሁሉ ኢንተለጀንት ዲዛይን መኖሩን የሚያሳዩ ናቸውና። እናም አዝጋሚ ለውጡ በዕቅድ የተካሄደ ነው።

በእግዚአብሔር መኖር የማያምኑ ዳርዊንያውያን ግን ኢንተለጀንት ዲዛይን ሳይንሳዊ ንድፈ ሐሳብ አይደለም ሲሉ በብርቱ ይቃወማሉ። ስለዚህ ኢንተለጀንት ዲዛይንን የሚቀበሉ ፈላስፎችና የባዮሎጂ ባለሞያዎች በምዕራቡ ዓለም ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተቀባይነት እንዳያገኙ፣ ሥራ እንዳይቀጠሩ፣ መሣቂያና መሳለቂያ እንዲሆኑ ብዙ ጥረት ይደረጋል። ከዚህም ባሻገር በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ክርክር ተካሂዶ (እስከ አገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ) ኢንተለጀንት ዲዛይን ሃይማኖታዊ እንጂ ሳይንሳዊ ንድፈ ሐሳብ ባለመሆኑ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በአማራጭነት ለተማሪዎች እንዳይቀርብ ተወስኖበታል።

አሁን ጥያቄው ለእያንዳንዳችን ነው። ፍጥረት በሚሊዮን ዓመታት ውስጥ ሂደት የተፈጠረ ቢሆንና ከአንዱ የፍጥረት ቤተሰብ ወደሌላኛው ለውጥ መኖሩ እውነት ቢሆን፣ ይህ የክርስትናን እውነትነት ያፈርሳልን?

እያየን እንጨምራለን።

https://t.me/PaulosFekadu
1.7K viewsedited  10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 10:59:43 ኢቮሊውሽን - ፪

(Dec. 19, 2019 የተጻፈ)

ዛሬ ደግሞ የምንመለከተው የምድርን ረጅም ዕድሜ የሚቀበለውን ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ነው፤ Old Earth creationism ተብሎ ይታወቃል። በዚህ ንድፈ ሐሳብ መሠረት የምድር ዕድሜ ሳይንሱም እንደሚለው በሚሊዮንና በቢሊዮን ዓመታት ሊቆጠር ይችላል። ከዚህ የተነሣ፣ በዚህ ጎራ ውስጥ ያሉ ወገኖች ፊዚክስን፣ ኬሚስትሪን፣ ጂኦሎጂን በሚመሳስሉ ጉዳዮች ከሳይንስ ጋር ዝምድና እንጂ ጠብ የላቸውም። ከሳይንስ ጋር ልዩነታቸው ያለው የሳይንስን ባዮሎጂ ነክ ትንታኔ፤ አዝጋሚ ለውጥን ባለመቀበል ነው። የዚህ ሐሳብ አቀንቃኞች ምድር ረጅም ዕድሜ እንዳላት ቢቀበሉም ወደዚህ መረዳት የደረሱባቸው የተለያዩ መንገዶች አሏቸው። አንድ ሁለቱን ዛሬ መመልከት እንችላለን።

የመጀመሪያዎቹ Gap theory ተብሎ የሚታወቀውን ንድፈ ሐሳብ ይቀበላሉ። ይኸውም በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 እና 2 መካከል እጅግ ረጅም የሆነ የዘመናት ክፍተት መኖሩን የሚያስብ ነው። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን መፍጠሩን ዘፍጥረት 1፥1 ይናገራል። የሚቀጥለው ቁጥር ግን ምድር ባዶ፣ ጨለማና አንዳችም ያልነበረባት መሆኑን በማስረዳት ይቀጥላል። እግዚአብሔር ግን ባዶና ጨለማ ምድርን አይደለም የፈጠረው። ምድር ምሉዕ ነበረች። እግዚአብሔር አሟልቶ ፈጥሯት በሰላም ለብዙ ዘመናት እየኖረች ሳለ፣ ከተፈጠሩት ኪሩቦች መካከል አንዱ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀና ከነግብረ አበሮቹ ወደ ታች ተወረወረ።

