Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-09 18:00:26 ተግተው የሚሹኝ ያገኙኛል!

ሉተር ለረጅም ጊዜ በፍለጋ ተግቶ ነው ለብዙዎች የመዳን ምክንያት የሆነው ብርሃን ልቡ ላይ የፈነጠቀው፡፡ ጰጳሱ ጆን ፓል 11 (Pope John Paul 11) ሉተርን “a profoundly religious man” ብለውታል፡፡ ይሁን እንጂ በውስጡ ብዙ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ በመሆኑም ሳያሰልስ እውነትን ፍለጋ ላይ ተጠምዶ ነበር፡፡

ሉተር በቀን ለሦስት ሰዓት ያህል የመጸለይ ልማድ የነበረው ሲሆን፣ በየአንድ ሰዓቱ ንስሐ ይገባ ነበር፡፡ አዘውትሮ በመጾሙም ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ውስጡ ምንም ዕረፍት አልነበረውም፡፡ እንዳውም በኃጢአተኝነት ስሜት ይከሰሰስ ስለ ነበር ስቃይ ውስጥ ነበር የቆየው፡፡ በዚያ ከባድ ሁኔታ ውስጥ እያለ፣ “ጻድቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል፡፡” (ሮሜ.1፥17) የሚለውን ምንባብ ሲያነብብ በመገረም ልቡ ይሸበር ነበር።

የእግዚአብሔር መንፈስ በዚሁ ቃል ደጋግሞ ተናግሮታል፤ ጥርት ብሎ አልገባውም እንጂ! ከረጅም ጊዜ በኋላ አንድ ልዩ የሆነች ቀን ላይ ግን በሚገርም ሁኔታ የቃሉ ፍቺ ልቡ ላይ ፏ ብሎ በራ፡፡ እናም የወንጌል ዋና መልእክት ወለል ብሎ ገባው፡፡ በዚያም የእግዚአብሔርን ጸጋ በሚገባ ስላስተዋለ፣ ሰው በሥራው ሳይሆን፣ በእምነቱ እንደሚጸድቅ ተረዳ፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

ለመሆኑ ይህ የእርሱ ፍለጋ (search) ምን ያስተምረናል? ጌታ በቅንነትና በትሕትና የሚሹትን እንደማያሳፍር ነዋ! ስለሆነም ነው የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ የሚለን፡-

➢ “እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።” (ምሳ.8፥17)፤

➢ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በልብህም ሁሉ በነፍስህም ሁሉ የፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።” (ዘዳ.4፥29)፤

➢ “አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ።” (1ዜና.28፥9)፡፡

መልካም ጊዜ ተባረኩ!
Dr. Beke
@nazrawi_tube
2.6K viewsΒενιαμίν, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 22:01:58 " #ፖርኖግራፊ ማየት የጀመርኩት በ16 አመቴ ነው እሁን ዕድሜዬ 34 ነው። ለማቆም ያላነበብኩት ያልሞከርኩት ነገር የለም። ሁሌ አምላኬን መበደል መሮኛል.....አሁንስ ሰለቸኝ!"

ሙሉ ታሪኩን ከታች ያለውን በመጫን ያገኙታል!
505 viewsAbrish, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 21:33:38 እግዚአብሔር ያስታውሳል!

በዘገየ የጸሎት መልስና በእግዚአብሔር ዝምታ አንዳንድ ጊዜ ልባችን በተስፋ መቈረጥ ይሞላል። በሕይወታችን “ዝምታዎችም” መካከል እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ በሥራ ላይ ነው። ልጅን ያለመወለድ ከርግማን፣ ከኀጢአት ወይም የእግዚአብሔር ሞግስ ከማጣት ጋር በሚያቆራኝ ማኅበረ ሰብ ውስጥ፣ ዘካርያስና ባለቤቱ ኤልሳቤጥ በታማኝነት ያገለግሉ ነበር። ይህ በነበሩበት ማኅበረ ሰብ ትውፊትና መንፈሳዊ ዐውድ ከባድ “መሰቀል ነበር”። “ለምን እግዚአብሔር ዝም አለ?”፣ እፍረታችንንስ ለምን “አይመለከትም?” የሚሉት ጥያቄዎች ዘወትር በነዝናዥነት ይከተሏቸው ነበር። አስነካሽ፣ ቀና የማያሰኙና ልብ አዛይ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች ነበሩ።

