Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-03-26 08:16:02 ፍየል የሚመራቸው በጎች

አንዳንዶቻችሁ ምናልባት እንደምታውቁት ተወልጄ ያደግኩበት አካባቢ (ወላይታ) በSIM ሚስዮናዊያን አማካይነት ወንጌል በቀዳሚነት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። አስታውሳለሁ ልጅ እያለሁ አማኞች በእኛ አካባቢ ውሻና ፍየል አያረቡም ነበር። ውሻ በሐሰተኛ መምህራን የተመሰለው ችግር ቢኖርበት አይደል? ብለው ነው። (ከውሾች ተጠበቁ ይላል) "እርኩስ ነው" ተብሎ ይታመናል። ፍየል የማያረቡበት ምክንያት ደግሞ በስተመጨረሻ በግራ በኩል ይሆናሉ የሚለውን አንብበው ነው። ከዚያም ባሻገር ፍየል በባሕርዩ ቀበጥ፣ ስግብግብ፣ ሴሰኛ፣ ነገር ነው ተብሎ አይወደድም።

በግ እንደሚታወቀው የዋህ፣ በእረኛው የሚታመን፣ የእረኛውን ድምጽ የሚሰማ፣ የሚከተል፣ የተረጋጋ ፍጥረት ነው። መዝ 23 የእረኛውን መግቦት ብቻ ሳይሆን የበጎቹንም እርጋታ (መርካት መቻል) የምናይበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። ክርስቲያኖች በበጎች ተመስለዋል ክርስቶስ የበጎች እረኛ መሆኑን ተናግሮአል። በግ በፍጥረቱም ገመናውን ሸፍኖ እርቃኑን ሳይገላልጥ የሚኖር ቡሩክ እንስሳ ነው።

ስለ ፍየል በደንብ አላጠናሁም ግን በጎችን መምራት የሚያስችል የሞራል ብቃት የለውም። አስተውላችሁ ከሆነ ፍየል "እረኛዬ ነው" ብሎ የራሱን ባለቤት በእርጋታ አይከተልም። ይልቅስ ቅጠል ወዳገኘበት በጥሶ ሊጎርስ ሯጭ ነው። ለሆድ አዳሪ ነው። የፍየል እረኛ መሆን አድካሚ ይመስለኛል። ፍየል ባለበት ሠላም ጸጥታና መረጋጋት አታገኙም። ፍየል ከስግብግብነቱ ከቀበጥነቱና ከሰሰኝነቱ አንጻር በጎችን የመምራት ዕድል ሊያገኝ አይገባውም። በተቀላጠፈ ነው እንዴ?

ለምንድ ነው ይህን ምሳሌ ያነሳሁት?? የሐስት መምህራን ስግብግብና ነገሮችን ከራሳቸው ግል ጥቅም አኳያ ብቻ የሚያዩ ከመሆናቸው አንጻር የበጎች መሪ መሆን የለባቸውም ብዬ ነው። በምንም መስፈርት ፍየል በግን መምራት አይኖርበትም። ሊመሩ የሚችሉት ወዴት እንደሆነ ስለሚታወቅ። እነዚህ ሐሰተኞች ሐዋሪያትና ተንባዮች የሚታይባቸውን ሌሎች ባሕርያት ሁሉ ትተን ስግብግብ ሆዳምነታቸውን ከተመለከትን በትክክል የፍየል ባሕርይ እንጂ በግነት ሲያልፍም አልነካካቸውም ማለት ትችላላችሁ። ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ከብልይና ከሐዲስ እንድታጠኑ ሰጥቻችሁ ልሰናበታችሁ።

1. "ካሕናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፣ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያሟርታሉ፤ ከዚህም ጋር እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።" (ሚክ. 3:11) ይላል። ገንዘብ መገኘቱን ብቻ እንጂ ስለሚናገሩት መልዕክት እውነተኝነት ግዴላቸውም ፍየሎቹ እረኞች። "ሠላም ነው"፣ "ድግስ ነው"፣ "ቁርጥ ነው"። ይላሉ የሚሆነው ግን ተቃራኒው ነው። ፍየሎቹ እረኞች "ደቡብ በእናንተ ምክንያት ሰላም ነች" በተባለ ማግስት ምን እንደተከሰተ ታስታውሳላችሁ። የሐሰተኞች ሠራተኞች ስግብግብነትና ሆዳምነት ከየትም የሚያመጡት ሳይሆን ከባሕርያቸው ያፈለቁት ካላመነ ልባቸው የሚያመነጩት ነው።

