Get Mystery Box with random crypto!

(ዐድዋን በማስመልከት ከ7 ዓመት በፊት የተጻፈ) ክርስትና “ቅዱስ ጦርነት” ባይኖረውም፣ በነገረ | ናዝራዊ Tube

(ዐድዋን በማስመልከት ከ7 ዓመት በፊት የተጻፈ)

ክርስትና “ቅዱስ ጦርነት” ባይኖረውም፣ በነገረ መለኮቱ ዓለም "Just War" (ፍትሓዊ/ትክክለኛ/ተገቢ ጦርነት) ተብሎ የሚታወቅ ርእሰ ጉዳይ አለ። ጦርነት በምድር ላይ አይቀሬ በመሆኑ መስፈርት ተቀምጦለት “ፍትሓዊ/ትክክለኛ” ሊባል ይችላል፤ ከመስፈርቱ ከጎደለም ውጉዝ ይሆናል። በፓለቲካዊ ነገረ መለኮት (Political Theology) ውስጥ የሚተነተነው የ“ትክክለኛ ጦርነት” ንድፈ ሐሳብ፣ የጦርነቱን ተገቢ መሆን አለመሆን የሚወስን ብቻ አይደለም፤ በጦርነቱ ውስጥ እና ከጦርነቱ በኋላ መከናወን ስላለባቸውና ስለሌለባቸው ነገሮችም በዝርዝር ያስረዳል።

እነዚህን የፍትሓዊ ጦርነት መስፈርቶች ዘርዝሮ በማስቀመጥና በማበጃጀት ረገድ ተጠቃሹ የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ አውግስጢኖስ ነው፤ በኋላ ደግሞ ቶማስ አኳይናስ። እናም የትኛውንም ጦርነት በእነዚህ መስፈሪያዎች እየሰፈሩ ጦርነቱ “ትክክለኛ” መሆን አለመሆኑን ማስተንተን ይቻላል። “ትክክለኛ ጦርነት” በክርስትና አይወገዝም። ለምሳሌ የዓድዋ ጦርነትን ብንወስድ በጣልያኖች በኩል ከታየ የግፍ ጦርነት በመሆኑ ውጉዝ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል ሲካሄድ ግን ትክክለኛ እና ተገቢ ጦርነት ነው። ምክንያቱም፡-

• ጦርነቱ የግፍ ወረራን በመቃወም የተካሄደ ነው።

• ጦርነቱ የታወጀው በአገሪቱ ሕጋዊ መሪ ነው፤ በዳግማዊ አጤ ምኒልክ።

• ጦርነቱን ለማስቀረትና በሰላማዊ መንገድ ችግሩን ለመፍታት በቅድሚያ ብዙ ጥረት ተደርጓል።

• በጦርነቱ የተማረኩ ጣልያናውያንም በእንክብካቤ ተይዘዋል እንጂ ግፍ አልተፈጸመባቸውም።

• ጦርነቱ ሲያበቃም ምኒልክ የሰላም ስምምነት ተፈራርመው ሰላምን መልሰው ለማምጣት ጥረት አድርገዋል።

• የተናቀውና የተገፋው ጥቁር ሕዝብ ዐንገቱን ቀና አድርጎ ሊሄድ መቻሉ ከጦርነቱ ትሩፋቶች መካከል ሊጠቀስ ይችላል።

https://t.me/PaulosFekadu