Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-20 21:50:42
የምድሪቱ ግፍ ወደ ጸባኦት ይጮኻል!

“ሙሴ” ፈርዖን ስለሆነ እግዚአብሔር የግብጽ አምላክ አይሆንም!

“ሙሴ” ፈርዖን ሲሆን የከፋ ነው፣ ቋንቋው የአይሁዶች ነው፣ ጭቆናው ግን የግብጾች ነው፣ የማይቀረው መቅሰፍት የሚመጣበት ግን ከተጨቋኞቹ አምላክ ከግዚአብሔር ነው፣ በዚህም ዘመን ያለ ጭድ ጡብ አምጣ የሚባል፣ በመብዛቱ ይወርሰናል ተብሎ የተፈራ፣ በትውልዱ ላይ የመጥፋት ዘመቻ የታወጀበት ሕዝብ አለ።

ነገር ግን፣ ልክ እንደ ድሮው፣ ዘንድሮም ጩኸት የሚሰማ፣ ወርዶ የሚያወርድ፣ የባሪያዎች አምላክ አለ! ህዝቡን “ልቀቅ“ የሚል፣ ጨቋኙን ለይቶ ለተጨቋኝ ራርቶ፣ መቃን ደም ቀብቶ፣ መናብርት ሳይፈራ በኩር የሚመታ አስር መቅሰፍት አለ፣ መቅሰፍት አለ፣ መቅሰፍት አለ! “ሙሴ” ፈርዖን ስለሆነ እግዚአብሔር የግብጽ አምላክ አይሆንም!

መጋቢ ሰለሞን ጥላሁን
@nazrawi_tube
755 viewsΒενιαμίν, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 00:25:50 ክርስቲያን የሆናችሁ ተፋቃሪዎች የፍቅር ግንኙነታችሁ እንደ እግዚአብሔር ቃል በቅድስና ሲሆን በመካከላችሁ የእግዚአብሔር ደስታ ይፈፀማል!

@Biblicalmarriage
879 viewsAbrish, 21:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 19:03:26 ዕለተ ዓርብ - ስቅለት፤ ሞት፤ ጨለማ፤ ስርየት

ጌታ፣ "ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ። ተከዳ፤ ተሸጠ፤ ተተወ፤ በአንድ ወቅት ይከተለው የነበረውና “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፤” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤” “ሆሣዕና በአርያም!” እያለ ያከበረው ሕዝብ “ይሰቀል!” በማለት አሳልፎ ሰጠው፤ ልብሱን ተገፈፈ፤ የእሾኽ አክሊል ተደፋበት፤ በወንበዴዎች መካከል ተሰቀለ፤ ተሰደበ፤ ተሾፈበት፤ ተጨነቀ፤ ተሠቃየ፤ እንደ ጠቦትም ለዕርድ ተነዳ፤ በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም፤ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ፤ ጨለማ ወረሰው!

መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር። የመስዋዕቱም በግ፣ ካህንም ሆነና ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው። ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ ተሠቃየም፤ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ። ለአሰቃዮቹ ሁሉ፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ጣር ውስጥ ማለደ። የፍጥረት ፈጣሪ፣ ተጠማ፤ በታላቅ ድምፅ ጮኾ፤ ነፍሱን ሰጠ፤ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፤ የዘላለም ቤዛነት ሊያስገኝ የራሱን ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ፤ ድነት ኾነ! በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

ዕለተ ቅዳሜ - መቃብር፤ ታላቅ ዝምታ

አምላክ ወደ መቃብር ወረደ፤ “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም!” ተባለ። "የታመነበት እግዚአብሔር ትቶታል" ተባለ፤ ስለራሱ የተናገረው ሐስት፣ የሰጠውም ተስፋ መና ነበር ተባለ። በልመና በድኑ ተቀበረ! በትልቅ ድንጋይ የመቃብሩ በር ተዘጋ፤ መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት፤ ታሪኩ ተዘጋ፤ ፍርሃት ወደቀ፤ ላመኑበትና ለተከተሉት ጨለማ ኾነ፤ እግዚአብሔር ዝም ያለ፣ ሞትም ለዘላለም የነገሠ መሰለ፤ ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ። ታላቅ ዝምታ ኾነ!

