Get Mystery Box with random crypto!

መልስ እስኪመጣ ጸልዩ አንዳንድ ቀን ለመጸለይ ፈልገን አንደበት ይለጉማል። ለመንበርከክ ቁርጭምጭሚ | ናዝራዊ Tube

መልስ እስኪመጣ ጸልዩ

አንዳንድ ቀን ለመጸለይ ፈልገን አንደበት ይለጉማል። ለመንበርከክ ቁርጭምጭሚት ይዝላል። በጸሎት ደብተራችንን ላይ የተመዘገቡ ነገር ግን ያልተመለሱ በርካታ የጸሎት ዓርዕስቶቻችንን ያየ ዓይናችን፣ ''ዛሬስ ባነባ ምን አዲስ ነገር ሊፈጠር?" በማለት ለመጨፈን ያንገራግራል።

የዚህኔ እንዲህ እናስብ። የብዙ ዘመን የሀና እንባኮነው ሳሙኤልን የወልደው። ደግሞስ የዘካሪያስ ጸሎት መች በዋዛ ቀረ፣ ለመሲሑ መንገድ ጠራጊ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ወገብ እንዲወጣ ምክንያት ሆኖ የለ?! ጌታችንስ ሲያስተምር አንድ ጨካኝ ዳኛ ንዝነዛ ሰልችቶት አያሌ ቀን እየተመላለሰች ላስጨነቀችው መበሊት ከፈረደላት "እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ለሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሳቸው ለምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?" አላለም ?!(ሉቃ 18፥7) ተስፋማ አለ። እንደ ቃሉ የተጸለየ ጸሎት በዋዛ አይቀርም፣ እንደ ፈቃዱ ምላሹ ልክ ጴጥርስ ለእርሱ ተሰብስበው ሲጸልዩበት የነበረውን የእነ ማርቆስን ቤት እንዳንኳኳ እንዲሁ ከደጃችን የከሰታል።

ሳይታክቱ መጸለይ መልሱ ከደጅ እስኪቆም ነው። ጸልዩ!

natty alex
@nazrawi_tube