Get Mystery Box with random crypto!

ኡጋንዳዊው ፓስተር ከስፖርት ውርርድ 26,800 ዶላር ካሸነፈ በኋላ የሚያገለግልባትን ቤተ ክርስቲያ | ናዝራዊ Tube

ኡጋንዳዊው ፓስተር ከስፖርት ውርርድ 26,800 ዶላር ካሸነፈ በኋላ የሚያገለግልባትን ቤተ ክርስቲያን ዘጋ!! እንዲህ የሚል ምስክርነትም ሰጠ፦

"ይህን ቤተ ክርስቲያን የከፈትኩት ተቀብቼ አይደለም። በስግብግብነት ምክንያት መሆኑን መቀበል አለብኝ። ብዙ ፓስተሮች ከህዝቡ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያገኙና ሰውን የበለጠ ለመሳብ የውሸት ትንቢት ሲናገሩ አይቻለሁ።

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተገነዘብኩ እንቅልፍ የሌላቸው ምሽቶች ማሳለፍ ጀመርኩ፣ ሁልጊዜም ያልተለመዱ ህልሞች አይ ነበር። ይህንን ቤተ ክርስትያን ከመክፈቴ በፊት ሁሉም ነገር በእኔ በኩል የተለመደ ነበር። ስለዚህ ይህንን ድርጊቴን ለመተውና እና ገንዘብ ለማግኘት ሌሎች መንገዶችን ለመፈለግ ወሰንኩ። አንድ ቀን የስፖርት ውርርድ ኖቲፊኬሽን በስልኬ ገባ። ከዛ በኋላ የስፖርት ውርርድ ስጫወት አጭበርባሪዎች መስለውኝ ነበር። በመጨረሻም አሸናፊ ሆኛለሁ!" ማለቱን የኡጋንዳው ቴሶ ቫይብስ ድረ ገፅ ነው የዘገበው።

የእኛዎቹ አንዳንድ ፓስተሮች ከዑጋንዳዊው አቻቸው ምን ይማራሉ?

Via፦Tewodros Teklargay
@nazrawi_tube