Get Mystery Box with random crypto!

ናዝራዊ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ nazrawi_tube — ናዝራዊ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @nazrawi_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.51K
የሰርጥ መግለጫ

ናዝራዊ: ማለት የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው።
@biblicalmarriage
On YT sub☞ https://bit.ly/2ZCsqFN
Inbox👉 @Nyouth_bot
--
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።
-- ኤር 6:16

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-11 09:37:49
በዐሥራ ስምንተኛ ክፍለ ዘመን፣ በምድረ አሜሪካ ለተነሣው መንፈሳዊ መነቃቃት ግንባር ቀደም አስተዋጽዖ እንዳደረገ የሚነገርለት ጆናታን ኤድዋርድስ፣ በግል ሕይወቱ ለመተግበር የቆረጠባቸውን ውሳኔዎቹን አማረ ታቦር፣ “ሰባዎቹ የጆናታን ኤድዋርድስ ቁርጠኛ ውሳኔዎች” በሚል ወደ አማርኛ የመለሰው ጽሑፍ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ
https://hintset.org/articles/jonathan-edwards-70-resolution/

--

@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
291 viewsΒενιαμίν, 06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 21:37:33
ሊዲያ ጥፋቷ ምንድነው?

ሊዲያ የምትኖረው ሀላባ ነው። ተማሪ ነች። እንደማንኛውም ተማሪ በትምህርት ቤቷ ተገኘች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አጠገብዋ ቆማ የነበረች አንዲት ሙስሊም ተማሪ መሬት ላይ ወደቀች። ይህች ልጅ በወደቀችበት ሆና "ኢየሱስ ጌታ ነው" አለች። (ልብ በሉ "ኢየሱስ ጌታ ነው!" ያለችው ሊዲያ አይደለችም የወደቀችው ተማሪ ነች) በቃ! የሆነው ይሄ ይኸው ነው።

የሚያስገርመው ግን ይህ ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ የወደቀችው ተማሪ ልጅ ቤተሰቦች ባቀረቡት ክስ ሊዲያ በፖሊስ ታሰረች። ቆይ የሊዲያ ጥፋት ምንድነው? ገፍትራ አልጣለቻት፤ በግድ አስፈራርታ "ኢየሱስ ጌታ ነው! በይ!" አላለቻት። ሙስሊሟ ልጅ የወደቀችው ራሷ! "ኢየሱስ ጌታ ነው" ያለችው ራሷ! ታዲያ ለምንድነው ሊዲያ የታሰረችው?

እንደሚሰማው ከሆነ የወደቀችው ተማሪ ቤተሰቦች በሊዲያ ላይ አቀረቡባት የተባለው ክስ "አስደግማባት ኢየሱስ ጌታ ነው እንድትል አደረገቻት" የሚል ነው። አሰቂኝም አሳዛኝም ነው። ይህንን ክስ የሚሰማ ሁሉ የሚያፍር ይመስለኛል።

እስኪ ፍረዱ፤ በትምህርት ገበታዋ ላይ ከመገኘቷ ውጪ የሊዲያ ጥፋቷ ምንድነው?

ቴዎድሮስ ተጫን
@nazrawi_tube
721 viewsΒενιαμίν, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 16:17:21
“የልጆቻችንን ቀጣይ ህይወት ብሩህ ልናደርግላቸው የምንችልባቸው ጥቂት መንገዶች አሉ። ከነዚህ መንገዶች መሃል ሠፊውና አስተማማኙ በውስጣቸው የንባብ ፍቅርን መዝራት ነው።”

---ማያ አንጄሎ
783 viewsΒενιαμίν, 13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 00:48:50 (ዐድዋን በማስመልከት ከ7 ዓመት በፊት የተጻፈ)