ዕለተ እሁድ - ትንሣኤና ሕያው ተስፋ

እንደ ተናገረው ተነሣ፤ ድንጋዩ ተንከባለለ፤ መቃብሩ ባዶ ኾነ፤ በፈቃዱ ነፍሱን ሰጠ፤ እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አስወግዶ አስነሣው፤ ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለምና! ግዛትን፣ ሥልጣንና ኀይልን ሁሉ ደመሰሰ፤ ጨለማው ነጋ! ልቅሶ በደስታ ተለወጠ፤ ፍቅር አሸነፈ፤ ወዳጆቹን ፍለጋ ሄደ። በፍርሃት በተዘጋ ደጅ የለበሩት “ሰላም ለእናንተ ይሁን አለ!” ስብራታቸው ጠግኖ፣ ተስፋቸውንም አድሶ ወደ ዓለም ሁሉ ላካቸው። ከአምላክ ጋር ዕርቅ ሆነ፤ ድነታችን ሙሉ ኾነ፤ ተስፋችንም ዘላለማዊና ሕያው! ያለ ትንሣኤው፣ ክርስቶስ ሰማዕት፣ መልክታችንም ታሪክ ብቻ ነበር የሚሆነው! ሞት በድል ተዋጠ፤ የሞት መንደፊያ ኀጢአት ተወገደ፤ ሰይጣን ተረታ። እንደ ተናገርው ሞተ፤ እንደ ተናገረው ተነሣ፤ እንደ ተናገረው ወደ ሰማይ ዐረገ፤ እንደ ተናገረው መንፈስ ቅዱስን ላከ፤ እንደ ተናገረው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር አለ፤ እንደ ተናገረው በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ፣ በክብር ይመለሳል!

እንደ ግል አማኝ፣ እንደ ቤተ ሰብ፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን፣ እንደ አገር የምናልፍባቸው ብዙ የፈተና ወቅቶች አሉ። በእግዚአብሔር የተተውን፣ እርሱም የማያየን፣ ዝም ያለን፣ እንዲሁም ይህቺ ምድር ለክፉዎች ዐልፋ የተሰጠች እስኪመስል ድረስ የፍትሕ ጨኸት የማይሰማበት፣ ክፋት ያሸነፈና ሰይጣን ለዘላለም የነገሠ የሚመስልባቸው የተስፋ መቁረጥ፣ የዝምታና የጨለማ "ዓርቦችና ቅዳሜዎች" አሉ።

ሆኖም፣ "ዓርብና ቅዳሜ" የመጨረሻ ቃሉች አይደሉም! የእኛም ኾነ የመላ ዓለሙ ታሪክ በእነዚህ ሁለት ቀናት በሆኑ ኹነቶች አልተቋጨም። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተነሥቶአል! ስለዚህ ይቅር መባላችን፣ የዘላለም ሕይወት ማግኘታችን፣ የትንሣኤ ተስፋችን፣ ከአቤል ጀምሮ እስከ አሁን እየፈሰሰ ያለው የንጹሓን ደም ጩኸት ምላሽ ማግኘቱ፤ መከራ መወገዱ፤ እንባ መታበሱ፣ ኀጢአት፣ ሞትና ሰይጣን ለዘላለም መወገዳቸው፣ በመጨረሻም አዲስ ሰማይን አዲስ ምድር የማየታችን ተስፋዎች እውነት ናቸው። እንደ ተናገረው ይመለሳል!

“እነዚህን ነገሮች የሚመሰክረው፣ “አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ና። የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይሁን፤ አሜን።” (ራእይ 22:20-21)

መልካም የትንሣኤ በዓል!
Dr. Girma bekele
@nazrawi_tube
475 viewsΒενιαμίν, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 10:10:29 ኢየሱስ በየትኛው ቀን ነው የተሰቀለው? . . . ከሞተ በኋላስ የት ነበር? (ኢ. ማ.)