2. "የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።" (2ቆሮ. 2:17) ሐዋሪያው ጳውሎስ እነዚያ ስግብግቦቹ ሌላው ቀርቶ ቃሉንም ቀላቅለው ይሸቃቅጣሉ።ይላል። ቅንነት የሌለባቸው ለሆድ አዳሪዎች መሆናቸውን ጠቁሞአል። እርሱ ግን እንደ መልዕክተኛ በቅንነት በክርስቶስ ሆኖ የሚናገር መሆኑን በንጽጽር ተናግሮአል። ልዩነቱ ጉልህ ነው። ሐሰተኞች አለመርካት፣ ጥቅመኝነት መለያቸው ነው። ተልዕኳቸው ራስ ተኮር ነው። ዓላማቸው ራስ ተኮር ነው። ግባቸው ራስ ተኮር ነው። መነሻቸውም መድረሻቸውም ራስ ተኮር ነው። የዛሬው መልዕክቴ በጎች ሆይ ምንም የዋህ ብት ሆኑ በፍየል አትመሩ!!መልካም ቀን!! ቻው።

ወርቅነህ ኮይራ
@nazrawi_tube
195 viewsΒενιαμίν, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 12:27:48
ተቀባይነትን የማግኘት ጣኦት

ድንቅ አጭር ትምህርት በአቤል ተሰማ
አድምጣችሁ አጋሩ።

tiktok.com/@abela361111
---
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
219 viewsΒενιαμίν, 09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 11:53:20 "የዕለት አንጀራችንን ዛሬ ስጠን"



.
ለምን የዕለት እንጀራ ኾነ? በሌላ አባባል ለምን የዕለት ብቻ? ለዕድሜ ዘመናችንን የሚበቃውን ኹሉ አንዴ ቢዘረግፍልን ምናለበት? ወይም ለምን የ10 ዓመት ዕቅዳችንን የሚሸፍን እንጀራ አንጠይቅም? የ50 ዓመቱን ብንለምነውስ? የሰማኒያውንስ ቢኾን? እርሱ እንደ ኾነ ኹሉ የተረፈው ነው፤ ምን አለበት የዳቦ ተራራ ቢሰጠን?

የዕለት እንጀራችንን እንዲሰጠን እግዚአብሔርን መለመን ያለብን ለምንድን ነው? እኛ የሕይወታችን ባለቤት አይደለንም። የህልውናችን ምንጭ እግዚአብሔር ስለ ኾነ ራሳችንን አላስገኘንም። ሕይወት የእግዚአብሔር ስጦታ ናት፤ የግል ርስታችን አይደለችም። “የሕያዋን ኹሉ ነፍስ፥ የሰውም ኹሉ መንፈስ በእጁ ናት[ና]” (ኢዮ 12፥10)፥ ለመገኘታችን ሌላ ሰበብ አልነበረም፤ የለምም። ከእርሱና በእርሱ ተገኝተናል፤ ወደ እርሱም እንመለሳለን። በፍጥረትም ኾነ በድኅነት የተቀበልነው ሕይወት ምንጭ ሕያው አምላክ ነው።

ሕይወታችን የምታሣሣ ችግኝ ነች። እግዚአብሔር ራሱ ከሕይወት ውሃ ካላጠጣን ለዘላለሙ ደርቀናል። እርሱ ጥላ ከለላ ካልኾነልን ላለመለምለም ጠውልገናል። እርሱ ካላቆመን ላለመነሣት ወድቀናል። እርሱ ካልሰበሰበን ለዘላለሙ ተበትነናል። …

የዘላለም ሕይወት የሰጠን አምላክ ምድራዊ እንጀራም ይሰጠናል። በሰብአዊ ኀይል፥ በቍሳቍስና በምድራዊ ባለጠግነት ሕይወታችንን አናጸናውም። ዕውቀትና ጥበባችን አልፈጠረንምና ገንዘባችን ሕይወት አልሰጠንምና የራሳችን አይደለንም። የሕይወታችን ባለቤት የፈጠረን አምላክ ነው። የሕይወታችን ባለቤትና ጌታ እግዚአብሔር ራሱ ነው። ያስብልናል። …

እግዚአብሔር የሕይወታችን ባለቤት ብቻም ሳይኾን መጋቢና ጠባቂዋ ነው። አንጡራ ሀብታችን፥ ገንዘባችንና ቍሳቍሳችን አሳዳሪዎቻችን አይደሉም። በዘላለም ሕይወት ዋስትናም አያኖሩንም። ዋስትናችን መግቦቱ ነው።

እውነተኛ አማኝነት በእግዚአብሔር ላይ የተደገፈ ሕይወት ነው። ከገበታችን ላይ በቀረበልን የዕለት ምግባችን ጀርባ የተወሳሰበ ምጋቤ ሀብታዊ የምግብ ሰንሰለት አለ። ከመጨነቅ ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ቋሚ መታመን ዋስትና ያስገኝልናል። ዲትሪክ ቦኖፈር “ክርስትያን መጨነቅ እንደማይችል እና እንደማይደፍር ብቻ ሳይኾን መጨነቅ እንደማያስፈልገውም ያውቃል። የዕለት እንጀራውን የሚያገኘው በመጨነቁ ወይም በመሥራቱ አይደለም፤ ምክንያቱም እንጀራ የአባት ስጦታ ነውና።” …
.
ሙሉውን ለማግኘት፦



ሰሎሞን አበበ ገብረ መድኅን (መጋቢ)
197 viewsΒενιαμίν, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 12:21:31 መንፈስ ቅዱስ እወድሃለሁ


391 viewsΒενιαμίν, 09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 20:37:58
---ስለ ኮንሰርቶቻችን ጥቂት---

ሰሞኑን ትንሽ ኮንሰርት በዛ ያለ ይመስላል እና አሁን ቢነገር ትርጉም ይኖረዋል።

ቃሉን ለምደነዋል እንጂ አብዛኛው የመዝሙር ኮንሰርት ተብለን የምንጋበዘው ትክክለኛው መጠሪያ ሊሆን የሚገባው "የመዝሙር ፌስቲቫል" ይመስለኛል።

ኮንሰርት የሚለው ቃል ተግባሩን ወክሎ የተገኘው "Concerto" /ኮንቼርቶ / ከሚለው የላቲን ቃል ሲሆን ከፍተኛ ጥበብ ያለበት የሙዚቃ ቅንብር ነው።

ኮንቼርቶ ሰዎች ሁሉ እየተሳተፉ፣ ለመድረኩ ከያኒያን ሞራል እየሰጡ አብረው ሙሉ ዝማሬውን የሚዘምሩበት፣ የሚደሳሰቱበት የዜማ ስራ አይደለም።

አምልኮም ኮንሰርት ተብሎ ሊጠራ የሚችል አይመስለኝም።

ሰዎች ታድመው የላቀ የዜማ እና የመሣሪያ ጥበብ ሠምተው የሚደመሙበት ሥራ ነው ኮንቼርቶ።

በእኛ ዘንድ ግን ጥበብ ለማዳመጥ ሆነ ለማጣጣም ልቦናውም ያለን አይመስልም።

የአዘማመር ጥበብ በፍጹም ጸጥታ /Absolute silence/
ውስጥ ማሳየት ከቻልን አዎ ኮንሰርት ነው።

Music presupposes absolute silence!!

የዜማ ስራ ነጩ ሰሌዳ "ጸ ጥ ታ" ይባላል። ይህም እንደ ሠዓሊ ነው! የተሞነጫጨረ ሠሌዳ ላይ ሠዓሊው ሊስል እንደማይችል ሁሉ በብዙ ጫጫታ ውስጥ ጥሶ የሚወጣ ድምጽ በመጠቀምም የዜማ ጥበብ አይሰራም!!