ክርስትና “ቅዱስ ጦርነት” ባይኖረውም፣ በነገረ መለኮቱ ዓለም "Just War" (ፍትሓዊ/ትክክለኛ/ተገቢ ጦርነት) ተብሎ የሚታወቅ ርእሰ ጉዳይ አለ። ጦርነት በምድር ላይ አይቀሬ በመሆኑ መስፈርት ተቀምጦለት “ፍትሓዊ/ትክክለኛ” ሊባል ይችላል፤ ከመስፈርቱ ከጎደለም ውጉዝ ይሆናል። በፓለቲካዊ ነገረ መለኮት (Political Theology) ውስጥ የሚተነተነው የ“ትክክለኛ ጦርነት” ንድፈ ሐሳብ፣ የጦርነቱን ተገቢ መሆን አለመሆን የሚወስን ብቻ አይደለም፤ በጦርነቱ ውስጥ እና ከጦርነቱ በኋላ መከናወን ስላለባቸውና ስለሌለባቸው ነገሮችም በዝርዝር ያስረዳል።

እነዚህን የፍትሓዊ ጦርነት መስፈርቶች ዘርዝሮ በማስቀመጥና በማበጃጀት ረገድ ተጠቃሹ የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ አውግስጢኖስ ነው፤ በኋላ ደግሞ ቶማስ አኳይናስ። እናም የትኛውንም ጦርነት በእነዚህ መስፈሪያዎች እየሰፈሩ ጦርነቱ “ትክክለኛ” መሆን አለመሆኑን ማስተንተን ይቻላል። “ትክክለኛ ጦርነት” በክርስትና አይወገዝም። ለምሳሌ የዓድዋ ጦርነትን ብንወስድ በጣልያኖች በኩል ከታየ የግፍ ጦርነት በመሆኑ ውጉዝ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል ሲካሄድ ግን ትክክለኛ እና ተገቢ ጦርነት ነው። ምክንያቱም፡-

• ጦርነቱ የግፍ ወረራን በመቃወም የተካሄደ ነው።

• ጦርነቱ የታወጀው በአገሪቱ ሕጋዊ መሪ ነው፤ በዳግማዊ አጤ ምኒልክ።

• ጦርነቱን ለማስቀረትና በሰላማዊ መንገድ ችግሩን ለመፍታት በቅድሚያ ብዙ ጥረት ተደርጓል።

• በጦርነቱ የተማረኩ ጣልያናውያንም በእንክብካቤ ተይዘዋል እንጂ ግፍ አልተፈጸመባቸውም።

• ጦርነቱ ሲያበቃም ምኒልክ የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ሰላምን መልሰው ለማምጣት ጥረት አድርገዋል።

• የተናቀውና የተገፋው ጥቁር ሕዝብ ዐንገቱን ቀና አድርጎ ሊሄድ መቻሉ ከጦርነቱ ትሩፋቶች መካከል ሊጠቀስ ይችላል።

https://t.me/PaulosFekadu
301 viewsΒενιαμίν, 21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 21:57:50 ከላይ websitu ላይ ገብታች ያላነበባችሁ INSTANT VIEW የሚለውን ተጭናችሁ አንብቡ
291 viewsΒενιαμίν, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 21:56:35 ጳውሎስ ፈቃዱ “እነዚህ ወንጌላዊ ክርስቲያኖችን አይወክሉም፤ ከእኛም ጋር በሃይማኖት አንድ አይደሉም። እነርሱ ነን ስላሉ ብቻ የእኛ አካል አድርገን አንወስዳቸውም። በሃይማኖት አንድ አይደለንም፤ እኛንም ሊወክሉን አይችሉም” ሲሉ ጠንከር ያለ ትችታቸውን ይሰነዝራሉ።

የወንጌላዊ አብያተ ክርስትያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ጻድቁ አብዶም፣ በመጋቢ ጳውሎስ ሀሳብ ይስማማሉ።

የሥነ መለኮት መምህሩ ተካልኝ ነጋ (ዶ/ር ) በበኩላቸው በምዕራቡ ዓለም እነዚህ ሰዎች የሚጠሩበት ስያሜ ፓስቶፕረነር (pastopreneur ) እንደሚባል በመጥቀስ “ነጋዴዎች” ይሏቸዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/czq0xq7zzv9o
309 viewsΒενιαμίν, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 13:20:33 በኢትዮጵያ በወንጌላውያን አማኞች ስም እየተበራከቱ የመጡት “ሐሰተኛ ነብያት እና ፓስተሮች”