ይህ ኪሩብ፣ ማለትም ሰይጣን ከሰማይ ወደ ምድር ሲጣል ብዙ ምስቅልቅል ተከስቷል። በዚህም ምድር ተናግታለች፤ በላይዋ የነበረው ሁሉ አደጋ ደርሶበታል። ስለዚህ ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 2 “ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ” የሚለው ይህንኑ ነው። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር በሰይጣን ዓመፅ የተበለሻሸችውን ምድር እንደገና ሊያበጃጃትና ሊያስካክላት ሥራ ጀመረ። በዚህ ጎራ ያሉ ሰዎች በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 መካከል በሚሊዮን (ወይም በቢሊዮን) የሚቆጠሩ ዓመታት መኖሩን ስለሚያሰቡ በምድር ዕድሜ ጉዳይ ከሳይንስ ጋር ይስማማሉ።

ሌለኞቹ ደግሞ እግዚአብሔር ፍጥረቱን በፈጠረባቸው ስድስት ቀናት ትርጓሜ ላይ ያተኩራሉ። በዚህ ጎራ ሐተታ መሠረት በዘፍጥረት 1 ላይ “ቀን” የተባለው አሁን እንደምናውቀውን 24 ሰዓት ተደርጎ መታሰብ የለበትም። ቀን የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ዮም" ብዙ ዘመናትንም ሊወክል ይችላል። ለምሳሌ፣ መጽሐፍ ቅዱስ “የጌታ ቀን ይመጣል” እያለ ስለ መጨረሻው ቀን ሲናገር፣ 24 ሰዓት ስላለው ቀን እያመለከተ አይደለም። (እኛም ብንሆን “ቀን ወጣለት፣ ቀን መጣ፣ ቀን ይመጣል” እያልን ስንናገር 24 ሰዓትን እያሰብን አይደለም።) ስለዚህ በዘፍጥረት 1 ላይ እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረባቸው ቀናት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዓመታት ሊሆኑ ይችላሉ።

ኧረ እንዲያውም ምድራዊ ቀናት ላይሆኑም ይችላሉ፤ cosmic time እንጂ። (ፀሓይ ሳትፈጠርም ጭምር ቀናት ሲቆጠሩ እንደ ነበር ልብ ይሏል።) የጊዜ አቆጣጠሩ የዚህ ዓለም ካልሆነ ደግሞ አንዱ ቀን ለእኛ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታት ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሚሊዮን ዓመታት ውስጥ እግዚአብሔር እየመጣ፣ አስቀድሞ በፈጠረው ፍጥረት ላይ አንዳች ነገር እያከለ ማለትም እያበጃጀው ይሄዳል። ፍጥረት የተፈጠረው በዚህ መልኩ ቀስ በቀስ፣ ለውጥ እየተካሄደበት ነው። አሁን ያለው ነገር በሂደት የተበጃጀ እንጂ ከመጀመሪያው እንደዚሁ አይደለም የተፈጠረው። ስለዚህ እዚህኛው ውስጥ ያሉቱ እንደ ላይኞቹ በጂኦሎጂ፣ በፊዚክስና በኬሚስትሪ ብቻ ሳይሆን፣ በተወሰነ መልኩ ከባዮሎጂም ጋር ከሳይንስ ጋር ስምሙ ናቸው።