ይህ አሳብ አምና በጥቂቱ፥ ዘንድሮ በመጠነኛ ስፋት የተወሳ አሳብ ነው። አምና ከተንሸራሸሩት አሳቦች ሌላው፥ 'ኢየሱስ ከሞተ በኋላ እስከ ትንሣኤው የት ነበር?' የሚለው ነው።

‘በየትኛው ቀን ተሰቀለ?’ ለሚለው፥ ነጥቡ ኢየሱስ ዐርብ ተሰቅሎ እሁድ ማለዳ ከተነሣ እንዴት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይሆናል? የሚል ነው። አንዳንድ ሙስሊሞችም ይህንን የሰማይ ስባሪ እመሬት ላይ እንደወደቀ አድርገው ያዳንቁታል። ከሙስሊሞች ጋር ስለዚህ ጉዳይ ስነጋገር፥ ‘ሲጀመር በትንሣኤው ታምናላችሁ ወይ?’ ብዬ እጠይቃቸዋለሁ። እንደማያምኑ የታወቀ ነው። እንደማያምኑ ከተናገሩ፥ ‘ስለ ቀኑ ሳይሆን ስለ ትንሣኤው እንነጋገር፤ ስለ ትንሣኤው ካላመናችሁ ስለምን ስለ ቀኑ እንከራከራለን?’ በማለት ወደ ዋናው ጉዳይ እሄዳለሁ። ለነገሩ የቁርኣኑ ዒሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ኢየሱስ አይደለም። ሆኖም አያውቅም። ስለዚህ ጉዳይ ያዘጋጀሁት መጽሐፍ እዚህ ይገኛል፤ https://t.me/zelalemmengistu/462

ወደ ቀኑ ስንመጣ፥ በወንጌላት ውስጥ ቀኑ የትኛው መሆኑ አልተጻፈም። ጥያቄውን ከሁለት አንጻር መመልከት እንችላለን።

1. በአይሁድ አንድ ሙሉ ቀንም የቀን ሽራፊም እንደ ቀን ነው የሚቆጠረው። ዐርብ፥ ቅዳሜ፥ እሑድ ሙሉም ጎዶሎም ሆነውም እንደ ሦስት ቀን ይቆጠራሉ። ዕድሜያችንን ስንቆጥር ወር አንቆጥርም። ዓመቱ ሊያልቅ አንድ ወር ወይም አንድ ቀንም ቢቀረው ቀጣዩን ዕድሜ አንቆጥርም። ከዓመቱ አንድ ወር ወይም አንድ ቀን ብቻ ቢያልፍም ለአሮጌው ይቀርባል ብለን በአሮጌው አንቆጥርም። ይህም ልክ እንደዚያ ነው። ይህ አንደኛው አሳብ ነው።

2. ሁለተኛው፥ በወንጌላት ውስጥ ቀኑ የትኛው መሆኑ አልተጻፈም ብያለሁ። ጸሎተ ኀሙስ፥ ስቅለተ ዕርብ የምንለው ከትውፊት እንጂ ቀኑ ይህ ነው ተብሎ አልተጻፈልንም። የመዘጋጀት ቀን መሆኑ፥ ሉቃ. 23፥54፤ የሰንበት ዋዜማ መሆኑ፥ ማር. 15፥42 በዮሐ. 19፥31 የማዘጋጀት ቀን መሆኑ ተጽፎልናል። ዮሐንስ ስለዚያ ቀን ሲናገር ከዚያም የበለጠ ብሎአል፤ አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት። ብሎአል። ἦν γὰρ μεγάλη ἡ ἡμέρα ἐκείνη τοῦ σαββάτου• ነበረና ትልቅ ቀን ያ ሰንበት።