ይህችን ጽሁፍ ሁሉም አማኝ ያንብብ

https://www.bbc.com/amharic/articles/czq0xq7zzv9o
-----

@nazrawi_tube
221 viewsΒενιαμίν, 10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 09:17:39 ክርስቶስ አብ ውስጥ የሆነውን ያህል እኛም በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ ነን፡ ከክርስቶስ የተረፈውን አብ ሳይሆን የምንካፈለው እራሱ ክርስቶስ "የተካፈለውን" ወይም "አለሁበት" ያለውን አብ ነው፡ ክርስቶስ ያለበት አብና እኛም በክርስቶስ በኩል ያለንበት አብ አንድ አይነት ነው፡ የክርስቶስ አብ ትልቅ የኛ አብ ደግሞ ትንሽ ብሎ ነገር የለም፡ "ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ" ሲልም ይህንን እውነት ያገናዘበ ሊሆን ይችላል።

የቤተክርስትያን አበው የነበሩት አትናቲዮስም፦

"እርሱ የሆነውን ሊያደርገን እኛ የሆንነውን ሆነ"

ማለታቸው ይህንን እውነት የሚያንጸባርቅም ይመስለኛል።

ባህር ውስጥ ጠልቀው አለመርጠብ የማይቻለውን ያህል ክርስቶስም ውስጥ ሆኖ አብ ውስጥ አለመሆን አይቻልም፡ እንደ ዮሐንስ እሳቤ It is simply Impossible.

እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል የሰጠን "መብት" ምን ያህል አይተመኔ መሆኑን ልብ ይሏል፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለዛ ማዶ ጠርቶን በምንሰማውና በምናየው እንዲሁም ባደግንበት አመለካከት ምክንያት ራሳችንን እዚህ ማዶ ልናስቀረው አይገባንም፡ አንተም፣ አንቺም፣ እኔም በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ ነን፡፡

በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ በመሆን ከመለኮታዊው ባሕርይ ተካፋይ ሆነናል፡ ምንም አይነት የስነ-አፈታት ጂምናስቲክ አያስፈልገውም፡ ክርስቶስ በአብ እንዳለ እንዲሁ እኛም በክርስቶስ በኩል በአብ አለን፡ ሲጀምርስ ክርስቶስ እንዲህ አይደል ያለው፦

"እኛም አንድ እንደሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፣ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፣ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፣ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ"

Do we really believe this?

ከእርሱም ጋር ብንጸና ደግሞ ከእርሱ ጋር አብረን የእግዚአብሔር ወራሾች ነን።

መስማት ያለብን የኤርትራ ባህር፣ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ እባብና ጊንጡን፣ አማሌቅን፣ ወይም የኢያሪኮን ቅጥር ሳይሆን ወደ ማንነቱ የጠራንን አብን ብቻ ነው፡ ክርስቶስም ይህንን እውነት በመናገር ወደ አብ ሕይወት እየጠራን ነው።

ግባችን "መንግሥተ-ሰማይ" ሳይሆን የእግዚአብሔር ህልውና ነው።

እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል ብሎናል የእግዚአብሔር መንፈስ በራሱ በዮሃንስ በኩል።

የዮሃንስ ወንጌል ምጡቅና ጥልቅ ነው፡
ስለዚህ ወንጌል እግዚአብሔር ይመስገን:
በተጻፈበትም መንፈስ እንድንረዳው ማስተዋልን ይሰጠን።


