Get Mystery Box with random crypto!

ሥነ መለኮት እና የእኔ ምልከታ የሰው ልጅን የአመለካከት፤ የዕይታ ዉስንነት አለበት፡፡ ስለዚህ ዬ | ናዝራዊ Tube

ሥነ መለኮት እና የእኔ ምልከታ

የሰው ልጅን የአመለካከት፤ የዕይታ ዉስንነት አለበት፡፡ ስለዚህ ዬትኛውም አመለካከትም ኾነ ሥነ መለኮታዊ እሳቤ ዉሱን ነው፡፡ የክርስትና መንገድ እውነቱ የማይለወጥ፤ መዳኛው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ የእኔም ኾነ የማንም ሰው ሥነ መለኮታዊ አቋም አመለካከት ብቻ ነው፡፡ ይህ አመለካከት በሙግት መልክ ቀርቦ፤ ካሉት አመለካክቶች ጋር ተንጻጽሮ ይበልጥ አሳማኝ ነው ወይም አይደልም ተብሎ ይዳኛል፡፡ ፍጹም የኾነ ሥነ መለኮት የለም፤ የስው እጅ ሥራዎች ናቸውና፡፡ በዚህ የእይታ መንጽር ውስጥ እኔም በአንድ ወቅት ልክ ናቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ሀሳቦች ሙግት አዋቅሬላቸው ሽንጤን ገትሬ ተሟግቼላቸው በሌላ ጊዜ የተሻለ መረጃ እና ርቱእ የሙግት ሀሳብ ሳገኝ ቀይሬ ይኾናል፡፡

በአጠቃላይ የሥነ መለኮታዊ ሀሳቦችን ፍጹም፣ ያለቀላቸው አድርጎ መምልክት ትክክል አይደለም ብዬ አስባለሁ፡፡ ሥነ መለኮታዊ ሀሳቦች በየጊዜው የሚክለሱ፣ በይዘትም ይኹን በአቀራረብ የሚሻሻሉ ናቸው፡፡ የትኛውም ሥነ-መለኮታዊ አቋም የማይቀየር የእግዚአብሔር ቃል አይደልም፡፡ ስለዚህ በየጊዜው ሊፈተሽ ይግባዋል፡፡

Dr. Tekalign duguma