ኾኖም፣ እየታገሉም በመሰጠት ጌታን ያገለግሉ ነበር። በኋላ እንደምናስተውለው ያገለግሉ የነበረበት ቤተ መቀደስና መሪዎቹ በብዙ መፈሳዊ ቀውስ ውስጥ ነበሩ። ለማገልገል ቀርቶ ለማምለክም ዐቅም የሚያሳጣ መንፈሳዊ ብሉሽነት እንደ ነበረ ጌታ ቤተ መቀዱስን ሲያጸዳ ከተናገረው መገመት ይቻላል፦

“ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፣ ሻጮችን ከዚያ አስወጣ፤ ደግሞም “ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን ‘የወንበዴዎች ዋሻ’ አደረጋችሁት።” (ሉቃስ 19፥45᎓6)።

ይሁን እንጂ በዚህም ልብን በሚጥል ሁኔታ ውስጥም ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ስሜታቸውን በመከተል ሳይሆን፣ እግዚብሔርን ተመልካች በማደረግና ልባቸውንም በእርሱ ሉዓላዊነት ላይ በማሳረፍ እያመለኩ ያገለግሉ ነበር። ዋጋቸው እርሱ ብቻ እንደሆነ ተገንዝበዋልና! እንደሚመስለኝ በዚህ ወቅት ስለ ልጅ መጸለይ አቁመዋል። የሚመለስ አይመስልም ነበርና። ስለዚህ ጸሎታቸው በመሲሑ መምጣት ስለሚሆነው የእግዚብሔርን ጕብኝት ይመስለኛል። በአጭሩ “መንግሥትህ ትምጣ” ሳይሆን አይቀርም። ከስምዖን ጸሎት እንደምንረዳው ይህ የትሩፋኑ ሕዝብ የመለኮታዊ ጕበኝት ናፍቆትና ጕጕት ነበር።

“በዚያን ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር።” (ሉቃስ 2፥25)

እኛ በምንፈለገው መንገድ ወይም ጊዜ ባልተመለሰ ጸሎትና የሕይወት እንቆቅልሽ ውስጥ እግዚአብሔር ተመልካችና አድማጭ በማድረግ እንድናመልከና እንደናገለግል የሚያስችል የጌታ ጸጋ አለ። ለዘካርያስና ለኤልሳቤጥ ዘመን መጣ - የእግዚአብሔር ጊዜ። ራሱ በወደደው ጊዜ በድነት ታሪክ ውስጥ በሕይወታቸው ውስጥ የነበረው ዝምታ ተሰበረ። በእግዚአብሔር የድነት ዓላማ ውስጥ ዮሐንስ መምጣት ነበረበት። ይህ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ካሰቡት፣ ከጠበቁትና ከተመኙት በላይ ትልቅ ዕቅድ ነበር። የእግዚአብሔር መግሥት በደጅ ነበር!

“የጌታም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሀትም ተዋጠ። መልአኩ ግን እንዲህ አለው፤ “ዘካርያስ ሆይ፤ አትፍራ፤ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለህ፤ ብዙዎችም እርሱ በመወለዱ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። ከእስራኤልም ሰዎች ብዙዎቹን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳቸዋል፤ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆቻቸው፣ የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ፣ ለጌታ የተገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኀይል በጌታ ፊት ይሄዳል።” (ሉቃስ 1፥11-16)

ሳይመለስ በዘገየ ጸሎት ልባችሁ የዛለና ለጊዜው መልስ ከሌለው ውስብስብ ችግር ጋር የምታገለግሉ ትኖሩ ይሆን? ያልታየን ስንመስል፣ በርግጥ እርሱ ያየናል! ያልተሰማስን ሲመስለን በርግጥ እርሱ አስቀድሞ ሰምቷናል። ሕይወት በዝምታና በጸጥታ ስትዋጥና የእግዚአብሔር አብሮነት ሳይሰማንም ሲቀር እግዚአብሔር በአጠገባችን አለ። በቅንነትና በታማኘት እናምልከው፤ እናገልግለውም! እንደ ስሙ፣ ዘካሪያስ - እግዚአብሔር ያስባል፤ እግዚአብሔር ያስታውሳል፤ እግዚአብሔር ይመለከታል።