ይሉ ዳኑ
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube
32 viewsΒενιαμίν, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 18:55:17 ˙ ትንሽ ስለ “ሪቫይቫል” መቼም በራሱ በእግዚአብሔር ህልውና፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እርሱ በተዘከረው እውነት እንዲሁም በሰው ልጆች ታሪክ መካከል ጣልቃ እየገባ ራሱን ያለምስክር እንደማይተው የምናምን ከሆነ በሪቫይቫል አለማመን አንችልም። ሰሞኑን ከአዝበሪው ዩኒቨርሲቲ ሪቫይቫል የተነሳ የተለያዩ ምልከታዎች ሲሰነዘሩ ማስተዋል ችለናል፡ ይሄ ትክክል ነው ያኛው ደግሞ ስሁት ነው ወደሚለው ፍረጃ…
344 viewsΒενιαμίν, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 18:54:56 ˙ ትንሽ ስለ “ሪቫይቫል”

መቼም በራሱ በእግዚአብሔር ህልውና፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እርሱ በተዘከረው እውነት እንዲሁም በሰው ልጆች ታሪክ መካከል ጣልቃ እየገባ ራሱን ያለምስክር እንደማይተው የምናምን ከሆነ በሪቫይቫል አለማመን አንችልም።

ሰሞኑን ከአዝበሪው ዩኒቨርሲቲ ሪቫይቫል የተነሳ የተለያዩ ምልከታዎች ሲሰነዘሩ ማስተዋል ችለናል፡ ይሄ ትክክል ነው ያኛው ደግሞ ስሁት ነው ወደሚለው ፍረጃ ውስጥ መግባቱ አስፈላጊ ባይሆንም በኔ ግምት መንፈሳዊ መነቃቃትን አስመልክቶ ልንጋፋቸው የማይገቡን ጥቂት ነጥቦች ያሉ ይመስሉኛል፡፡

~ ፩ ~

አንድ ሰው፣ ወይም አንድ አጥቢያ ቤተክርስትያን፣ ወይም የአንድ ዘመን አማኞች ሪቫይቫል መናፈቃቸው በራሱ የሆነ ነገር ትክክል አለመሆኑን ወይም የሆነ ነገር እንደ ጎደላቸው የሚጠቁም ምልክት ነው፡ በታሪክ ውስጥ የተከሰቱትን፣ ወይም አሁን እየሆነ ካለው “የአዝበሪው መነቃቃት፣ ካልሆነም በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር በሰዎች መካከል ያደረገውን ጉብኝት በማስተዋል ያንን አሁንና እዚህ እንዲሆን መናፈቅ ቢያንስ ቢያንስ አሁን በያዝነው ነገር አለመርካታችንንና ሌላ የምንራበው ነገር እንዳለ የሚያስረዳ ነው፡ ይሄ ደግሞ ፍጹም የጤነኝነት ምልክት እንጂ የመታመም ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባውም፡ የጤና-ቢስነት ምልክት ሊሆን የሚችለው እንደዚህ አይነት ርሃብና ናፍቆት ባይኖር ነበር።

ውሃ ጠጥቶ ወዲያው “ድገሙኝ” የሚል ሰው ገና እንዳልረካ ነው የሚያሳየው እንጂ መታመሙን አይደለም፡ እንዲሁም ሪቫይቫልን መናፈቅ የሆነ ነገር እንደጎደለን ከማሳየቱ ባሻገር ፍጹም የሆነ የጤንነት ማረጋገጫ ነው፡ ካልጠማን ወይም ካልራበን እንፍራ ምክንያቱም በዚያው ይዞን ሊሄድ ይችላልና።

~ ፪ ~

ሪቫይቫልን ፈጽሞ የምንኮርጀው ወይም የምናስመስለው ጉዳይ አይደለም፡ በቅዱሳን ሕብረት ውስጥ ብዙ ነገር ማስመሰል ይቻላል፡ ስብከትን፣ መዝሙርን፣ ጸሎትን እንዲሁም ሌሎች ሌሎችን፡ መንፈሳዊ መነቃቃትን ግን ፈጽሞ ማስመስል አይቻልም፡ ምክንያቱም ሪቫይቫል ከንግግር፣ ከመዝሙርና ከስብከት በተለየ መልኩ ሰፊ ወደ ሆነ የሕይወት ለውጥና ጥልቅ ወደ ሆነ እግዚአብሔርን ወደ መፍራት መንገድ ይመራልና፡፡