የአይሁድ ፋሲካ በአዲሱ ዓመታቸው የመጀመሪያ ወር 14ኛ ቀን ነው የሚከበረው፤ ዘሌ. 23፥5፤ ዕዝ. 6፥19፤ ሕዝ. 45፥21።በተለያዩ ምክንያቶች በቀኑ ማክበር ያልቻለ እንዲያውም በሁለተኛ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ያከብረዋል፤ ዘኁ. 9፥1-14፤ 2ዜና 30፥1-18። የአይሁድ ወር ጨረቃዊ ወር ነውና ይህ ቀን ሁሌም በአንድ ቀን ላይ አያርፍም። ፀሐያዊ ወርም እንኳ ቢሆን በአንድ ቀን አያርፍም። ስለዚህ የአይሁድ ፋሲካ የግድ በአንድ ቀን እንደሚያርፍ አድርገን መጠበቅ የለብንም። ፋሲካ የበዓል ቀን እንጂ የሰንበት ቀን አይደለም።

ሌላው፥ ትልቅ ሰንበት ወይም ታላቅ ሰንበት የተባለ ሰንበት በብሉይ ኪዳን አንድ ብቻ ሆኖ ተጠቅሶአል። የተለመደው የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነና ቀናቸው የሚጀምረው ከምሽት ጀምሮ ስለሆነ፥ ስቅለት ዐርብ እንደሆነ መውሰዱ አግባብ ነው። ሰንበት ማለት ትርጉሙ ማረፍ ነው። ሰባተኛው ቀን ስለሆነም ሰባት ማለትም ነው። ከሰባት ይልቅ ግን ትርጉሙ ማረፍ ወይም ከሥራ መታገድ ነው። አይሁድ ከሰባት ቀናት በአንዱ ማረፍን ያርፋሉ። በአይሁድ ከሰባቱ ቀናት ሌላ ሰንበት የተባለ ቀንም አለ። በሰባት ዓመት የሚከበር የዓመት ሰንበትም አለ። በዚህኛው ሰው ብቻ ሳይሆን ምድሪቱም ሰንበት አድርጋ ታርፋለች አትታረስም። በ50ኛው ዓመት የሚከበር የኢዮቤልዩ ዓመትም አለ። ስለ ተለየ የሰንበት ቀን በዘሌ. 16 እናገኛለን። ይህ ሰንበት የስርየት ቀን የተባለው ቀን ነው። ቀኑ በሰንበት (ወይም ሰባተኛ) ቀን ዐረፈም አላረፈም ሰንበት ይባላል። ከሳምንቱ በየትኛውም ቀን ቢያርፍ ሰንበት ይባላል። ይህኛው ቀን የሚውለው ሰባተኛው ወር እና አሥረኛው ቀን ነው፤ ዘሌ. 16፥29-31። ይህ ቀን በዓመት አንዴ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚገባበት ቀን ነው። ያ ቀን የተለየ ሕዝባዊ ወይም ብሔራዊ የስርየት ቀን ነው።

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ያ የስቅለት ዕለት ከዚያ ቀን ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ያስባሉ። ቀኑ שַׁבָּתוֹן שַׁבָּת ሻባት ሻባቶውን ተብሎአል፤ ሰንበተ ሰንበት ማለት ነው። በዘሌ. 16፥31 ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፥ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው። የተባለው ቀን ነው። ይህ ቀን ሁሌም ሰባተኛ ወር አሥረኛ ቀን ስለሆነ ሰኞ ወይም ረቡዕ፥ ወይም ቅዳሜም ሊውል ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ትልቅ ሰንበት የፋሲካ ሰንበት ሊሆን አይችልም። ፋሲካ በሰባተኛው ሳይሆን በአንደኛው ወር ነው የሚከበረውና።

እንግዲህ ኢየሱስ የተሰቀለው የፋሲካ ቀን፥ ልብ እንበል ፋሲካ የምንለው በጉ የሚታረድበት ቀን ነው፤ በተለምዶ ስቅለተ ዐርብ እንበል እንጂ ፋሲካ ዐርብ ነው መባል የነበረበት። ይህ ቀን ታዲያ የግድ ዐርብ ነው ማለት አይደለም። ረቡዕ ወይም ኀሙስም ሊሆን ይችላል። ከሆነ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ከዚህ አንጻርም ሲታይ ስሌቱ ትክክል ሊመጣ ይችላል።

. . . . .

