Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቶስን ማወቅ ፕሮቴስታንት የሚባል ኅይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጉዳይና ናፍቆት ነ | ናዝራዊ Tube

ክርስቶስን ማወቅ ፕሮቴስታንት የሚባል ኅይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፍጥረት ሁሉ ጉዳይና ናፍቆት ነው::

ፍጥረት ሁሉ የጎደለው ክርስቶስን ከማወቅ ነው ስለዚህም ፍጥረት ሁሉ የሚሞላው ክርስቶስን በማወቅ ነው::

ፍጥረትን እንዳለ የሚፈውሰው ክርስቶስን ማወቅ እንጂ የሆነ ፖለቲካዊ ርዕዮተ-አለምን ማወቅ አይደለም: ፍጥረት በሰው ፍልስፍና አይድንም በእግዚአብሔር "ፍልስፍና" እንጂ - እርሱም ክርስቶስ::

Knowing Christ is the apex of the whole creation.

ጳውሎስ:-

"እርሱንና የትንሳኤውን ኃይል እንዳውቅ . . . ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን ተጎዳሁ"

". . . ክርስቶስን ታውቁ ዘንድ እጋደላለሁ"

". . . ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው"

መልካም ዕለተ እሁድ ለሁላችን::
ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube