Get Mystery Box with random crypto!

የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ.... አንድ ፍልስፍና አፍቃሬ ወዳጄ በብዙ የፍልስፍናና የሥነ ልቡና መጻሕ | ናዝራዊ Tube

የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ....

አንድ ፍልስፍና አፍቃሬ ወዳጄ በብዙ የፍልስፍናና የሥነ ልቡና መጻሕፍት ውስጥ ራሱንና አዳኙን ፈለገ፡፡ በየመጣጥፉ ውስጥ የሕይወትን ምንነትና ትርጉም ያገኝ ዘንድ ተጋ፡፡ ግራ የተጋባው ሕይወቱ ይቀና ዘንድ ያልሞከረው ነገር አልነበረም፡፡ መጨረሻ ላይ ተስፋ ሲቆርጥ ሰካራም ሆነ፡፡ በዚያ ሁኔታ ላይ ሆኖም ግን ፍለጋውን አልተወውም ነበር፡፡ ጫቱን እየቃመ የእስልምና መጻሕፍትን፣ የዮጋ መጣጥፎችን፣ የሒንዱ ድርሳናትንና ፓለቲካውን ወዘተ አስነካው፡፡ ሆኖም ግን ነፍሱ የፈለገችውን ሊያገኝ አልቻለም፡፡

ተስፋ ከመቁረጡ የተነሣም ይባስ ብሎ ጠንከር ያሉ አደንዛዥ ዕፆችን እየወሰደ ካለበት ውስብስብ ሥነ ልቡናዊ ጫና ለመደበቅ ሞከረ፡፡ ወዴትም ማምለጥ አልቻለምና ነፍሱ ሞትን ናፈቀች፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት ሳውቀው ሽቅርቅር የነበረ ወንድሜ ለየለትና ጀዘበ (ይቅርታ ለዚህ ቃል፥ እንዲገልጸው ብዬ ነው)፤ ራሱን ጣለ፡፡
መጨረሻ ላይ ድንገት አንዲት ያረጀች አዲስ ኪዳን ብቻ ያላት አነስተኛ መጽሐፍ ቅዱስ (pocket Bible) እጁ ላይ ገባች፡፡ እንደ ቀልድ እየደጋገመ ከማቴዎስ ወንጌል ጀምሮ እስከ ራእይ አነበባት፡፡

አንዲት ልዩ ቀን ግን ዮሐንስ ወንጌልን እያነበበ ሳለ፣ በቃሉ ውስጥ ጌታ ኢየሱስን በክብሩ አየው–አዳኙ ተገለጠለት፡፡ ከዚያም በታላቅ እፎይታ መጽሐፉን አስቀምጦ “ጌታዬ አምላኬ” (ዮሐ.20፥28) ብሎ ሰገደለት፡፡ አሁን በሚገርም እረፍትና እርካታ ውስጥ ሆኖ ሕይወትን ያጣጥማል፤ ያንን በሚደንቅ ብርሃን የተገለጠለትን ኢየሱስ ለሰማው ሁሉ እየመሰከረ ሰዎችን ወደ ጽደቅና ቅድስና የሚመልስ የብርሃን ልጅ ሆኗል፡፡

ወገኖቼ ጌታ ኢየሱስ ዓይናችንን
በተገቢው መጠን ይግለጠው!

Dr. Bekele birhanu
@nazrawi_tube