Get Mystery Box with random crypto!

የምድሪቱ ግፍ ወደ ጸባኦት ይጮኻል! “ሙሴ” ፈርዖን ስለሆነ እግዚአብሔር የግብጽ አምላክ አይሆንም | ናዝራዊ Tube

የምድሪቱ ግፍ ወደ ጸባኦት ይጮኻል!

“ሙሴ” ፈርዖን ስለሆነ እግዚአብሔር የግብጽ አምላክ አይሆንም!

“ሙሴ” ፈርዖን ሲሆን የከፋ ነው፣ ቋንቋው የአይሁዶች ነው፣ ጭቆናው ግን የግብጾች ነው፣ የማይቀረው መቅሰፍት የሚመጣበት ግን ከተጨቋኞቹ አምላክ ከግዚአብሔር ነው፣ በዚህም ዘመን ያለ ጭድ ጡብ አምጣ የሚባል፣ በመብዛቱ ይወርሰናል ተብሎ የተፈራ፣ በትውልዱ ላይ የመጥፋት ዘመቻ የታወጀበት ሕዝብ አለ።

ነገር ግን፣ ልክ እንደ ድሮው፣ ዘንድሮም ጩኸት የሚሰማ፣ ወርዶ የሚያወርድ፣ የባሪያዎች አምላክ አለ! ህዝቡን “ልቀቅ“ የሚል፣ ጨቋኙን ለይቶ ለተጨቋኝ ራርቶ፣ መቃን ደም ቀብቶ፣ መናብርት ሳይፈራ በኩር የሚመታ አስር መቅሰፍት አለ፣ መቅሰፍት አለ፣ መቅሰፍት አለ! “ሙሴ” ፈርዖን ስለሆነ እግዚአብሔር የግብጽ አምላክ አይሆንም!

መጋቢ ሰለሞን ጥላሁን
@nazrawi_tube