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ የት ነበር የቆየው?

ኢየሱስ ወደ ሲዖል ወረደ፤ በዚያም ተሰቃየ፤ አጋንንት ሲሳለቁበት፥ ሲጫወቱበት ቆይተው በዚያ ዳግም ተወልዶ በሦስተኛው ቀን ተነሣ ብለው ኑፋቄ የሚያስተምሩ አሉ። በአጋንንት መሰቃየቱና ዳግም መወለዱን እንተወው፤ የራሳቸው እኩይ ፈጠራ ስለሆነ። ወደ ሲዖል መውረዱን ከወዴት አገኛችሁት ብለን እንጠይቅና ከዚያ ለመልሳቸው ምላሽ መስጠት ይቻላል። በብሉይ ኪዳን ቋንቋ ሲዖል (שְׁאוֹל ሽዖውል) የኃጢአተኞች የስቃይ ፍጻሜ ስፍራ ከመሆን ጋር፥ መቃብር ከማለት ጋርም አንድ ነው። ለምሳሌ፥ ያዕቆብ፥ ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። ሲል (ዘፍ. 42፥38) ወደ ሲዖል ወረደ ማለት አይደለም፤ ሞቶ ተቀበረ እንጂ። ኢየሱስም ሞቶ ተቀበረ እንጂ ወደ ሲዖል ወረደ ተብሎ አልተጻፈም።

ይህንን ጥያቄ በሉቃ. 23፥43 ከተጻፈው መመለስ ይቻላል። ኢየሱስ አብረውት ተሰቅለው ከነበሩት አንዱ ለተናገረው ሲመልስ፥ ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው። ተብሎ ተጽፎአል። ኢየሱስ በገነት እንደሚሆን ከተናገረና እነዚህ በሲዖል ሦስት ቀን ቆየ ካሉ ማንን እንስማ? አሳቾቹን ከሰማን ሲዖል ማለት እና ገነት ማለት አንድ ናቸው ማለት ነው።

ዘላለም መንግስቱ
@nazrawi_tube
704 viewsΒενιαμίν, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 10:09:54

ጥያቄ????

መልስ
593 viewsΒενιαμίν, edited  07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:29:37 እዝራ ንጉሴ
new song

"የተነሣ ጠፋ እንጂ፣ የሞተማ ስንት አለ!"




መልካም የትንሣኤ በዓል!
@nazrawi_tube
602 viewsΒενιαμίν, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:19:40 እየነደደ አበራልኝ
eyob ali
New song

@nazrawi_tube
613 viewsΒενιαμίν, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 08:19:21
"... ውርደታችን ጥልቅ ስለ ኾነ አዳኛችን ምርጥ መኾን አለበት። በብርቱ ስለ ተሰበርን ድንቀኛ በኾነ መንገድ መጠገን አስፈልጎናል። ይህን እውን ለማድረግም እግዚአብሔር ምርጡን ብላቴናውን አዘጋጅቶ ወደ ዓለም ልኮታል። “እኛም አይተናል፤ አባትም ልጁን የዓለም መድኀኒት ሊኾን እንደ ላከው እንመሰክራለን” (1ዮሐ. 4፥14)።

Solomon Abebe Gebremedhin
@nazrawi_tube
745 viewsΒενιαμίν, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:21:28 ብቻ /// Sola
*Hanna tekle*
*New song*

@nazrawi_tube
975 viewsΒενιαμίν, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:22:23 ይሄን ቪዲዮ በእንባ ሆኜ ካየው በኋላ ክርስቶስን ይበልጥ ወደድኩት
"ዘ ፓሺን ኦፍ ዘ ክራይስት"
የተሰኘው ክርስቶስ ለእኛ የከፈለውን ዋጋ የሚያሳይ ፊልም

አውርዳችሁ ተመልከቱ ሼርም አድርጉ
@nazrawi_tube
1.2K viewsΒενιαμίν, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