እስቲ ኳስ በመሬት!!

Reta Paulos
@nazrawi_tube
474 viewsΒενιαμίν, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 15:31:01 ሥነ መለኮት እና የእኔ ምልከታ

የሰው ልጅን የአመለካከት፤ የዕይታ ዉስንነት አለበት፡፡ ስለዚህ ዬትኛውም አመለካከትም ኾነ ሥነ መለኮታዊ እሳቤ ዉሱን ነው፡፡ የክርስትና መንገድ እውነቱ የማይለወጥ፤ መዳኛው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ የእኔም ኾነ የማንም ሰው ሥነ መለኮታዊ አቋም አመለካከት ብቻ ነው፡፡ ይህ አመለካከት በሙግት መልክ ቀርቦ፤ ካሉት አመለካክቶች ጋር ተንጻጽሮ ይበልጥ አሳማኝ ነው ወይም አይደልም ተብሎ ይዳኛል፡፡ ፍጹም የኾነ ሥነ መለኮት የለም፤ የስው እጅ ሥራዎች ናቸውና፡፡ በዚህ የእይታ መንጽር ውስጥ እኔም በአንድ ወቅት ልክ ናቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ሀሳቦች ሙግት አዋቅሬላቸው ሽንጤን ገትሬ ተሟግቼላቸው በሌላ ጊዜ የተሻለ መረጃ እና ርቱእ የሙግት ሀሳብ ሳገኝ ቀይሬ ይኾናል፡፡

በአጠቃላይ የሥነ መለኮታዊ ሀሳቦችን ፍጹም፣ ያለቀላቸው አድርጎ መምልክት ትክክል አይደለም ብዬ አስባለሁ፡፡ ሥነ መለኮታዊ ሀሳቦች በየጊዜው የሚክለሱ፣ በይዘትም ይኹን በአቀራረብ የሚሻሻሉ ናቸው፡፡ የትኛውም ሥነ-መለኮታዊ አቋም የማይቀየር የእግዚአብሔር ቃል አይደልም፡፡ ስለዚህ በየጊዜው ሊፈተሽ ይግባዋል፡፡

Dr. Tekalign duguma
401 viewsΒενιαμίν, 12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 22:49:42 እነሆ የተሰቀለው ክርስቶስ! እነሆ ለሁሉ በመስቀል የተገለጠው እግዚአብሔር !! 'እነሆ ሰውየው!' [ዮሐ.19፥ 6]

እግዚአብሔር ለማዳን የተገለጠበትን መንገድ ማጤን ግድ ይለናል ይላል ማርቲን ሉተር ። የቅዱሳት መጻሕፍትን ታሪክ ፍሰት ማመሳከሪያ በማድረግ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ለማዳን [ሰውን ከጠፋበት መንገድ ለመመለስና ለመታረቅ] ሲገለጥ ልክና ወሰን የለሽ ክብሩን በማሳየት አይደለም፤ ይልቅኑ በተቃራኒው ነበር ይለናል።

ሐዋርያቱም በአደባባይ የሰበኩት 'ንጉሡንና ወሰን የለሽ ክብር የተጎናጸፈውን' አይደለም። የተሰቀለውን እንጂ። አዚማሞቹንም የገላቲያ ማሕበራት 'ክርስቶስ በክብሩ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረም ወይ?' አልተባሉም። 'እንደ ተሰቀለ' ተባሉ እንጂ። የተሰቀለውን ማሳየት ይቻላል፤ በመስቀል የደከመውን መስበክ የቤተክርስቲያን ኃላፊነት ነው። ዓለም ሞኝነት ያለችውን የማዳንና የመታደግ መንገድ ቤተክርስቲያን ጥበቤ ነው ትላለች። በክብር #እስኪገለጥ ሞቱን ትመሰክራለች።

'እነሆ ንጉሥሽ' የተባለውን ካላየን ሲሉ 'ከምድር ከፍ ከፍ ስል ሁሉን ወደኔ እስባለሁ' ብሎ ነበር ክርስቶስ። እነሆ መስቀሉ ለሁሉ የሚታይበት መንገዱ ነበረና።

