Get Mystery Box with random crypto!

ሌላ ኢየሱስ… ልዩ መንፈስ… ልዩ ወንጌል “የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም | ናዝራዊ Tube

ሌላ ኢየሱስ… ልዩ መንፈስ… ልዩ ወንጌል

“የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።” (2ቆሮ. 11:4)

1. “ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ” -
————————-
ከተሰበከው … መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን … የቀደሙን ምስክሮች እነጳውሎስ ከሰበኩት ጋር የማይመሳሰል ሌላ ኢየሱስ የሚሰብኩ አሉ።

Then, ሁል ጊዜ በመድረኮቻችን እየተሰበከ ስላለው ኢየሱስ ትክክለኛነት ወይም እውነተኛነት እርግጠኞች መሆን ይኖርብናል።

የተሰቀለውን ለሰው ልጆችም ኃጢአት የሞተውን ክርስቶስ ኢየሱስን ሳይሆን የሰውን ሥጋዊ ምኞትና ፍላጎት ለማሟላት የሚታዘዘውን ኢየሱስ እየተነሡ የሚልኩትን  ኢየሱስ የሚሰብኩ ሸቀጣሞች ምትሐተኞችና አስመሳዮች ሰባኪዎች አሉ። እንደዚህ ያሉትን ሰባኪዎች አትታገሡ። እንደ ቆሮንቶሶች አትሁኑ።

2. “ልዩ መንፈስ ብታገኙ” -
—————————
ያላገኘነውን ልዩ መንፈስ ሊሰጡ የሚመጡ የክርስቶስ ያልሆነውን መንገስ የሚያከፋፍሉ የውሸትን መንፈስ የሚያሰራጩ አሉ።

ያኔ ክርስቶስን ስናምን ከተሰጠን ከታተምንበት ቅዱሱ መንፈስ ጋር የማይናበብ፣ ለክርስቶስ ተገዢ እንድንሆንና ትዕዛዙን አክባሪ እንድንሆን የማያበረታታንን መንፈስ ሊያስተላልፉልን የሚመጡ የልዩ መንፈስ አቀባዮች አሉ።

ክርስቶስን ወደመምሰል የማያሳድገን መንፈስ በተቃራኒው ግን ምድራዊና ቁሳዊ ፍላጎቶቻችንን እየተከተልን እንድንከንፍ የሚጠይቀን መንፈስ የሚያናፍሱ ራሳቸውንም እንደ መንፈስ የሚቆጥሩ ሰባኪዎች አሉ። ይህ መንፈስ ስሙ ብቻ ነው እንጂ ዓይነቱ ሌላ ነው። አትታገሡአቸው። እንደቆሮንቶስ አትሁኑ።

3. “ልዩ ወንጌል ብታገኙ” -
—————————-
ከክርስቶስና ከርሱ ታማኝ አገልጋዮች ከተቀበልነው ወንጌል የሚለይ፣ ሰምተን ከዳንንበት ወደ ሕይወት መንገድ ካመጣን ከጌታችንና ከመድኃኒታችን  ወንጌል ጋር የማይጣጣም ልዩ ወንጌል ይዘው በየከተማው የሚዞሩ ሰባኪዎች አሉ።

የዘር የጎሳ የክፍፍል ወንጌል፣ የጥቅም የክብርና የዝና ወንጌል፣ የባሕል የልምድ የወግና የሥርዓት ብቻ ወንጌል፣ ስሜት ቀስቃሽ ብቻ ወንጌል፣ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ማኅበራዊ ጉዳዮች ወንጌል … የሚሰብኩ ዙሪያችን ላይ ቁጥራቸው ከፍ እያለ ነው።

የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚሰውር ወንጌል፣ አሰናካይና ወደ ኋላ ጎታች ወ ጌል፣ የግልሰቦችን ልምምድ  ብቻ የሚያራግብ ወንጌል ይዘው ወደ ቤታችን፣ ወደ ሠፈራችን፣ ወደ ሀገራችን የሚመጡ ሰባኪዎችን አትታገሡአቸው። እንደቆሮንቶስ አትሁኑ።

ወርቅነህ ኮየራ
@nazrawi_tube