Get Mystery Box with random crypto!

ሊዲያ ጥፋቷ ምንድነው? ሊዲያ የምትኖረው ሀላባ ነው። ተማሪ ነች። እንደማንኛውም ተማሪ በትምህርት | ናዝራዊ Tube

ሊዲያ ጥፋቷ ምንድነው?

ሊዲያ የምትኖረው ሀላባ ነው። ተማሪ ነች። እንደማንኛውም ተማሪ በትምህርት ቤቷ ተገኘች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ አጠገብዋ ቆማ የነበረች አንዲት ሙስሊም ተማሪ መሬት ላይ ወደቀች። ይህች ልጅ በወደቀችበት ሆና "ኢየሱስ ጌታ ነው" አለች። (ልብ በሉ "ኢየሱስ ጌታ ነው!" ያለችው ሊዲያ አይደለችም የወደቀችው ተማሪ ነች) በቃ! የሆነው ይሄ ይኸው ነው።

የሚያስገርመው ግን ይህ ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ የወደቀችው ተማሪ ልጅ ቤተሰቦች ባቀረቡት ክስ ሊዲያ በፖሊስ ታሰረች። ቆይ የሊዲያ ጥፋት ምንድነው? ገፍትራ አልጣለቻት፤ በግድ አስፈራርታ "ኢየሱስ ጌታ ነው! በይ!" አላለቻት። ሙስሊሟ ልጅ የወደቀችው ራሷ! "ኢየሱስ ጌታ ነው" ያለችው ራሷ! ታዲያ ለምንድነው ሊዲያ የታሰረችው?

እንደሚሰማው ከሆነ የወደቀችው ተማሪ ቤተሰቦች በሊዲያ ላይ አቀረቡባት የተባለው ክስ "አስደግማባት ኢየሱስ ጌታ ነው እንድትል አደረገቻት" የሚል ነው። አሰቂኝም አሳዛኝም ነው። ይህንን ክስ የሚሰማ ሁሉ የሚያፍር ይመስለኛል።

እስኪ ፍረዱ፤ በትምህርት ገበታዋ ላይ ከመገኘቷ ውጪ የሊዲያ ጥፋቷ ምንድነው?

ቴዎድሮስ ተጫን
@nazrawi_tube