2023-01-31 10:28:24
በታዳጊ ወጣቶች ሕይወት በቲክቶክ ሊሆኑ የሚችሉ አሉታዊ ውጤቶች፦ (Potential negative effects of TikTok)
ክፍል ሁለት :-
የዛሬውን ጽሁፌን ከዚህ ቀጥሎ ባለው መግቢያ ብጅምር እወዳለሁ ። ብዙ የቴሌቪዥንና የድረ ገጽ ዜናዎች ትኩረት ሰጥተውታል ፤ ይሁን እንጂ እንደ ሲ ኤን ኤን ( CNN ) ዘገባ ቲክ ቶክ በታዳጊ ወጣቶች ሕይወት በአግባብ ማለመያዙ ራስን ከማጥፋት እና ከአመጋገብ መዛባት ( eating disorders) እንዲሁም ሌላ ተዛማጅ ጎጂ የሆነ ባህሪያትን ከማስከተል ጅምሮ ብዙ ጉዳትን እና ጣጣ እያስከተለ እንዳለ ዘግቧል። ይህን ስንመለከት መተግባሪያው በታዳጊ ወጣቶች ሕይወት ተጽዕኖ ማሳደሩ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ትኩረት የሚጡበትእና ሊከታተሉት የሚገባ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቷል ። ይህም ብቻ አይደለም የቤተ ክርስቲያን የሰንብት ትምህርት አስተማሪዎች ልጆችን ለማዳን ትኩረታቸውን በዚህም አቅጣጫ ለማድረግ ዝግጅት ይጠበቅባቸዋል።
በአሁኑ ጊዜ ቲክ ቶክ በታዳጊ ወጣቶች ሕይወት ምን አሉታዊ ጉዳት እና ተፅዕኖ እያስከተለ እንዳለ ብዙ እየተጻፈ ፤ በዜና ማሰራጫዎችም እየተነገረ ይገኛል። እኔ ግን በዚህ ጽሑፌ ትኩረት የሰጠሁባቸውንና ዋና ዋና የምላቸውን እንደሚከተለው አቅርቤላችኋለሁ።
1. አሉታዊ ውጤቶች ምንድናቸው ?፦
1.1 ሱስ (Addiction)፡-
ሰዎች በአልኮሆል መጠጦች፣ በሲጋራዎች እና በእጽ ሱሰኞች ሊሆኑና ከሱስም ለመውጣት ሊቸገሩ እንደሚችሉ ፣ እንዲሁ ታዳጊ ወጣቶችም በዚህ መተግበሪያ “ማቆሚያ ወደ ሌለው የሱሰኝነት ዥረት” ሊገቡ እንደሚችሉ በአሜሪካ በእንግሊዝና በካናዳ የተደረጉ ጥናቶች አሳይተዋል ። ብዙዎቹ የተለያየ ይዘት ኖሯቸው በስልካቸው ላይ በሚመጡ የሚያማልሉ ቨድዮዎች ሱሰኞች ሆነዋል። ተግበሪያው በባህሪው አንድ ጊዜ ስማርት ስልካቸውን ከፍተው ከጀመሩት እንዳይላቀቁትና ጊዜያቸውን በዚያ ላይ ለረዥም ጊዜ እንዲያሳልፉ የሚያደርግ ባህሪ ያለው በመሆኑ በቲክ ቶክ ሱስ እንዲጠመዱ ያደርጋል። ተጓዳኝ ጠንቁ በትምህርታቸውም ሆነ ከቤተሰብ ጋር ባላቸው ግንኙነት ውጤታማ እንዳይሆኑ ከማድረጉም በላይ ጤናማ መስተጋብር የሌላቸውና በራሳቸው የሳይቨር ዓለም ውስጥ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።
1.2 ጉልበተኝነት (Bullying)፡
ማንኛውም ሰው ዓለማቀፋዊ ( Global Ethics) እና መጽሓፍ ቅዱሳዊ ሥነ- ምግባሩን ያልጠበቀን ንግግርንና ድርጊትን በዚህ መተግበሪያ ላይ ሲያስቀምጥ፣ ራሱን ለማንአለብኝነትና ለጉልበተኝነት ክፍት እንደሚያደርግ ፣ ቲክቶክንም የሚጠቀሙ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ታዳጊ ወጣቶች ለዚህ ዓይነቱ ችግር ተጋላጭ አድርጓቸዋል። በተለይም በአሥራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ለዚህ ችግር ያላቸው ዓለማቀፋዊ ተጋላጭነት ከፍ እያለ መምጣቱን ቢቢሲ በድረ ገጹ አስነብቧል። ቪዲዮዎቻቸው ሊሳለቁና በሌሎች ላይ በጉልበተኝነት ሲያፊዙ ( bullying) ፤ ከዚያም ተመሳሳይ እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ወጣቶች ሲያጋሩ ዓለማቀፋዊ ተዛማጅነቱና የዚህም ችግር ተጠቂነታቸው ከፍ ያለ ነው።