አሜን!
Dr. Girma Bekele
@nazrawi_tube
595 viewsΒενιαμίν, edited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 13:16:17 " አይዞአችሁ ክርስቲያኖች! ነገሮች ለአጋጣሚ የተተዉ አይደሉም፡ እውር ዕጣ ፈንታ ዓለምን አይገዛም። እግዚአብሔር ዓላማ አለው፥ ዓላማውም ይፈጸማል። እግዚአብሔር ዕቅድ አለው፥ ዕቅዶቹም ​​ጥበበኞች ናቸው፥ ፈጽሞ ሊፈርሱ አይችሉም።"

-- ቻርለስ ስፐርጅን --

@nazrawi_tube
1.7K viewsΒενιαμίν, edited  10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 14:51:01 ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን "ባለራዕይና መስራች ነኝ" ብሎ በራሱ ራዕይ የተጠመደ ሳይሆን "ከሰማይ ለተቀበልሁት ራዕይ እምቢ አላልሁም" የሚል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን የራሱን ክብርና ምቾት ሳይሆን የላከውን ክብርና መታየት የሚፈልግ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ዘይት የሚቸበችብ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ዘይት የረሰረሰ:

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን "እኔና አንተ ከዚህ በፊት ተገናኝተን እናውቃለን?” ብሎ የሚቀልድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ጥበብና ሃይል የሆነውን ክርስቶስን የሚገልጥ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ከእግዚአብሔርና የእግዚአብሔርን ምስክርነት እንጂ የሰው ምስክርነት ያላሰከረው:

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ለመወደድ ብሎ የሚያገለግል ሳይሆን እግዚአብሔርን ከመውደዱ የተነሳ የሚያገለግል:

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ከብር ኋላ የሚሮጥ ሳይሆን ራሱን ከሕዝቡ ጋር ጨምሮ ከክርስቶስ ኋላ የሚሮጥ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ጫማውን የሚያስምና መጽሐፍ ቅዱሱን በአሽከር የሚያሸክም ሳይሆን ራሱን ክዶና መስቀሉን ተሸክሞ ከፊት የሚወጣ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን "ብር ትራሱ" የሆነ ሳይሆን ካለው የሚያካፍልና አገልግሎቱም እንደ ኢየሱስ ድሆች ላይ ያተኮረ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በቲፎዞና በጋሻ ጃግሬ የተከበበ ሳይሆን ባኅጢአተኞችና በቀራጮች የታጀበ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን የራሱን ኢምፓየር የሚገነባና ስሙን የሚተክል ሳይሆን ለእግዚአብሔር መንግስት የሚሮጥና በመንግስቱ እሴተ-ስርዓት የሚገዛ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በስሪ-ፒስ መድረክ ላይ የሚምነሸነሽ ሳይሆን ትህትናን እንደ ልብስ የለበሰና የዋህ የሆነ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በመድረክ ትወናው ደክሞት ላቡን መጥረጊያ ጨርቅ የያዘ ሳይሆን እግር ማበሻ ፎጣ የያዘ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም የሚነግድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ስም የሚያገለግልና ለእግዚአብሔር ስም ክብር የሚሰጥ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ካጣ ከነጣው የሚመነትፍ ሳይሆን ለሌለው የሚያካፍል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን የራሱን ፈቃድ በማድረግ የተጠመደ ሳይሆን "ፈቃድህ ትሁን" ብሎ የሚያስተምርም የሚኖርም፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የሚሰለጥን ሳይሆን ለሕዝቡ ጥቅምና እድገት የሚለፋ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ከኋላ ሆኖ ሕዝቡን የሚያስበላ ሳይሆን ከፊት ሆኖ ደጀን የሚሆን፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን እርሱ ዋናውን በልቶና ጠጥቶ ለሕዝቡ መናኛውንና ትርፍራፊውን የማያድል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ሕዝቡን የሆነ ቦታ ለመድረስ መነሻ ያደረገ ሳይሆን ሕዝቡ ራሱ መዳረሻው የሆነለት፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ሁለቷን አሳና አምስቷን ቂጣ የቀደመ ብሎ የሚጎርስ ሳይሆን ለሕዝቡ እንድትሆን የሚያካፍል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በገንዘብና በራስ ፍቅር የተነደፈ ሳይሆን ለእግዚአብሔርና ለሕዝቡ ፍቅር የተሸነፈ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ሕዝቡ ውስጥ እንዴት አድርጌ ራሴን ልትከልባቸው ብሎ የሚጨነቅ ሳይሆን "ክርስቶስ እስኪሳልባችሁ ድረስ ምጥ ይዞኛል" የሚል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ጎልያድ ሲመጣ ሕዝቡን ጥሎ የሚፈረጥጥ ሳይሆን በተግዳሮት ፊት እግዚአብሔርን ታምኖ ለሕዝቡ ዘብ የሚቆም፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ጥሪ አለኝ ብሎ ኪሱ ሲሞላ "አዲዮስ" የሚል ሳይሆን ጥሪው የማያረጅበትና በጥሪው ጸንቶ የሚቆም፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ለማንኛውም ብሎ ባጣ ቆየኝ የደበቀ ሳይሆን በሙሉ ልቡ እግዚአብሔርን አምኖና ታምኖ ሕዝቡን የሚያገለግል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ትምህርት እምቢ ስላለውና ንግድ ስለፎረሸበት ሳይሆን በእውነት የተጠራና ለጥሪውም ዋጋ የሚከፍል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን ከሰው ወይም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የሆነ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን እንደ አቤሴሎም የሚፈልገውን እስቲያገኝ ድረስ በር ላይ ቆሞ ወጪ ወራጁን የሚስም ሳይሆን ያለምንም ድብቅ አጀንዳ ብድራቱን ከእግዚአብሔር ብቻ ጠብቆ የሚያገለግል፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን በዛሬ ብቻ የታወረ ሳይሆን ዛሬ ላይ ሆኖ ነገ የሚታየው፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን የከተማ ዜንጦ ሳይሆን አፍጋኒስታንም ቢሆን ለመሄድ የተዘጋጀ፡