ነገር ግን ባለጠጎችና 'ጸጋ ሞል' ነን የሚሉቱ መስቀል ጠል ናቸው። መስቀል ጠሎች ደግሞ 'እነሆ አምላካችን' ቢሉም የሚያሳዩት ወርቃቸውንና ብራቸውን ነው። ይዋሻሉ፤ ዋሾ ናቸው። መስቀል የተሰወረባት ማሕበር 'እነሆኝ' ብትል ታዳጊውንና በመስቀል የሞተውን አዳኝ አታሳይም፤ ሌላ ክርስቶስን ካልሆነ በስተቀር።

ማኀበራትም ሁለት ናቸው:- አንደኛይቱ በዚህ ዓለም የቆሰለውን አዳኝ ሳያፍሩ- የሚመሰክሩና ፈለጉን የሚከተሉ ያሉባት ናት። ኹለተኛይቱ ግን እንደ ዓለም ሁሉ በመስቀል ሞቱ የሚያፍሩ ያሉባት ናት።

እና የ'እነኾኝ' ጥሪዎች 'እነኾኝ መስቀል' ካላሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ጥበብ ይሰውራሉ። አጀንዳቸውም ሌላ ነው። ይኸው ነው።

#የተሰቀለው_ክርስቶሰ #የእግዚብሔር_ክርስቶስ #እግዚአብሔር_የሾመው_ንጉሥ

Tegegn mulgeta
@nazrawi_tube
230 viewsΒενιαμίν, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 06:28:54
ኡጋንዳዊው ፓስተር ከስፖርት ውርርድ 26,800 ዶላር ካሸነፈ በኋላ የሚያገለግልባትን ቤተ ክርስቲያን ዘጋ!! እንዲህ የሚል ምስክርነትም ሰጠ፦

"ይህን ቤተ ክርስቲያን የከፈትኩት ተቀብቼ አይደለም። በስግብግብነት ምክንያት መሆኑን መቀበል አለብኝ። ብዙ ፓስተሮች ከህዝቡ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያገኙና ሰውን የበለጠ ለመሳብ የውሸት ትንቢት ሲናገሩ አይቻለሁ።

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተገነዘብኩ እንቅልፍ የሌላቸው ምሽቶች ማሳለፍ ጀመርኩ፣ ሁልጊዜም ያልተለመዱ ህልሞች አይ ነበር። ይህንን ቤተ ክርስትያን ከመክፈቴ በፊት ሁሉም ነገር በእኔ በኩል የተለመደ ነበር። ስለዚህ ይህንን ድርጊቴን ለመተውና እና ገንዘብ ለማግኘት ሌሎች መንገዶችን ለመፈለግ ወሰንኩ። አንድ ቀን የስፖርት ውርርድ ኖቲፊኬሽን በስልኬ ገባ። ከዛ በኋላ የስፖርት ውርርድ ስጫወት አጭበርባሪዎች መስለውኝ ነበር። በመጨረሻም አሸናፊ ሆኛለሁ!" ማለቱን የኡጋንዳው ቴሶ ቫይብስ ድረ ገፅ ነው የዘገበው።

የእኛዎቹ አንዳንድ ፓስተሮች ከዑጋንዳዊው አቻቸው ምን ይማራሉ?

Via፦Tewodros Teklargay
@nazrawi_tube
423 viewsΒενιαμίν, 03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 12:59:14 "መንፈስን አታዳፍኑ"
***
ከጠፊው ዓለም የተጠሩት የእግዚአብሔር ኅሩያን (ምርጦች) የእምነት ተጓዦች ናቸው። አዎ አማኞች ወደ ቤታችን በመኼድ ላይ ያለን የእምነት ተጓዦች ነን። ወደ ዘላለም ቤታችን በመኼድ ላይ ነን። ቲም ፌሎስ አንድ አገላለጽ አለው፤ “ዘላን ቤት የለውም፤ ሽፍታ ከቤቱ የሸሸ ነው፤ እንግዳ ከቤቱ የራቀ ሲኾን፥ የእምነት ተጓዥ ግን ወደ ቤቱ የሚኼድ ነው።” አዎ፥ ተጓዦች ነን።