ጉልበተኝነት ( bullying) በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ለሚገኝ ልጆች ደህንነት ላይ ያለው ተጽእኖ ከፍተኛ ነው። በጉልበተኝነት ምክንያት የሚፈጠረው መገለል የአእምሮ ጤና ተፅእኖ በመፍጠር ራስን ወደ ማጥፋት እንኳን እንደሚያደርስ ታውቋል። በኒውዮርክ ያለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር እንደገለጸው አንዳንድ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው በቪዲዮ በሚያደርጉት መበሻሸቅ፣ ሌሎች ደግሞ በእኩዮቻቸው ላይ ለማሾፍ ሲሉ በሚሰሩት ቪዲዮ ከማህበራዊ መገለል ራስን እስከ ማጥፋት የደረሱ ተበራክተዋል።
1.3 ከሌሎች ጋር ጤናማ ያልሆነ ማነፃፀር (Comparison ) -
ማንም ሰው የሚሰማውንና የሚወደውን ተከታይ ማግኜት የማህበራዊ ሚዲያ እና የቲኪቶክ ዋና አካል ነው። አንድ ወጣት በየትኛውን መልኩ ትኩረት የሚስብና የሌሎችን ቀልብ ሊገዛበት የሚችልበትን ቪድዮ ከለቀቀ እና የበለጠ ምላሽ የሚያገኝበት ከሆነ፣ በተመሳሳይ ሌሎችም ተከትለውት ለማድረግ አሉታዊ ስሜትና ተነሻሽነት ውስጥ ይገባሉ ። አንዳንዶች አጸናፊና አደገኛ በመስራት ሕይወታቸው ፈተና ውስጥ የገባበት ዋና ምክንያት ይህ ነው። ይህንን በአንድ መቶ ተማሪዎች ላይ ጥናት ተሰርቶ በ89 ላይ ማየት ተችሏል። ጉዳዩም የአቻ እድሜ የጽዕኖ የሚፈጥረው እኩይ ጣጣ እንደሆነ የማህበራዊና የባህርይ ሳይንስ ዲፓርትመን ዳሬክተሩ ፕሮፌሰር ብሬይን ኦስቲን ተናግረዋል። ጉዳዩም በእድሜያቸው ከሚመጣባቸው የሆርሞን ለውጥ በተጨማሪ ወደ ጭንቀት እና ድብርት ሊመራ ይችላል። ውጤቱም በአደገኛነቱ እየተገለጠ ነው ።
ቅድመ ታዳጊ ወጣቶች እና ወጣቶች እድሜያቸው ከሚፈጥረው ባሻገር እንደማንኛውም ሰው ዓለማቀፋዊ ተግዳሮቶች አሉባቸው። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዓለማወፋዊው እድል ይዞ እንደመጣ እንዲሁ አለማቀፋዊ ስጋትንም አብሮ ይዞ መጥቷል። በእድሉ ተጠቃሚ በመሆን ስጋቱ ከሚያመጣው ችግር ለመላቀቅ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ መንፈሳዊ የንቃተ ሕሊና የበላይነት አስፈላጊ ነው። በአጠቃላይ ወጣቶችን ማዳን የሚቻለው በመጽሓፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረተ መንፈሳዊነት ነው።
የእግዚአብሔር ቃል በማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከወንጌል በሚገኝ እውነት ከየትኛውም የክፋትና የኅጢአት ኅይል ነፃ በማውጣት እንዲመለሱ እና ዓይናቸው ለእግዚአብሔር መንግሥት እንዲከፈት፣ በነፍሳቸው ላይ ከፍተኛና ስር ነቀል የነፍስ ቀዶ ጥገና ሥራ ይሠራል ( ዕብ 4፣ 12)። ትውልድን በዚህ ክፉ ዘመን በእግዚአብሔር ቃል እንዲታነጹ ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭና የማዳኛ መንገድ የለም። ያኔ የትኛውንም ነገር በሚዛናዊነት እንዴት መጠቀምና መያዝ ያውቃሉ።
አበቃሁ
ቸር ሰንብቱ !!
ነቢዩ ነኝ።
https://t.me/+C1QfeS09E1pmZDU5
ወጥና ተከታታይ ክርስቲያናዊ ጽሑፎችን በማንበብና ትምህርቶችን በመማር ፣ በክርስቲያናዊ ሕይወትዎ የአመለካከት፣ የተግባር እና የሕይወት ለውጥ በማምጣት በሚኖሩበት ቤተሰብ ፣ ማህበረሰብና ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወትዎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን የዚህ ቴሌግራም ቡድን አባል እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።
@nazrawi_tube
978 viewsΒενιαμίν, 07:28