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን አለም-አቀፋዊ ሳይሆን እዛው ባለበት አራት በአራት ውስጥ ለውጥ የሚያመጣ፡ ሎካሉም በሆነልን እንኳን ኢንተርናሽናሉ።

ባለ ራዕይማ ይፈለጋል፤
ነገር ግን . . . . . . . .

ይልቃል ዳንኤል
@nazrawi_tube
2.4K viewsΒενιαμίν, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 06:33:01 መልስ እስኪመጣ ጸልዩ

አንዳንድ ቀን ለመጸለይ ፈልገን አንደበት ይለጉማል። ለመንበርከክ ቁርጭምጭሚት ይዝላል። በጸሎት ደብተራችንን ላይ የተመዘገቡ ነገር ግን ያልተመለሱ በርካታ የጸሎት ዓርዕስቶቻችንን ያየ ዓይናችን፣ ''ዛሬስ ባነባ ምን አዲስ ነገር ሊፈጠር?" በማለት ለመጨፈን ያንገራግራል።

የዚህኔ እንዲህ እናስብ። የብዙ ዘመን የሀና እንባኮነው ሳሙኤልን የወልደው። ደግሞስ የዘካሪያስ ጸሎት መች በዋዛ ቀረ፣ ለመሲሑ መንገድ ጠራጊ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ወገብ እንዲወጣ ምክንያት ሆኖ የለ?! ጌታችንስ ሲያስተምር አንድ ጨካኝ ዳኛ ንዝነዛ ሰልችቶት አያሌ ቀን እየተመላለሰች ላስጨነቀችው መበሊት ከፈረደላት "እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ለሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሳቸው ለምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?" አላለም ?!(ሉቃ 18፥7) ተስፋማ አለ። እንደ ቃሉ የተጸለየ ጸሎት በዋዛ አይቀርም፣ እንደ ፈቃዱ ምላሹ ልክ ጴጥርስ ለእርሱ ተሰብስበው ሲጸልዩበት የነበረውን የእነ ማርቆስን ቤት እንዳንኳኳ እንዲሁ ከደጃችን የከሰታል።

ሳይታክቱ መጸለይ መልሱ ከደጅ እስኪቆም ነው። ጸልዩ!

natty alex
@nazrawi_tube
2.1K viewsΒενιαμίν, 03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 15:37:53
1.7K viewsΒενιαμίν, 12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 21:23:10 “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።

