Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቶስ አብ ውስጥ የሆነውን ያህል እኛም በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ ነን፡ ከክርስቶስ የተረፈውን | ናዝራዊ Tube

ክርስቶስ አብ ውስጥ የሆነውን ያህል እኛም በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ ነን፡ ከክርስቶስ የተረፈውን አብ ሳይሆን የምንካፈለው እራሱ ክርስቶስ "የተካፈለውን" ወይም "አለሁበት" ያለውን አብ ነው፡ ክርስቶስ ያለበት አብና እኛም በክርስቶስ በኩል ያለንበት አብ አንድ አይነት ነው፡ የክርስቶስ አብ ትልቅ የኛ አብ ደግሞ ትንሽ ብሎ ነገር የለም፡ "ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ" ሲልም ይህንን እውነት ያገናዘበ ሊሆን ይችላል።

የቤተክርስትያን አበው የነበሩት አትናቲዮስም፦

"እርሱ የሆነውን ሊያደርገን እኛ የሆንነውን ሆነ"

ማለታቸው ይህንን እውነት የሚያንጸባርቅም ይመስለኛል።

ባህር ውስጥ ጠልቀው አለመርጠብ የማይቻለውን ያህል ክርስቶስም ውስጥ ሆኖ አብ ውስጥ አለመሆን አይቻልም፡ እንደ ዮሐንስ እሳቤ It is simply Impossible.

እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል የሰጠን "መብት" ምን ያህል አይተመኔ መሆኑን ልብ ይሏል፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለዛ ማዶ ጠርቶን በምንሰማውና በምናየው እንዲሁም ባደግንበት አመለካከት ምክንያት ራሳችንን እዚህ ማዶ ልናስቀረው አይገባንም፡ አንተም፣ አንቺም፣ እኔም በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ ነን፡፡

በክርስቶስ በኩል አብ ውስጥ በመሆን ከመለኮታዊው ባሕርይ ተካፋይ ሆነናል፡ ምንም አይነት የስነ-አፈታት ጂምናስቲክ አያስፈልገውም፡ ክርስቶስ በአብ እንዳለ እንዲሁ እኛም በክርስቶስ በኩል በአብ አለን፡ ሲጀምርስ ክርስቶስ እንዲህ አይደል ያለው፦

"እኛም አንድ እንደሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፣ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፣ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፣ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ"

Do we really believe this?

ከእርሱም ጋር ብንጸና ደግሞ ከእርሱ ጋር አብረን የእግዚአብሔር ወራሾች ነን።

መስማት ያለብን የኤርትራ ባህር፣ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ እባብና ጊንጡን፣ አማሌቅን፣ ወይም የኢያሪኮን ቅጥር ሳይሆን ወደ ማንነቱ የጠራንን አብን ብቻ ነው፡ ክርስቶስም ይህንን እውነት በመናገር ወደ አብ ሕይወት እየጠራን ነው።

ግባችን "መንግሥተ-ሰማይ" ሳይሆን የእግዚአብሔር ህልውና ነው።

እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል ብሎናል የእግዚአብሔር መንፈስ በራሱ በዮሃንስ በኩል።

የዮሃንስ ወንጌል ምጡቅና ጥልቅ ነው፡
ስለዚህ ወንጌል እግዚአብሔር ይመስገን:
በተጻፈበትም መንፈስ እንድንረዳው ማስተዋልን ይሰጠን።


ይሉ ዳኑ
@nazrawi_tube
@nazrawi_tube