የምድርን ረጅም ዕድሜ የሚቀበሉቱ ክርስቲያኖች አዝጋሚ ለውጥን በሚመለከት micro evolution ይቀበላሉ እንጂ macro evolutionን አይቀበሉም። micro evolution በአንድ የፍጥረት ቤተሰብ (species) ውስጥ ብቻ የሚካሄድን ለውጥ ይመለከታል። ለምሳሌ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አዳምና ሔዋን ቢሆኑም፣ ቀስ በቀስ ጥቁር፣ ነጭ፣ ቀይ፣ ቡኒ ተብሎ የሚታወቅ የሰው ዘር መጥቷል፤ በሚኖሩባቸው ውስጣዊና ከባቢያዊ ሁኔታዎች ምክንያት። ይህም የሰውን ቁመት፣ የቆዳ ቀለም፣ የአፍንጫንና የከንፈርን ቅርጽ፣ የጠጉርን ዐይነት፣ ወዘተ. የለወጠ ሂደት ነው። አለዚያማ አፍሪካዊ፣ አረባዊ፣ ቻይናዊ፣ ሕንዳዊ፣ ላቲናዊ፣ ምዕራባዊ፣ እስያዊ … የሚባሉ መልኮች ከየት መጡ? በአዝጋሚ ለውጥ አይደለምን? ልክ እንደዚሁ ዐይነት ለውጦች በእንስሳትም ሆነ በተክሎች መካከል ተከስተዋል። ሁሉም ለውጦች ግን በአንድ የፍጥረት ቤተሰብ (species) ውስጥ ብቻ የተገደቡ ናቸው። ከአንድ ቤተ ሰብ ወደ ሌላኛው የተካሄደ ለውጥ የለም። እናም ከእንስሳ በአዝጋሚ ለውጥ ሰው ወደ መሆን ለውጥ አልተካሄደም። እናም እነዚህኞቹ በማይክሮ ኢቮሊውሽን ካልሆነ በቀር በማክሮ ኢቮሊውሽን ከሳይንስ ጋር አይስማሙም።

(በነገራችን ላይ የዘፍጥረት አንዱ “ቀን” 24 ሰዓት ላይሆን እንደሚችል ጥያቄ መነሣት የጀመረው ዛሬ አይደለም፤ በ4ኛው እና በ5ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ አውግስጢኖስም (St. Augustine) ይህንኑ ብሎ ነበር።)

የአገራችንን ክርስቲያኖችን በሚመለከት በዘፍጥረት 1፥1 እና 1፥2 መካከል ረጅም ዕድሜ መኖሩን የሚያምኑ በጣም ጥቂት ክርስቲያኖችን ዐውቃለሁ፤ የዘፍጥረት 1 ቀን 24 ሰዓት ላይሆን እንደሚችል የሚቀበሉም እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች አውቃለሁ። በስብከትም ሆነ በጽሑፍ ይህንኑ ለመግለጽ የደፈረ ግን አላጋጠመኝም።

እያየን እንጨምራለን።

https://t.me/PaulosFekadu
2.0K viewsedited  07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 21:33:42 ኢቮሊውሽን - ፩

( Dec. 16, 2019 የተጻፈ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማቱን ሲቀበሉ፣ የኖቤል ኮሚቴው ሊቀ መንበር ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን በማውሳት፣ “በዚህ ረገድ፣ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን” በማለት ተናግራ ነበር። ንግግሯ ጮቤ ካስረገጣቸው ሰዎች መካከል ክርስቲያኖችም አሉበት። ይህ ግን በአንዳንድ ወገኖች ላይ የጥያቄና የተቃውሞ ሰበብ ሆኖ ታይቷል። “ዓለም የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት የተቀበለው ከሉሲ በመነሣት ነው፤ ይህ ግን የሰው ልጅ በአዝጋሚ ለውጥ ከዝንጀሮ መሰል እንስሳ ወደ ሰው-ነት እንደ ተቀየሩ ለሚያስቡቱ እንጂ ለክርስቲያኖች የሚመጥን አይደለም። እናስ እንዴት ክርስቲያን በዚህ ይደሰታል?” የሚሉ ሐሳቦች እየተወረወሩ ነበር።