.
በእምነት በምንጓዝበት ጊዜ ታዲያ ብቻችንን አይደለንም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው። የዚህ ዐብሮነቱ ማረጋገጫው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ማደሩ ነው። አዎ፥ ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ “ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንኾን፥ በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው” (ቲቶ 3፥6-7)። ...
.
ከማንኛውም ክፉ ትምህርትና ተመክሮ ለመራቅ መፍትሔው እውነተኛውን አሠራር ማዳፈን አለመኾኑን መረዳት የተገባ ነው (1ቆሮ. 14፥39-40)። በመንፈስ ነጻነትና በድንጋጌ ሥርዐት መካከል ተገቢ ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋል። ትእዛዙም “መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ኹሉን ፈትኑ፤ መልካሙንም ያዙ፤ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ” (1ተሰ. 5፥20) የሚል ነውና። ..
.
... ሙሉውን መልእክት ለማግኘት፦

817 viewsΒενιαμίν, 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 15:19:23
የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ....

አንድ ፍልስፍና አፍቃሬ ወዳጄ በብዙ የፍልስፍናና የሥነ ልቡና መጻሕፍት ውስጥ ራሱንና አዳኙን ፈለገ፡፡ በየመጣጥፉ ውስጥ የሕይወትን ምንነትና ትርጉም ያገኝ ዘንድ ተጋ፡፡ ግራ የተጋባው ሕይወቱ ይቀና ዘንድ ያልሞከረው ነገር አልነበረም፡፡ መጨረሻ ላይ ተስፋ ሲቆርጥ ሰካራም ሆነ፡፡ በዚያ ሁኔታ ላይ ሆኖም ግን ፍለጋውን አልተወውም ነበር፡፡ ጫቱን እየቃመ የእስልምና መጻሕፍትን፣ የዮጋ መጣጥፎችን፣ የሒንዱ ድርሳናትንና ፓለቲካውን ወዘተ አስነካው፡፡ ሆኖም ግን ነፍሱ የፈለገችውን ሊያገኝ አልቻለም፡፡

ተስፋ ከመቁረጡ የተነሣም ይባስ ብሎ ጠንከር ያሉ አደንዛዥ ዕፆችን እየወሰደ ካለበት ውስብስብ ሥነ ልቡናዊ ጫና ለመደበቅ ሞከረ፡፡ ወዴትም ማምለጥ አልቻለምና ነፍሱ ሞትን ናፈቀች፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት ሳውቀው ሽቅርቅር የነበረ ወንድሜ ለየለትና ጀዘበ (ይቅርታ ለዚህ ቃል፥ እንዲገልጸው ብዬ ነው)፤ ራሱን ጣለ፡፡
መጨረሻ ላይ ድንገት አንዲት ያረጀች አዲስ ኪዳን ብቻ ያላት አነስተኛ መጽሐፍ ቅዱስ (pocket Bible) እጁ ላይ ገባች፡፡ እንደ ቀልድ እየደጋገመ ከማቴዎስ ወንጌል ጀምሮ እስከ ራእይ አነበባት፡፡

አንዲት ልዩ ቀን ግን ዮሐንስ ወንጌልን እያነበበ ሳለ፣ በቃሉ ውስጥ ጌታ ኢየሱስን በክብሩ አየው–አዳኙ ተገለጠለት፡፡ ከዚያም በታላቅ እፎይታ መጽሐፉን አስቀምጦ “ጌታዬ አምላኬ” (ዮሐ.20፥28) ብሎ ሰገደለት፡፡ አሁን በሚገርም እረፍትና እርካታ ውስጥ ሆኖ ሕይወትን ያጣጥማል፤ ያንን በሚደንቅ ብርሃን የተገለጠለትን ኢየሱስ ለሰማው ሁሉ እየመሰከረ ሰዎችን ወደ ጽደቅና ቅድስና የሚመልስ የብርሃን ልጅ ሆኗል፡፡

ወገኖቼ ጌታ ኢየሱስ ዓይናችንን
በተገቢው መጠን ይግለጠው!

Dr. Bekele birhanu
@nazrawi_tube
522 viewsΒενιαμίν, 12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