— ገላትያ 1፥8
1.7K viewsΒενιαμίν, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 20:42:15 በፈረንጆች አቆጣጠር በግምት 2008 ዓ.ም በአራት ኪሎ ዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ ሁለት ሺህ ለሚሆኑ የኮሌጅ/ ሃይስኩል (?) ክርስቲያን ተማሪዎች ኢቫሱ ባቀረበልን ጥያቄ መሰረት እኔ ሰሎሞን ጥላሁን፣ ወንድም ምኒልክ አስፋውና ወንድም ተስፋዬ ሮበሌ ስለ Secret / "ሚስጥሩ" ትምህርት እንድናቀርብ ተጠይቀን አቅርበን ነበር፡፡

አሁን በዚህ ሰሞን ወንድም ጌታነህ ሔራሞ ያቀረበውንም ሙግት ተመለከትኩና ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ የሁላችንም ዘመን ጩኸት አንድ ኣይነት መሆኑ አስደነቀኝ

አሁን ሚስጥሩ ግልጥ ሆኖ አገር እያተራመሰ ስናይ "ይህ ህዝብ..." በሚል ስሜት ተይዘናል፡፡ ያን ጊዜ እኔ ያቀረብኩትን ወረቀት ከድሮው ፎንት እንደምንም ለመቀየር ሞክሬ የሚከተለውን መክፈቻ ንግግር አገኘሁና አንድ ገጽ ለምትታገሱ አንባብያንና ምናልባት ከሁለት ሽሆቹ ጥቂቶች ካላችሁ ለማስታወስ እነሆ ልበለችሁ... የዛሬ 15 ኣመት ከተናገርኩት ላይ አንዲት ፊደል እንኳ አልጨመርኩበትም!

[በመጻሕፍት ገበያ እሽቅድድም በድንገት ፈትልኮ የወጣ፣ ቀድመውት ከወጡ አቻዎቹም ከእነ ዳቬንቺ ኮድና ሃሪ ፖተር ይልቅ በድንገት የገበያውን ማእበል ያግለበለበ መጽሐፍ ነው። ርእሱ መልስ ፈላጊ ለሆነው የሰው ልጅ አእምሮ ማራኪ ነው ቀለሙና የሽፋኑ ገጽታ በዘይት ያማረ ጥርብ ጣውላ ይመስላል፣ ደምቆ ዓይን አይወጋም፣ ፈዞም አይሰወርም።

በመጽሐፉ ውስጥ የተነሱ ርእሰ ጉዳዮች አይመለከተኝም የሚል ከቶውንም ቢሆን አይኖርም። የጥረትና የግረት ምክንያቶች በመሪ ርእሰ ጉዳይነት ከነፈጣን መፍትሔአቸው ተዘርዝረዋል። እሺ ባይ ሁሉ ተጠቃሚ እንደሆነ ሙሉ ተስፋ ይሰጣል። ደሃን እንደሚያበለጽግ፣ ባለጠጋን እንደሚያናጥጥ፣ በሽተኛን እንደሚፈውስ፣ ጤነኛን እንዳይታመም እንደሚያደርግ የጠበቀና የማያወላዳ ተስፋ ይሰጣል።

በትዳር በሥራ በሕይወትህ ወይ ደግሞ ገንዘብ በማጣት አዝነሃል? አዕምሮህን ተጠቀም የተሻለውን ማንነትህን አስብ ፕዘቲቭ አስተሳሰቦች ይለውጡሃል የምታውቃቸውን ማንኛውንም ዓይነት መልካም ነገሮች ሁሉ ይስቡልሃል ይህ የማይታመን ይመስልህ ይሆናል ግዴለም ደግመህ አስብ በሳይንስም የተደገፈ ነውና
ታዋቂው የሲ ኤን ኤን ቶክ ሾው አቅራቢ

ታዲያ እርሱ እንዲህ ያስተዋወቀውን መጽሐፍ ማን በቀላሉ ያየዋል!