ስለዚህም በክርስቲያናዊ አስተምህሮ እና በአዝጋሚ ለውጥ አስተሳሰብ መካከል ያለው መስተጋብር ምን እንደሚመስል ውስን ሐሳቦችን በዚሁ አጋጣሚ ማንሣቱ ተገቢ ይመስለኛል። (በነገራችን ላይ ብዙዎቻችን ሉሲ ጋ ቆመናል እንጂ፣ የሉሲ ታላቅ የሆነችው አርዲን ያስታወስናት አልመሰለኝም።)

ጥንተ ፍጥረትን በሚመለከት ከሚቀርቡ ክርስቲያናዊ አስተሳሰቦች መካከል የምድርን ወጣትነት የሚያወሳውን ለዛሬ እንመለከታለን፤ ከነስሙም “Young Earth” በመባል ይታወቃል። በዚህ አስተሳሰብ መሠረት የምድር ዕድሜ ከ6 ሺህ እስከ 10 ሺህ ዓመት ቢሆን ነው። ይህም የሚሆንበት ምክንያት እግዚአብሔር ፍጥረትን የፈጠረባቸው በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ላይ ያሉት 6 ቀናት እያንዳንዳቸው 24 ሰዓት ያላቸው ቀናት ተደርገው ስለሚታሰቡ ነው። ስለዚህ ምድርና ሞላዋ የተፈጠሩት በ6 ቀናት ውስጥ ነው። ከዚያ አዳም ከኖረበት ዕድሜ በመነሣት፣ የሌሎችንም ዕድሜ ደማምረው በሺ የሚቆጠሩ ዓመታት ላይ ይደርሳሉ። በዚህ ጎራ ውስጥ ያሉ ሰዎች አዳም ከውድቀት በፊት የነበረውን ዕድሜም ከግምት የሚከትቱ አይመስለኝም። ስለዚህ ይህን ሐሳብ የሚቀበሉ ሰዎች፣ ሳይንስ የምድርን ዕድሜ (እናም የመላለሙን) በሚሊዮኖችና በቢሊዮኖች ማስላቱን ከቅጥፈት ይቆጥሩታል። የቅሪተ አካላት ግኝትንም በጭራሽ አይቀበሉም።

ፍጥረታት ሲጠኑ ከዕድሜያቸው በላይ የሚመስሉት ከመጀመሪያም "ባለ ትልቅ ዕድሜ" ሆነው ስለ ተፈጠሩ ነው። ለምሳሌ አዳም የተፈጠረው ለአካል መጠን የደረሰ ሰው ሆኖ እንጂ ጨቅላ ሆኖ አይደለም። የዚያን ቀን (ወይም በማግስቱ) ዕድሜው 1 ቀን ብቻ ቢሆንም፣ ሲታይ ግን ጎልማሳ ነው። ሔዋንም በተፈጠረችበት የመጀመሪያ ቀኗ ላይ ለአካለ መጠን የደረሰች ኮረዳ ነበረች። ስለዚህ አዳምና ሔዋንን አግኝቶ የሚመራመር ሰው በምድር ላይ ከኖሩበት ዕድሜያቸው በላይ ነው የሚገምታቸው።

ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር ተራራውን፣ ሸለቆውን፣ ዐለቱን፣ ወንዙን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትን ሲፈጥር ሚልዮን ምናምን ዓመታት የሞላቸው አድርጎ ፈጥሯቸው ቢሆንስ? ልክ አዳምና ሔዋንን ዐዋቂ ሰዎች (adults) አድርጎ እንደ ፈጠራቸው ማለት ነው። በዚህም ላይ የጥፋት ውሃ መከሰት አንዳንድ መልክዐ ምድሮች ከትክክለኛው ዕድሜያቸው በላይ የተጋነነ ዕድሜ ያላቸው እንዲመስል ማድረጉን ለዚህ በማስረጃነት የሚጠቅሱ ሰዎችም አሉ። ለእነዚህ ሰዎች አዝጋሚ ለውጥ ብሎ ነገር አንዳችም እውነትነት ስለ ሌለው፣ ሰዎችም ሆኑ እንስሳት ከሺዎች ዓመታት በፊት ሲፈጠሩ የነበራቸው መልክ ይዘው ቆይተዋል እንጂ ከቶ አልተለወጡም። ስለዚህ ምድር ከተፈጠረች ገና 6 ሺ ዓመታት ገደማ ነው።