ሪቫይቫል “የመልካም ወጣት” ፕሮግራም አይደለም።

እግዚአብሔር ቸብ ቸብ አድርጎ ወይም እንደ ጠበል ረጨት ረጨት አድርጎን ሊያልፍ ሳይሆን የሚመጣው ሰዎች ያረከሱትን ስም ለመቀደስ የጣሉትን ክብር ደግሞ ለማንሳትና እርሱ ወደሚፈልገው የሕይወት ቀጠና ለማስገባት ነው፡ ጠቅለል ባለ መልኩ የሚኮረጅ መነቃቃት የለም፤ አይሄድ አይመጣ በሆነ መልኩ የሸመደድነው ሪቫይቫል ካለ ሲጀምርም ሪቫይቫል አልነበረም ማለት ነው፡ እንደ ግብጽ ጠንቋዮች የተወሰነ መንገድ ሙሴን ልናስመስለው እንችል ይሆናል ነገር ግን መጨረሻ ላይ እባባችን በሙሴ እባብ መዋጧ አይቀሬ ነው።

~ ፫~

ሪቫይቫል ፈጽሞ እኛ በምንጠብቀው መንገድና መለኪያ ይመጣል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት የለብንም፡ ሪቫይቫል ፈልገንም፣ የሚመጣበትንም መንገድ ወስነንም አይቻልም፡ በሪቫይቫል ወቅት የመነቃቃቱ ባለቤት “ይቀበሉኛል ወይስ አይቀበሉኝም” የሚል ሥሌት ውስጥ ከማንም ጋር አይገባም፡ ጥጉን ይዘን ስንፈላሰፍበት እንከርማለን እንጂ እግዚአብሔር ማናችንንም ሪቫይቫል ስለመሆኑ ለማሰመን ጊዜ አያጠፋም፡ በዋነኘናት ሲጀምርም ስለ እኛ ስይሆን ስለ ስሙ ነው፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥም ይሁን እንዲሁም በታሪክ ውስጥ በእግዚአብሔር ስራ ላይ “ሲፈላሰፉ” ራሱ እግዚአብሔር ያመለጣቸውና ጥጋቸውን እንደያዙ የቀሩ ሰዎች አሉ፡ ልክ ያ ንጉሱ ይደገፈው እንደነበረው አይነት ሰው ማለት ነው፡ “በውኑ እግዚአብሔር የሰማይን መስኮት ቢከፍት ይህ መሆን ይችላልን?” ብሎ አለ፡ አርቆ ማሰቡ ነበር፡ ነገር ግን የሰማይና የምድሩን ጌታ እየወሰነው እንደሆነ አላስተዋለም ነበር፡፡

እግዚአብሔር በእውነት በሚሰራበት ወቅት የሚያዋጣው ብዙ ማውራቱና መፈላሰፉ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ በአንድ መሰመሩ ነው፡፡

አዕምሮአችንን ጥለን ዝም ብለን መጋለብ ባይገባንም እግዚአብሔር ስራ ሲሰራ ግን ጥጉን ይዘን በሚጢጢዬ አዕምሮአችን ተፈላስፈን ከጨርስን በኋላ አይደለም የምንቀላቀለው፡ የሚገርመው ሪቫይቫሉ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ሁሉ በአዕምሮአችን ብንመራመርበት መልስ ላናገኝለት ሁሉ እንችል ይሆናል፡ በእንደዚህ አይነት ወቅት ከፍልስፍናው ይልቅ እግዚአብሔር እንዲረዳንና ማስዋልን እንዲሰጠን መጸለዩ ብቻ ነው የሚያዋጣው፡ አለበለዚያ ከእግዚአብሔር ጋር መሸዋወድ ሁሉ ይቻላል፡ ይሄንን ልብ እንበል፤ እግዚአብሔር እኛ ልንቀበለው ወይም የስነ-መለኮት ሳጥናችንን ሊሞላ በሚችል መልኩ ብቻ ይመጣል ብለን ካሰብን ከሪቫይቫሉ ባለቤት ጋር የመተላለፍ በሩ ሰፊ ሊሆንብን ይችላል፡ እግዚአብሔር ከሳጥናችን የሚያልፍ ነገር ሊያደርግ ይችላል፡ ስለዚህ ጉዳዩ ቀመራዊ ሳይሆን “መንፈሳዊ” ብቻ ሊሆን ይችላል።