በእንግድነት በሔድኩበት በአንድ ቤ ት ውስጥ ከአልጋው ፊት ለፊት በቁም ሳጥኑ ከፍ ባለ የመዝጊያ ጠርዝ የተለጠፉ ሁለት ብሮች አየሁ የመለጠፋቸው ምክንያት የገባኝ ከጥቂት የቆይታ ቀናት በኃላ ነው በዚያ ቤት ውስጥ ነዋሪ የሆነ ወጣት ካነበበው አንድ መጽሐፍ የተነሣ የብር ሐሳብ ብርን ይስባል ለዚህም ብርን ግድግዳ ላይ ለጥፎ ማፍጠጥ ወይም ስለ ብሩ ማሰላሰል የብር ሐሳብን ወደ ብር ይለውጣል

በውጪ አገር የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ የኮሌጅ ተማሪ ቡና እየጠጣን ስለ ትምህርት ቤት ጉዳይ ስናወራ የአንድ ትምህርት ፕሮፌሰር ቫይብ /ቫይብሬሽን/ ወይም ከውስጡ የሚወጣው ነዛሪ ኤሌክትሪክ ሲያስቸግረው እንደ ከረመ አጫወተኝ ምንድን ነው ይሄ ቫይብ ብዬ ብጠይቀው የሰውየው ኔጋቲቭ የኤሌክትሪክ ንዝረት ከእኔ ከሚወጣው ጋር በመጋጨት ተጽእኔ ያሳድርብኛል በኃላ ሁኔታውን ሳጣራ የሚከተለው አንድ ህቡዕ /ስውር/ እምነት ያለው ሰው እንደሆነ አወቅሁ

«ሚስጥሩ´ ሚስጥሩ አንድ ነው እርሱ ሃይማኖታዊ መልእክት ነው መልእክቱም ሰው አምላክ ነው የሚለው ነው ለዚህ ነው ኢ አማኒያኑ /ኢቲስቶች/ የዚህ መጽሐፍ መልእክት ከሌሎች ሃይማኖች ይልቅ ያሳሰባቸው ምክንያቱም አሁን በሚስጥሩ የተነሳ ነባሩ አምላክ አለወይም የለም የሚለው ክርክር ሰው አምላከ ነው ወይስ አይደለም ወደሚለው ዞሯልና ነው

ዘ ሴክሬት የተባለው መጽሐፍ በቁሳዊው ዓለም ስላሉ ልዩ ልዩ ስኬቶችና የማግኛ ቀመራቸው /ፎርሙላ/ አኮብኩቦ ተሳፋሪውን ከያለበት ስፍራ ስበትን አስለቅቆ ሲያንሳፍፍ ከዋለ በኃላ ወደ ማክተሚያው ሲደርስ አንተ አንቺ አምላክ ነህ ከዚህ በኃላ በራስህ መንገድ ማረፍ ትችላለህ በማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ተሳፋሪዎቹን አየር ላይ ጥሎአቸው የሚሔድ በራሪ ቅዥት ነው:: ይሁን እንጂ በርካታ ክርስቲያናዊ ቃላትን በመውሰዱ አስተሳሰቡ በሙሉም ሆነ በከፊል ያመነው ማሕበረሰብ ውስጥ ለመግባት ያመቸዋል በተለይም የእምነትን ትምህርት በተለጠጠ መልኩ በሚያስተምሩት ቤተ ክርስቲያኖች አካባቢ ከምስባኩ /ከመድረኩ/ የተለመዱ ቃላትን ስለሚጠቀም እነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች ትምህርቶቻቸውንና የሚጠቀሙባቸውን ቃላት ሊመረምሩ ይገባል ...]

መጋቢ ሰለሞን ጥላሁን
@nazrawi_tube
1.8K viewsΒενιαμίν, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 09:44:19 የመሳብ ሕግ ለጥብቅ ሳይንሳዊ  ማስረጃ ድጋፍ የለውም ( Lack of scientific evidence) ። ብዙ ጊዜ  የሚቀርበው እንደ ሁለንተናዊ መርህ ነው ፤ ጽንሰ ሓሳቡ ስለ ስበት ያነሳና ፣ በዚያ ውስጥ የሚነሱት የይገባኛል ጥያቄዎች ግን በሜታፊዚካል ወይም በግል ታሪኮች እና ተሞክሮዎች ላይ የተመሰረቱ ሆነው ይገኛሉ ፣በዚህ ምክንያት ሳይንቲስቶቹ አስተማማኝ ሳይንሳዊ ማስረጃ እንደሌለው ይናገራሉ።  

__
ሙሉውን ሀሳብ ለማንበብ፦
Instant view የሚለውን ይጫኑ
__

https://telegra.ph/ክፍል-3-የመሳብ-ሕግ-እምነቶች-06-23
2.3K viewsΒενιαμίν, 06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