በአገራችን በርካታ ወንጌላውያን ክርስቲያኖች ምድባቸው እዚህኛው ጎራ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም። እንዲያውም የምድርን ዕድሜ ወደ 10 ሺውም አያደርሱትም። በየስብከቱም የምንሰማው ይህንኑ ነው፤ ምድር ከተፈጠረች 6 ሺህ ዓመቷ እንደ ሆነ ስለ ደቀ መዝሙርነት ባሳተመው መጽሐፉ ላይ የጠቀሰ መጋቢም ዐውቃለሁ። ኦርቶዶክሳውያኑም ቢሆን፣ ከአዳም እስከ ክርስቶስ 5 ሺህ ዓመት፣ ከክርስቶስ በኋላም 2 ሺህ ዓመት ስለ መሆኑ በይፋ ያስተምራሉ። ስለ 8ኛው ሺህ የሚያቀርቡት ንግርትም ከዚህ ጋር አንዳች ትይይዝ አያጣውም።

ለማንኛውም፣ እዚህ ሰፈር የለሁበትም!

እያየን እንጨምራለን።

https://t.me/PaulosFekadu
2.5K viewsedited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 13:23:18 “እንግዶቹን አማልክት” (ዘፍ. 35፥2)

“እንግዶችን አማልክት” (ዘፍ. 35፥4፤ ኤር. 11፥10)

“የማታውቋቸውን አማልክት” (ዘዳ. 11፥28)

“የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት” (ዘዳ. 13፥2)

“የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት” (ዘዳ. 13፥6)

“የማታውቋቸውን ሌሎችን አማልክት” (ዘዳ. 13፥12)

“ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት” (ዘዳ. 28፥64)

“እንግዶች አማልክት” (ኢያሱ 24፥23፤ 1ሳሙ. 8፥8፤ ኤር. 7፥9)

“እንግዶች አማልክትን” (1ሳሙ. 7፥3)

“የእንግዶቹንም አማልክት” (2ዜና 14፥3)

“እንግዶችንም አማልክት” (2ዜና 33፥15)

“የማታውቋቸውን እንግዶች አማልክት” (ኤር. 7፥9)

“እንግዶች አማልክት” (ኤር. 7፥9)

* * *

“እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።” (ዮሐ. 4፥22)

"ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን" (1ዮሐ. 1፥1-2)

https://t.me/PaulosFekadu
2.0K viewsedited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:18:22 ቻርልስ ሲምፕሰን የተባሉ የቤተ ክርስቲያን መሪ ስለ መሪነት ሲናገሩ ይህን ገጠመኛቸውን ያነሣሉ።

* * *

መኪና ተከራይቼ ወደ ሎስ አንጀለስ አየር ማረፊያ የነዳሁበት ያ ቀን ትዝ ይለኛል። ከዚህ በፊት መንገደኛ ሆኜ ባውቀውም መኪና እየነዳሁ ለመሄድ ግን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበር። ባለ ስድስት መስመር ፈጣን አውራ ጎዳና ውስጥ ገብቼ ሳሽከረክር ባለቤቴ የከተማውን ካርታ ይዛ ትረዳኝ ነበር። ብዙ ከሄድን በኋላ ነው ራሱን ሎስ አንጀለስን ዐልፌ እንደ ወጣሁ ያወቅሁት።

“ምንም አይደል፤ በቂ ጊዜ አለን” አልኩና ከዋናው መንገድ ፈቀቅ ብዬ ቀይ መብራት ያቆመውን ነጂ “ወደ አየር ማረፊያው የምደርሰው እንዴት ነው? ብዬ ጠየቅሁ። “ወደ ኋላ ዙርና ወደ ደቡብ ሂድ፤ የሚቀጥለውን ዋና ጎዳና በቀኝ በኩል ያዝና ብዙ ኪሎ ሜትር ወደ ፊት ሂድ፤ አታጣውም” አለኝ።