~ ፬ ~

ሪቫይቫልን ስናስብ የሆነ ሙታን ከመቃብር እየተጎተቱ ሲወጡ፣ እውራን ሲበሩና አንካሶች ሲዘሉ ብቻ አድርገን ማሰብ የለብንም፡ የመንፈሳዊ መነቃቃት ትልቁ አላማ ሰዎችን በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ከልባቸው በመውቀስ ንስሃ እንዲገቡ ማድረግና እግዚአብሔርን ወደሚመስል ሕይወት መጥራት ነው፡ በሪቫይቫል ወቅት እግዚአብሔር ታላላቅ ድንቅና ታምራትን በማድረግ ሰዎችን የማስደመም አባዜ የለበትም፡ በአብዛኛው ወቅሶና አሳምኖ እንጂ አስደንቆና አስገድዶ አይደለም የሚለውጠው፡ ጉዳዩ የ impression ሳይሆን የ conviction ነው።

ስለዚህ አንዳንድ እኛ የሪቫይቫል መለኪያ ብለን ያስቀመጥናቸው ወይም የምናምናቸው ነገሮች ባይኖሩም እንኳን ነገርዬው እግዚአብሔር ሊኖርበት ይችላል፡ ከላይ እንዳልነው ቁም ነገሩ እኔ እቀበለዋለሁ ወይስ አልቀበለውም የሚለው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚመጣበት መንገድ ነው፡ ሲጀምር እኔ ማን ነኝ?!

~ ፭ ~

ሪቫይቫልን የልብ እንጂ የቦታ ጉዳይ አድርገን ማሰቡ ያን ያህልም ተገቢ ላይሆን ይችላል፡ እንኳን መቶ ሰው አይደለም የዓለም ሕዝብ እንዳለ አዝበሪ ቢመጣ ምንም ሳይሆን እንደመጣ በዛው ሊመለስ ይችላል፡ አዝበሪ ስለሄድን የሚወድቅብን መንፈስ እንዳለ አድርገን ማሰብም አግባብነት ላይኖረው ይችላል፡ እዛው አዝበሪ ቻፕል ከነበሩት ውስጥ ስንቶቹ “ተነኩ” ወይም የሪቫይቫሉ ተጽዕኖ አገኛቸው ብሎ መጠየቅም ተገቢ ይመስለኛል፡ ለምሳሌ ያህል ከወጡት ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደምናስተውለው እዛው ስብስብ ውስጥ የሚያለቅሱትና “የሚዘሉት” ጥቂቶች እንጂ አብዛኛው ሰው እጁን አጣምሮ ነበር የቆመው፡ ለምን እነዚህኞቹ ዘለሉና አለቀሱ እነኛዎቹስ ለምን አልዘለሉምም አላለቀሱምም የሚለው ክርክር ውስጥ ለመግባት ሳይሆ እዛው አዝበሪ ቻፕል ውስጥ ተገኝቶም እንደነበራት ሆኖ ወደቤቱ የሚመለስም አይጠፋም ለማለት ያህል ነው፡ የሚያዋጣው አዝበሪ ድረስ ለመሄድ መናፈቅ ሳይሆን ( መሄድ በራሱ ምንም ክፋት የለውም ) እዛው ያለንበት ቦታ እግዚአብሔር እሳቱን እንዲጥል መንበርከኩ ነው፡፡

የአዝበሪው ጌታ የሁሉ ጌታ ነው።
347 viewsΒενιαμίν, 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