ዞረን ወደ ደቡብ ሄድን፤ የሚቀጥለውን ቀኝ ያዝንና ብዙ ነዳን፤ ግን ኤርፖርቱ የለም። ቀኑ እየመሸ መጣ፤ ጊዜም እያነሰ ነው። አውሮፕላኖቹ የሚበርሩበት አቅጣጫ ምናልባት ይመራኝ ይሆን? ስል አሰብኩ፤ ግን እርሱም አልሠራም።

ከዋናው መንገድ እንደገና ወጣሁና “የቤንዚን ማደያው ሠራተኛ ሊረዳኝ ይችላል” ብዬ ወደ ማደያው መኪናዬን አስጠጋሁ፤ ቦታው ጨለምለም ብሏል።

“እባክዎ ሊረዱኝ ይችላሉ …?"

እኔ እንግሊዝኛ ስናገር እርሱ በስፓኒሽ ይመልስልኝ ጀመር።

“ሌላ የሚረዳኝ …?"

ምንም መግባባት አልተቻለም፤ ስፓኒሾች ሰፈር ነበር የገባነው። ቦታው እንደ ጠፋኝ በደንብ ገባኝ። “ምነው የማውቀው ባይመስለኝ ኖሮ” አልኩና በልቤ፣ አንድ መንገድ ላይ ስንወጣ መብራት አቆመን።

“እባክዎን ወደ ሎስ አንጀለስ አየር ማረፊያ እንዴት እንደምንደርስ ሊነግሩኝ ይችላሉ?” አልኩና አጠገቤ የነበረውን ሌላ አሽከርካሪ ጠየቅሁ።

“ተከተለኝ” አለኝና እንደ ረፈደብኝ ያወቀ ይመስል ይከንፍ ጀመር። ሰውዬውን አላውቀውም፤ መንገዱን ማወቁንስ በምን ዐውቃለሁ? አንድ ነገር ግን ርግጥ ነበረ፤ መንገዱን እኔ አለማወቄ። እርሱ ወደ ቀኝ ሲዞር እኔም ወደ ቀኝ፤ ወደ ግራ ሲዞር እኔም ወደ ግራ፣ ቢጫ መብራት ሲጥስ እኔ ቀይ እየጣስሁ፣ ሲያፈጥን እያፈጠንሁ የእርሱን ጅራት እንደ ተከተልሁ ከዐሥር ደቂቃ ግስገሳ በኋላ የሎስ አንጀለስ አየር ማረፊያ ላይ ከቸች ስንል መንግሥተ ሰማይ የገባሁ ነው የመሰለኝ። ምስጋናዬን በታላቅ ፈገግታ ገልጬ ተሰናበትኩትና ወደ አውሮፕላኑ አመራሁ፤ ለጥቂት ሳይዘጋ ደረስሁ።

መሪነት ምን እንደ ሆነ የገባኝ ያን ቀን ነው። መሪነት የሩቅ ጥቆማ አይደለም፤ መሪነት ማመላከት አይደለም፤ መሪነት ወደሚፈለገው ግብ ራስ ሄዶ ማሳየት ነው።

(በንጉሤ ቡልቻ ከተጻፈው “ወቅታዊ ዘላለማዊ” ከተሰኘ መጽሐፍ የተወሰደ፤ ገጽ 90-91።)

https://t.me/PaulosFekadu
960 viewsedited  10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 12:53:48

979 views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 15:03:14 “አገር ተረጋግቷል
በደሊላ ጭን ላይ
ሳምሶን እጅ ሰጥቷል።”
ትላላችሁ አሉ፤
የተላጩት ፀጉሮች
እልፍ እሾሆች ሆነው
ብቅ ብቅ እያሉ።

(ደረጀ በላይነህ - የዕድሜ መንገድ)
674 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